Posts filter


በገጠር ያለ የከተማ መሬት ላይ የተሰራ ቤትም ቢሆን እንኳ በይዞታው ላይ ያፈራው የማይንቀሳቀስ የግል ንብረቱ ስለሆነ ቤቱን መሸጥ የማይከለከልና ሽያጩም ህገ ወጥ ነው የማይባል ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል።


በገጠር ያለ የከተማ መሬት ላይ የተሰራ ቤትም ቢሆን እንኳ በይዞታው ላይ ያፈራው የማይንቀሳቀስ የግል ንብረቱ ስለሆነ ቤቱን መሸጥ የማይከለከልና ሽያጩም ህገ ወጥ ነው የማይባል ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል።
Join
https://t.me/ethiolawtips


ባል እና ሚስት ከፍቺ ቡኃላ ይቅር ለቤቴ ተባብለው አብረው ቢኖሩ #በሁኔታ ጋብቻ አለ ማለት አይቻልም።ይቅር ለቤቴ ብለው መኖር ከጀመሩ ከሶስቱ የጋብቻ መመስረቻ መንገዶች በአንዱ መጋባት አለባቸው በማለት የፈደሬሽን ምክር ቤት ወስኗል።
Join 👇
https://t.me/ethiolawtips


ዋዜማ- በፍትሕ ሚንስቴር ከደምወዝ ጭማሪ፣ ከቤት፣ ከትራንስፖርትና ከተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች አለመሟላት ጋር ተያይዞ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ ከ 3 መቶ በላይ ነባርና ልምድ ያላቸው ዓቃቤ ሕጎች ከመስሪያ ቤቱ በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ዋዜማ ከታማኝ ምንጮቿ ሰምታለች።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው በተቋሙ ከስምንት ዓመታት በላይ ያገለገሉ ከፍተኛ ዓቃቤ ሕጎች እንደገለጹት፣ በነዚህ ስምንት ዓመታት ውስጥ የደምወዝ ማስተካከያ የተደረገው አንድ ግዜ በ 2012 ዓ.ም ነው ብለዋል።

እየተከፈላቸው ያለው ክፍያ ከተሰጣቸው ተልዕኮ፣ ኃላፊነትና ከወቅታዊው የኑሮ ውድነት አንጻር እጅቅ ዝቅተኛ ነው ሲሉ ለዋዜማ የገለጹት ባለሙያዎቹ፣ በዚህም ምክንያት ሙያውን ወደው እና አክብረው እንዳይሰሩ “እንቅፋት ሆኖብናል” ሲሉ ገልጸዋል።

ከደምወዝ በተጨማሪ የቤት እና የትራንስፖርት ክፍያ ማስተካከያ ከተደረገላቸው ዓመታት መቆጠራቸውን ያነሱ ሲሆን፣ ባለሞያዎቹ በተደጋጋሚ አመልክተው መፍትሄ አለማግኘታቸውን አንስተዋል።

ዓቃቤ ሕጎቹ ለረጅም ዓመታት ሲጠይቁ የነበረው ሌላ ጥያቄ የቤት ጥያቄ መሆኑን ለዋዜማ ያስረዱ ሲሆን፣ ተቋሙን በሚንስትርነት ሲመሩ ከነበሩትና በቅርቡ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ከተሾሙት ጌዴዎን ጢሞቴዎስ አንስቶ ከሳቸው በፊት ለነበሩት ሚንስትሮችም ጥያቄው ሲነሳላቸው ነበር ሲሉ አክለዋል። ሆኖም “ጥረት እያደረግን ነው፣ እየተነጋገርንበት ነው” ከሚሉ ማዘናጊያ ቃላት በዘለለ እስከ አሁን ድረስ ጥያቄያቸው መልስ አለማግኘቱን ተናግረዋል።

ዓቃቤ ሕጎቹ ለዋዜማ እንደገለጹት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በፍትሕ ሚንስቴር ትይዩ ያለ ተቋም መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ ሆኖም በስሩ ላሉ ዳኞች በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ መገናኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመኖሪያ ቤት ገንብቶ ማስረከቡን ጠቁመዋል።

