#ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?
ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፤ ሚስቱም መካን ነበረች ልጅም አልወለደችም። የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ አንቺ መካን ነሽ፣ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ። እነሆ ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።
ሴቲቱም ለባልዋ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደ መጣ አልጠየቅሁትም ስሙንም አልነገረኝም። እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አሁን የወይን ጠጅ የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ ርኩስም ነገር አትብዪ አለኝ ብላ ተናገረች። ማኑሄም “ጌታ ሆይ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እባክህ እንደ ገና ወደኛ ይምጣ፤ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንድናደርግ ያስገንዝበን” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም። ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ለባልዋም “እነሆ በቀደም ዕለት ወደ እኔ የመጣው ሰው ደግሞ ተገለጠልኝ” ብላ ነገረችው።
ማኑሄም ሚስቱን ተከትሎ መጥቶ “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን?” አለው። እርሱም፦ “እኔ ነኝ” አለ። ማኑሄም “ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? የምናደርግለትስ ምንድን ነው?” አለው። የእግዚአብሔር መልአክም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም “አንተ የግድ ብትለኝ መብልህን አልበላም፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበርና “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” አለው። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።
መልአኩም ተአምራት አደረገ፣ ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ ሲወጣ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ በምድርም በግምባራቸው ተደፉ። እርሱም ዳግመኛ አልተገለጠላቸውም፤ ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ለሚስቱም “እግዚአብሔርን አይተናልና እንሞታለን” አላት። ሚስቱም “እግዚአብሔርስ ሊገድለን ቢወድድ ኖሮ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ከእጃችን ባልተቀበለን፣ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን፣ እንዲህ ያለ ነገርም በዚህ ጊዜ ባላስታወቀን ነበር” አለችው። ሴቲቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሶምሶን ብላ ጠራችው፤ ልጁም አደገ፤ እግዚአብሔርም ባረከው። የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444