አንድ ድርጅት ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ ግብር እንዲከፍል የማይጠየቀው ድርጅቱ በአንድ የሂሳብ ጊዜ(የበጀት ዓመት) ውስጥ የተገኘውን ያልተከፋፈለ ትርፍ የሂሳብ ጊዜው በተጠናቀቀ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ የአባላቱን የአክስዮን ድርሻ መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል በተገኘው ትርፍ መጠን ያሳደገ እንደሆነ ነው፡፡
ድርጅቱ ያልተከፋፈለ ትርፍ የሌለው መሆኑን የሚያስረዳው በአንድ የሂሳብ ጊዜ(የበጀት ዓመት) ውስጥ የተገኘው የተጣራ ትርፍ የባለአክስዮኖችን የአክስዮን ድርሻ መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል ለማሳደግ የዋለ መሆኑን በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የፀደቀ ቃለ-ጉባኤ እና ከንግድ ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ካለው የክልል/የከተማ አስተዳደር ቢሮ የድርጅቱ ካፒታል ማደጉን የሚገልጽ ሰነድ በጣምራ በማቅረብ ነው በማለት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡
https://t.me/ethiolawreview