ሆኖም ፍትሕ ሚንስቴር ከላይ የተገለጹትን ጥያቄዎች ባለመመለሱ የተነሳ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ ከ 3 መቶ በላይ ዓቃቤ ሕጎች በራሳቸው ፈቃድ ከሥራ መልቀቃቸውንና፣ አሁንም መልቀቂያ እያስገቡ ያሉ በርካታ ዓቃቤ ሕጎች መኖራቸውን ይናገራሉ።

ከሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የለቀቁት ዓቃቤ ሕጎች በተቋሙ ውስጥ የረጅም ዓመታት ልምድ ያላቸው፣ ከባድ እና ውስብስብ የሚባሉ መዛግብት ሲሰሩ፣ ክርክር ሲያደርጉና ለውጤት ሲያበቁ የነበሩ ባለሙያዎች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ሁሉ ሲሆን በመስሪያ ቤቱ በኩል ልምድ ያለው ባለሙያ ለቀቀ ብሎ የመቆጨት፣ የመቆርቆርና የመጸጸት አዝማሚያ አለማየታቸው እንዳሳዘናቸው የሚገልጹት ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ባለሙያዎች፣ ይህም በፍትሕ ስርዓቱ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን አደጋ ቀላል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ እንደገለጹት በርካታ የሚባሉ የወንጀል፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ይዘት ያላቸውን መዛግብት ላይ ክርክር በማድረግ ከሥራ ሲወጡ ካለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት የተነሳ በታክሲ መሳፈር ቅንጦት ስለሚሆን፣ እንደማንኛውን ዜጋ በከተማ አውቶቡሶች ተጋፍተን ነው የምንሄደው ሲሉ ለዋዜማ አስረድተዋል።

የእነሱ ሙያ ከሌላው የመንግሥት ሠራተኛ በብዙ ነገር እንደሚለይ የሚገልጹት ዓቃቤ ሕጎቹ፣ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ የግድያ፣ የስርቆት እና ሌሎችም የወንጀል መዛግብት ላይ እንደሚከራከሩ በመግለጽ፣ እነዚህ መዛግብትም በግል ሕይወታቸው ለጥቃት ሊዳርጓቸው የሚችሉና የደኅንነት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ መሆናቸውን ያብራራሉ።

በጎረቤት አገራት ለዓቃቤ ሕጎች የሚከፈለው ክፍያና ጥቅማጥቅም እንዲሁም ለሙያው የሚሰጥው ክብር ከእኛ አገር ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር፣ ልዩነቱ የሰማይና የምድር ነው የሚሉት ባለሙያዎቹ፣ በዚህም ምክንያት ተቋሙ በርካታ ሠራተኞችን እያጣ እንደሆነ ገልፀዋል።


ሁሉም ሊያውቃቸው የሚገቡ ጠቃሚ የሕግ ምክሮች

1ኛ/ #ቅጂውን_ሳታገኙ_ወይም_ሙሉውን_ሳታነቡ_ምንም_ነገር_ላይ_አትፈርሙ!

ብዙ ጊዜ ሰዎች ለራሳቸው ቀሪ ቅጂ ሳይኖራቸው ወይም የተፃፈውን ሳይረዱ የተለያዩ ስምምነቶችን ይፈርማሉ። በዚህም የተነሳ ወዳልተገባ ክርክርና ጥል ውስጥ ይገባሉ። ስለዚህ ሁሌም ቢሆን የፈረሙበትን የስምምነት ቅጂ በወረቀት ኮፒ መያዝ ይመረጣል። ይህ የማይመች ከሆነ ደግሞ የፈረሙትን እያንዳንዱን ሰነድ በፍጥነት ፎቶ አንስቶ መያዝ ይገባል።

2ኛ/ #ቤተሰብዎንና_ንግድዎን_ከሕግ_ስጋት_ይጠብቁ!

የንግድ ስራ ሲሰሩ ድንገት የገንዘብ ዕዳ ቢከሰት እራስዎን እና ቤተሰብዎን ከዚህ ተጠያቂነት ማዳን የሚችሉት ኃ/የ/የግ/ማ ወይም አ/ማ ኩባንያ መስርተው ሲሰሩ መሆኑን ተረድተው ሀብትዎን የንግድ ድርጅት በማቋቋም ያንቀሳቅሱ!

