እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮ ቴሌኮም ከ47 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት ለማድረግ የሚያስችለውን ወሳኝ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው!!
መንግስት ያደረገውን የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ ኢትዮ ቴሌኮምን ወደ አክሲዮን ማኀበርነት ለመቀየር የተቋሙን 10 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ሽያጭ ከጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለ121 ቀናት በዲጂታል መንገድ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎችን በስፋት በመሳተፍ በተከናወነው የመደበኛ አክሲዮን ሽያጭ ከ47,377 ዜጎች ከ10.7 ሚሊዮን የአክሲዮን ድርሻ ዢ በዲጂታል መንገድ በማከናወን ብር 3.2 ቢሊየን የሚጠጋ ሀብት በማሰባሰብ ዜጎች በካፒታል ገበያ የሚሳተፉበትን መደላድል መፍጠር ተችሏል፡፡
የተሸጡ አክሲዮኖች ድልድል በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የማጽደቅ ሂደት ከተከናወነ በኋላ ውጤቱን የምናሳውቅ ሲሆን፣ ቀሪ አክስዮኖችን በተመለከተ አክሲዮን የገዙ ባለድርሻዎችን መብት ባስጠበቀ መልኩ በቀጣይ በዝርዝር የሽያጭ ሂደቱን የምንገልጽ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/42u5SrT