Video is unavailable for watching
Show in Telegram
“የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋ መጥቷል”_ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ
በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋ መምጣቱን ጠቅሰው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተቋማቱ ከ2 ዩኒቨርሲቲዎች ወደ 51 የመንግስት እና 315 የግል ተቋማት ማደጋቸውን እንዲሁም የተማሪዎች ምዝገባ ወደ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ገልጸዋል።
ነገር ግን የትምህርት ጥራት ማሽቆልቆሉን አምነው፣ ተቋማቱ ብቁ ተመራቂዎችን ለመፍጠር፣ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራዊ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ጥናትና ምርምሮችን ለማድረግ እንዲሁም ውጤታማ አስተዳደርን ለማስፈን እየሰሩ ነው ብለዋል።
አክለውም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ በ2011 ዓ.ም የወጣው የትምህርት ፍኖተ ካርታ የዩኒቨርሲቲዎች ራስን በራስ ማስተዳደርን እንደ ቁልፍ ማሻሻያ ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1294 መሠረት የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ በመሆን የሁለት ዓመት ሽግግር ያደርጋል ተብሏል።
በሚቀጥለው ዓመትም 10 ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች የራስ ገዝ አስተዳደር ማዕቀፉን እንዲቀላቀሉ እቅድ መያዙን አመልክተዋል።
እነዚህ ማሻሻያዎች ከፍተኛ መዋቅራዊ ለውጦችን እና በባለድርሻ አካላት መካከል የትብብር ጥረቶችን ይጠይቃሉ ብለዋል።
ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ይህን የገለጹት የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ዘጠኝ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ራስ ገዝ ለማድረግ የሚያስችል የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ባደረገበት ወቅት ነው።
!