" እስከተባለው ጊዜ ካልገባችሁ በእጣና በሽያጭ ነው ለሌላ ነዋሪ የሚተላለፈው " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ የማይገቡበት ከሆነ ውል የሚቋረጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ማስጠንቀቁ ይታወሳል።
ኮርፖሬሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ማስተላለፉ አመልክቷል።
"በተለያዩ ጊዜያት በሽያጭ ተላልፈው የቤት ባለቤቶች ውል የተዋዋሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ አሁን ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀመባቸውና ለፀጥታ ስጋት እየሆኑ ይገኛል " ብሏል።
ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው እንደሚቋረጥ ገልጿል። ውል ከተቋረጠ በበኃላ በእጣ እና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፍ ነው ኮርፖሬሽኑ ' ለመጨረሻ ጊዜ ' ሲል ያስጠነቀቀው።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