በዶሮ ቅርፅ የተሰራው የዓለማችን ትልቁ ሕንፃ
በፊሊፒንስ የሚገኘው በዶሮ ቅርፅ የተሰራ የዓለማችን ትልቁ ሕንፃ ለሆቴል አገልግሎት የተገነባ ነው፡፡
ይህ ግዙፉ ሆቴል 6 ፎቆች ያሉት ሲሆን ቁመቱ ከ114 ሜትር በላይ ሆኖ በውስጡ 15 ክፍሎች መያዙም ተነግሯል፡፡
በኔግሮስ ኦክሲደንታል ደሴት ላይ በሚገኘው ካምፑስቶሃን ሃይላንድ ሪዞርት ኮረብቶች አናት ላይ የሚገኘው ሆቴሉ ሌላ ለየት የሚያደርገው ነገር የሆቴሎቹ ክፍሎች መስኮት አልባ መሆናቸው ነው፡፡
ሆቴሉ የዶሮ ቅርጽ ያለው ትልቁ ሕንፃ በመባልም በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ መስፈር ችሏል።
የሆቴሉ ባለቤት ታን ሲናገር" ይህን ሕንጻ የሰራሁት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ለመቅጠር እና የወፍ ዘር ለኔግሮስ ሕዝብ ያለውን ጠቀሜታ ለማክበር እና ለማሳየት ነው" ብሏል፡፡
በሆቴሉ የመኝታ ዋጋ ለአራት ሰዎች የሚሆን አንድ ክፍል ከ80 የአሜሪካ ዶላር በታች ሲሆን እስከ ሰባት ለሚደርሱ ሰዎች የሚበቃው ክፍል ደግሞ 120 ዶላር ገደማ ወጪ ይጠይቃል ተብሏል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አካባቢው ለመዝናኛ ተመራጭ እየሆነ የመጣ ሲሆን፤ በዶሮ ቅርጽ የተሰራውን ግዙፍ ሕንፃ ለመመልከትም በርካቶች ወደ ስፍራው እያቀኑ መሆኑን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
(Ebc)