3ኛ/ #የሕግ_ባለሙያ_እስኪያማክሩ_ድረስ_ሃላፊነትን_ወይም_ተጠያቂነትን_አምነው_አይቀበሉ!

በጭንቀት ወይም በፍርሃት ስሜት ዉስጥ ሆነን የምንናገራቸው ነገሮች እኛኑ መልሰዉ ሊጎዱን ይችላሉ ስለሆነም በፍርድ ቤት በፖሊስ ጣቢያ ወይም በሌላ መሰል ስልጣን ባላቸው አካላት ፊት የምንሰጣቸውን ቃላት ማስተዋል ያስፈልጋል። ከተቻለ የሕግ ባለሙያ ወይም ጠበቃ እስኪያማክሩ ድረስ ዝምታ ጥሩ መፍትሄ ነው።

4ኛ/ #የሕግ_ጉዳዮችን_በተመለከተ_የሕግ_ባለሙያ_ያማክሩ!

ከሕግ ባለሙያ ጋር መማከር በጣም አስፈላጊ ነው። ብዙ ጠበቆች በነፃ ወይም በክፍያ ወሳኝና አስፈላጊ ምክር ይሰጣሉ። የመንግስት አቃቤ ሕግም አቅም ለሌላቸው ወገኖች የሕግ ድጋፍ ያደርጋል። ስለሆነም የሰለጠነ ባለሙያ ጉዳይዎን እንዲመለከተው በማድረግ የሕግ መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ። ለምሳሌ፦ ውል ከመፈረምዎ በፊት ውሉ ልዩ የሕግ ቋንቋ የሚያካትት ከሆነ እነዚያ ድንጋጌዎች ብዙ ጊዜ ከባድ እና ያልተጠበቁ ውጤቶች ሊኖራቸው ስለሚችል ውሉን ከመፈረምዎ በፊት የሕግ ባለሙያ ቢያማክሩ ይመረጣል።

5ኛ/ #ማናቸውንም_ስምምነቶች_በጽሁፍ_ያድርጉ! #ሰነዱንም_ደህንነቱ_በተጠበቀ_ቦታ_ያስቀምጡ!

ሰዎች ያለማቋረጥ ስምምነቶችን ያደርጋሉ። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ እነኚህን ስምምነቶች በፅሁፍ አድርገው በጥንቃቄ ሲዋዋሉ አይስተዋልም።
ለምሳሌ እንደ ቤት ሽያጭ፣ የመኪና ሽያጭ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ ወዘተ ስምምነቶች ሕጋዊ ለመሆን ግዴታ በጽሁፍ መሆን አለባቸው። ስለሆነም ሁልጊዜ ስምምነቶችዎን በጽሁፍ የመፃፍ፣ ሁሉም ተዋዋይ ወገኖችና እማኞች መፈረማቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም ሰነዱን በጥቅቃቄ ማስቀመጥ ስምምነቱ የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ይረዳዎታል።Henok ayalwe


#የመፋለም ክስ ( petitory action)

ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡

ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ  ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡

ድንጋጌው የሚንቀሳቀስ ንብረትን የባለሀብትነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት በሌለው በፍ/ብ/ህግ አንቀፅ 1845 ስር የተመለከተው ተመሳሳይ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሆን ተፈልጎ ካለመሆኑ በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀስ ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት ባህሪ ያለው እና ከትውልው ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ የባለሀብትነቱ መብት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች( አንቀፅ 1168....)  ይሆን ዘንድ ተፈልጎ የተቀመጠ ድንጋጌ መሆኑን እንገነዘባለን።

በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መዝ/ቁ 43600)

N.B= ይህ ሲባል ግን ከውርስ፣ ከሽያጭ፣ ከስጦታና ከሌሎች ውሎች በመነጨ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ማለት የሚቻል ሳይሆን ለጉዳዩ አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቀመጡ የይርጋ ጊዜዎች የሚስተናገዱ ይሆናል።
https://t.me/ethiolawtips


