«የተማሪዎቹ እገታ በብልጽግና የተቀነባበረ ነው»ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው ቡድን!
ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ፣መንግሥት ሸኔ የሚለው ቡድን በቅርቡ ከኦሮምያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን እግቷል መባሉን አስተባበለ።
የኦሮምያ መንግሥት ኮምኒኬሽን ቢሮ በዚህ ሳምንት አጋማሽ ባወጣው መግለጫ አሸባሪ ያለውን ቡድኑን በአጋችነት ከሷል። እገታውን በገዥው የብልጽግና ፓርቲ አባላት የተቀነባበረ ያለው ቡድኑ ግን ለእገታው «የብልጽግና ካድሬዎች ፣ሰላዮች እና የፀጥታ ኅይሎች»ያላቸውን ተጠያቂ ማድረጉን አዲስ ስታንዳርድ የተባለው የሀገር ውስጥ የህትመት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበሩት ከ160 በላይ ተማሪዎች የታገቱት ገርባ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ነበር። የኦሮምያ መንግሥት ከ167ቱ ታጋቾች መካከል 160ውን ማስለቀቅ መቻሉን እና ቀሪዎቹንም ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ባለፈው ረቡዕ ነበር ያስታወቀው ።ይሁንና ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የተማሪዎቹ ጓደኞችና ቤተሰቦች ግን እስከ ትናንት ድረስ ተማሪዎቹ አልተለቀቁም ብለዋል። ከእገታ ያመለጠ አንድ ተማሪም ትናንት እንደተናገረው ተማሪዎቹ አሁንም በአጋቾች እጅ ናቸው። ቤተሰቦች እንደሚሉት የሚገኙበት ሁኔታም አሰቃቂ ነው። አንድ የታጋች ተማሪ እህት ለዶቼቬለ እንደተናገሩት አጋቾቹ ደውለውላቸው ብዙ ገንዘብ እንዲያመጡ ጠይቀዋቸዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