ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ እና 151 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሃብት ታግዶ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑ ተጠቆመ
46 መኖሪያ ቤቶች፣ 1 ሕንጻ፣ 86 ተሽከርካሪዎች፣ 81 ሺ ካሬ መሬት እግድ ወጥቶባቸዋል
ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ እና 151 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሃብት ታግዶ የወንጀል ምርመራ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የኦዲት ግኝት የባለድርሻ አካላት የትብብር ፎረም አመለከተ፡፡
የሦስት ዓመታት የኦዲት ግኝት የባለድርሻ አካላት የትብብር ፎረም የጋራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ውይይት ትላንት ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተካሂዷል፡፡
ፎረሙ ባለፉት ሦስት ዓመታት ትግበራው፤ ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ እና 150 ሚሊዮን 504ሺህ ዶላር ያህል ሃብት እግድ እንዲወጣ ማድረጉን በሪፖርቱ አመልክተዋል፡፡
እንዲሁም 46 መኖሪያ ቤቶች እና አንድ ሕንጻ፣ 86 ተሽከርካሪዎች፣ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚያወጣ የአክሲዮን ብር ዋጋ ያለው፣ 81 ሺህ ገደማ ካሬ የመሬት ይዞታዎች እግድ እንደወጣባቸው ተመልክቷል።
ፎረሙ ባካሄደው ግምገማ በፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት በግኝት ከለያቸው መካከል የጥሬ ገንዘብ ጉድለት፣ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከአንድ ወር ጀምሮ 10 ዓመትና ከዚያ በላይ የቆየ መሆኑ፣ የመንግሥትን ገቢ በወጡ ሕጎች መሠረት አለመሰብሰብ፣ ሕግን ያልተከተሉ ክፍያዎች መፈጸም ይገኙበታል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