ከጥበቃ ሰራተኛ ጋር በመመሳጠር ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ላፕቶፖችን በመስረቅ እና በመግዛት የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ነሐሴ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 መገናኛ ቤተልሄም ፕላዛ ከሚገኝ አንድ የንግድ ሱቅ ውስጥ ከሌሊቱ 10:00 አካባቢ ነው።
በአንድ ኤሌክትሮኒክስ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው የጥበቃ ሰራተኛ የተጣለበትን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከሁለት ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የሚጠብቀውን ሱቅ መስታወት በዘነዘና በመስበር 22 የተለያዩ አይነት ሞዴል ያላቸውን ላፕቶፖች ከግብረ አበሮቹ ጋር ይዘው ይሰወራሉ።
የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቁ በኋላ የምርመራ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ፖሊስ አስታውቋል። በተሰራው የምርመራና የክትትል ስራ በመጀመሪያ ሁለቱ ዋና የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው በተደረገ የምሪት ስራ ንብረቶቹ ከተሸጡበት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቶታል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ድረስ በመሄድ የተሰረቀውን ንብረት የገዙ ሦስት ግለሰቦችን በመያዝ ከሰረቁት 22 ላፕቶፖች ውስጥም 17ቱን ማስመለስ ተችሏል።
በአጠቃላይ 5 ተጠርጣሪዎች ተይዘው ጉዳያቸው በፍ/ቤት እየታየ ሲሆን የተሰረቀውን ንብረት በመግዛት የተጠረጠሩ ሦስቱ በዋስትና ወጥተዋል።
የምርመራ ስራው መቀጠሉን የጠቀሰው ፖሊስ እንደዚህ አይነት የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል ባለንብረቶች የጥበቃ ሰራተኞቻቸውን በቅርበት መከታተል እና ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝም ወዲያው ለጸጥታ አካላት ሪፖርት በማድረግ እንዲሁም ህብረተሰቡ ወንጀል ፈጻሚዎችን አጋልጦ መስጠት እንደሚጠበቅበት መልዕክት ተላልፏል።
via_አአ ፖሊስ
https://t.me/ethio_mereja_news