የመቃወም አቤቱታ (ከውሳኔ በኋላ የሚቀርብ ክርክር ሥነሥርዓት)
================
1 • ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል በማለት አስቀድሞ ለአንድ ወገን የተሰጠውን ውሳኔ ለማሰረዝ በመቃወም አመልካች የሚቀርብ አቤቱታ ነው።
የመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ ክርክሩ የሚካሄደው በመቃወም አመልካች እና አስቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ ተጠቃሚ በሆነው የመቃወም ተጠሪ በሚባለው ወገን መካከል ሲሆን የዚህ ዓይነቱ ክርክር የሚቀርብበት እና የሚመራበት ስርዓት እንዲሁም የዚህ ዓይነቱን ክርክር የሚሰማው ፍርድ ቤት ስላለው ስልጣን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ከቁጥር 358 እስከ 360 ተመልክቷል፡፡ የመቃወም አቤቱታው መቅረብ የሚገባው በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 222 እና 223 ድንጋጌዎች መሰረት ክስ እና የማስረጃ መግለጫ የሚቀርብበትን ስርዓት መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ በግልጽ ተደንግጎአል፡፡
የመቃወም አቤቱታው እና የማስረጃው ቅጂ የመቃወም ተጠሪ ለሆነው ወገን እንዲደርስ መደረግ የሚገባው መሆኑን ከመግለጽ በስተቀር የመቃወም ተጠሪው የጽሁፍ መልስ እና የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚገባው በእነዚህ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ የተጻፈ ባይሆንም የመቃወም ተጠሪ የሆነው ወገን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 234 ድንጋጌ መሰረት ለቀረበበት የመቃወም አቤቱታ ያለውን የመከላከያ መልስ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚገባው ስለመሆኑ ከቁጥር 360(1) እና (2) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይም የመቃወሚያው ክርክር የሚሰማው የመጀመሪያው ክርክር በተሠማበት ስነ ስርዓት መሰረት ስለመሆኑ በቁጥር 360(2) የተመለከተው አስገዳጅ ድንጋጌ በቀጥታ የቀረበ ክስ እና ክርክር የሚስተናገድበትን ስርዓት በተመለከተ በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከቱት መሰረታዊ ድንጋጌዎች የመቃወሚያ ክርክርን በማስተናገድ ረገድም በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጻሚ ሊደረጉ የሚገባቸው መሆኑን በግልጽ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
በዚህ ድንጋጌ የተመለከተው የክርክር አመራር ስርዓት ዓይነተኛ ዓላማ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች እኩል ዕድል እንዲኖራቸው እና በተለይም የመቃወም አመልካች የሆነው ወገን የክርክሩ ተካፋይ ባልነበረበት ጊዜ የቀረበውን የመቃወም ተጠሪ ወገን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ በመስቀልኛ ጥያቄ እና በማስተባበያ ክርክር ጭምር የመፈተን ዕድል እንዲያገኝ ለማስቻል እንደሆነ ይታመናል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 86398 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 222፣ 223፣ 350-360
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 አንድ የክርክሩ ተካፋይ መሆን የሚገባው ሰው የክርክሩ ተካፋይ ሳይሆን ውሳኔ ተሰጥቶ ከሆነ እና ውሳኔውም ያረፈው በአንድ የክርክሩ ምክንያት በሆነ ንብረት ላይ ሁኖ ይህንኑ የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ወገንን መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑ ከተረጋገጠ ፍርዱ ይኸው ወገን ባለበት እንዲታይና በሕግና በማስረጃ የተደገፈ ሁኖ ሲገኝ እንዲነሳለት የሚደነግግ ነው፡፡ አቤቱታው የሚቀርብበት ሥርዓትም በቁጥር 359 ስር በተመለከተው መንገድ መሆን እንደአለበት የተቀመጠ ሲሆን ይህ ድንጋጌ የመቃወሚያ አቤቱታ አቀራረብ በክስ አመሰራረት አይነት ሁኖ ማስረጃ ዝርዝር ሁሉ ይህንኑ ስርዓት ማሟላት እንደአለበት ያስገነዝባል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ይዘቱና መንፈሱ ሲታይ ክርክሩ መኖሩን ከጅምሩ እያወቀ ውጤቱን በመጠበቅ ከፍርዱ በኋላ የፍርድ መቃወሚያ የሚያቀርበውን ወገን አቤቱታውን በመቀበል ለማስተናገድ አስፈላጊ ያለመሆኑን ሁሉ ያስገነዝባል፡፡


በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 145 መሠረት ማስረጃ ማስቀረብ
=======================
በሶስተኛ ወገን እጅ የሚገኝን ማስረጃ በተከራካሪው ጠያቂነት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስቀረብ የሚቻልበት ሥርዐት ነው።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145 መሰረት የተጠየቀ ማስረጃ ሳይቀርብ ፍርድ መስጠት የፍርድ አካሄዱ በተሟላበት ሁኔታ የተሰጠ ነው ለማለት የማይቻል መሆኑ የሚታመን ሲሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145 መሰረት የፍርድ ቤቱን እገዛ በመጠየቅ ማስረጃ ማስቀረብ የሚቻለው ግን ጠያቂው ወገን እንዲቀርብ የተጠየቀውን ማስረጃ ትክክል ግልባጭ በቅርብ ጊዜ ለማምጣት የማይችልበትን ወይም ማስገልበጫ የሚያስፈልገውን ወጭ ለመክፍል የማይችል መሆኑን እንዲሁም እንዲቀርብ የተጠየቀው ማስረጃ ለክርክሩ ምን ያህል ጠቃሚነት እንዳለው፤ ትክክለኛን ፍርድ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን በፅሁፍ ገልፆ ማስረዳት እንዲሚጠበቅበት የተጠቃሹ አንቀጽ ንዑስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል፡፡ በመሆኑም ተከራካሪ ወገን በፍርድ ቤት እገዛ ማስረጃ እንዲቀርብለት ሲጠይቅ በሕጉ የተመለከቱትን መስፈርቶችን በግልጽ ገልፆ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳት ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145(1) እና (2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያሳያል፡፡
የፍርድ ቤት ውሳኔ በማስረጃነት እንዲቀርብለት የሚጠይቅ ተከራካሪ ውሳኔው በየትኛው ፍርድ ቤትና በየትኛው የመዝገብ ቁጥር እንደተሰጠ ሳይገልጽ ከቀረ የጠየቀው ማስረጃ ሳይቀርብለት ውሳኔ እንደተሰጠበት የሚያቀርበው ቅሬታ የህግ ድጋፍ የለውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 89494 ቅጽ 15፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 145በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 145 መሠረት ማስረጃ ማስቀረብ
=======================
በሶስተኛ ወገን እጅ የሚገኝን ማስረጃ በተከራካሪው ጠያቂነት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስቀረብ የሚቻልበት ሥርዐት ነው።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145 መሰረት የተጠየቀ ማስረጃ ሳይቀርብ ፍርድ መስጠት የፍርድ አካሄዱ በተሟላበት ሁኔታ የተሰጠ ነው ለማለት የማይቻል መሆኑ የሚታመን ሲሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145 መሰረት የፍርድ ቤቱን እገዛ በመጠየቅ ማስረጃ ማስቀረብ የሚቻለው ግን ጠያቂው ወገን እንዲቀርብ የተጠየቀውን ማስረጃ ትክክል ግልባጭ በቅርብ ጊዜ ለማምጣት የማይችልበትን ወይም ማስገልበጫ የሚያስፈልገውን ወጭ ለመክፍል የማይችል መሆኑን እንዲሁም እንዲቀርብ የተጠየቀው ማስረጃ ለክርክሩ ምን ያህል ጠቃሚነት እንዳለው፤ ትክክለኛን ፍርድ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን በፅሁፍ ገልፆ ማስረዳት እንዲሚጠበቅበት የተጠቃሹ አንቀጽ ንዑስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል፡፡ በመሆኑም ተከራካሪ ወገን በፍርድ ቤት እገዛ ማስረጃ እንዲቀርብለት ሲጠይቅ በሕጉ የተመለከቱትን መስፈርቶችን በግልጽ ገልፆ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳት ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145(1) እና (2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያሳያል፡፡
የፍርድ ቤት ውሳኔ በማስረጃነት እንዲቀርብለት የሚጠይቅ ተከራካሪ ውሳኔው በየትኛው ፍርድ ቤትና በየትኛው የመዝገብ ቁጥር እንደተሰጠ ሳይገልጽ ከቀረ የጠየቀው ማስረጃ ሳይቀርብለት ውሳኔ እንደተሰጠበት የሚያቀርበው ቅሬታ የህግ ድጋፍ የለውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 89494 ቅጽ 15፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 145





10 last posts shown.