ከህግ ትምህርት ቤት መሠረታዊ ትሩፋቶች ጥቂቶቹ
*********
ምንጭ ወ/ሮ ትብለጥ ቡሽራ Tiblet Bushra
**********
የህግ ትምህርት ቤት በአንድ ወገን ብቻ የተነገረ ታሪክ ወይም ፍሬ ነገር ሁሌም ጎዶሎ እንደሆነ ያስተምርሀል፡፡ በምንም ጉዳይ አቋም ከመውሰድህ፣ ከመፍረድህ፣ አስተያየት ከመስጠትህ በፊት ሙሉ ታሪኩን ማወቅ በመርህ ደረጃ እንደቅድመ ሁኔታ ያስቀምጥብሀል ”There is always the other side of a story” ብለህ እንድታስብ ያስገድድሀል፡፡ ከዛ ውጪ የሚደረስ ድምዳሜ ትክክለኛ ያልሆነ ወይም የተዛባ፣ ያዳለ፣ ፍትሀዊነት የጎደለው ነው፡፡ ይህ አይነት አስተሳሰብ እንዲኖርህ የሚጠበቀው ደግሞ እጅህ ላይ በመጡ የህግ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን በአገራዊ ጉዳዮች፣ በግለሰቦች ጉዳዮች በምትሰማቸው ከአንድ ወገን የሚነገሩ ታሪኮች፣ ውሳኔዎችም ጭምር ነው፡፡
የህግ ትምህርት ቤት ለሀሳቦች ክፍት መሆንን (Open mindedness) ያስተምርሀል፡፡ እውነት ወይም ሀሰት ፈተና ቀርቦልህ ለአንድ ጥያቄ እውነትም ብለህ 10/10 ሀሰትም ብለህ 10/10 ልታገኝ ትችላለህ ልታጣም ትችላለህ፡፡ ለመልስህ እንዳቀረብከው የክርክር ነጥብ ጥንካሬ እና ምክኒያታዊነት፡፡ በዚህ አንተ ከያዝከው ሀሳብ የተለየ ሀሳብ ይዞ አሳማኝ ምክኒያት ለሚያቀርብልህ እጅ መስጠት እና የራስን ሀሳብ በምክኒያት መተው ሽንፈት እንዳልሆነ ያስተምርሀል፡፡
የህግ ትምህርት ቤት የሀሳብ ነጻነት ጠቀሜታን፣ የሀሳብ ነጻነት ማክበርን ወይም ለሌሎች እይታ ዋጋ መስጠትን ያስተምርሀል፡፡ በአንድ አከራካሪ ጉዳይ ላይ አስተማሪህ የያዘውን አቋም እያወክ ይህን ጉዳይ በፈተና መልክ ሲያመጣው ካስተማሪው የተለየው የራስህን አቋም በምክኒያት አስደግፈህ ካቀረብክ ከኔ አቋም ውጪ አቋም ኖረው ብሎ ዜሮ አይሰጥህም፡፡ ካንተ ጋር ባይስማማም እንደ መከራከሪያ ነጥቦችህ ጥንካሬ እና ምኪኒያታዊነት ከፍ ያለ ማርክ ሊሰጥህም ይችላል፡፡ ይህን ሲያረግ ከኔ ብትለይም ያንተን ሀሳብ አከብራለሁ፣ ዋጋ እሰጠዋለሁ፣ አቋሜን እያወክ የራስህን አቋም ማስቀመጥህን እንደንቀት አላየውም እንደጥንካሬ፣ እንደ እሴት ጭማሪ አየዋለሁ እንጂ የሚል ትምህርት ያስተምርሀል፡፡
የህግ ትምህርት ቤት ስለ “ጥርጣሬ ተጠቃሚ” “benefit of doubt” ጽንሰ ሀሳብ ሲያስተምርህ ይህን ጽንሰ ሀሳብ ከወንጀል ጉዳዮች በዘለለ በሌሎች ጉዳዮችም እንድትተገብረው ጥበብን (wisdom) ያስተምርሀል፡፡ ስለሆነ ሰው ወይም ጉዳይ የማትገምተው አይነት ነገር ስትሰማ “እውነት ላይሆን ይችላል” “ከሚመስለው ውጪ ሊሆን ይችላል እውነቱ” “ምናልባት ይሄን እንዲያደርግ ያስቻለው አስገዳጅ ሁኔታ ሊኖር እኮ ይችላል” እና የመሳሰሉ ሌላ ከሚኖሩ አጠራጣሪ ነገሮች ለመጠቀም የሚያስችለው ሁኔታዎችን ከግምት ማስገባትን ሊጨምር ይችላል፡፡
የህግ ትምህርት ቤት በመርህ ደረጃ በጭፍን መታዘዝ (blind obedience) ልክ አለመሆኑን ያስተምራል፡፡ ለአለቃ መታዘዝ አንደኛው የስነ-ምግባር ግዴታ ቢሆንም ህገ-ወጥ የሆነ ትእዛዝን አለመቀበል መብትህ ሳይሆን ግዴታህ አርጎ ያስተምርሀል፡፡ ይህ ትምህርት እና አመክኒዮው ደሞ ለሌሎች ጉዳዮችም እንድትጠቀመው ትምህርት ይሆንሀል፡፡
የህግ ትምህርት ቤት ስለሰው ልጆች ክቡርነት፣ እኩልነት፣ ነጻነት… እያስተማረህ ትህትናን/ humility፣ በምንም ሁኔታ ላይ ብትሆን አንተ ከማንም እንደማታንስ ከማንም እንደማትበልጥም ያስተምርሀል ወይ ደግሞ ያስታውስሀል።
የህግ ትምህርት ቤት ባህል፣ ወግ፣ ሀይማኖት፣ ማንነት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ወይም በግለሰቦች ውስጥ ያለውን ቦታ ያንን ችላ ያለ ምንም ነገር ዘለቄታ እንደማይኖረው ያስተምራል፡፡ በዛው ልክ ጎጂ የሆኑ ባህላዊ ድርጊቶችን ለመቀየር ወይም አዲስ ባህልን ለመፍጠር (to set Norm or standards) ሕግ ያለውን ኃይል ያሳይሀል
የህግ ትምህርት ቤት የህግ የበላይነትን መጠበቅ ወይም ማስጠበቅ ለሁላችንም የጋራ ሰላም፣ ደህንነት እና ጥቅም፣ ዋስትና መሆኑን ፈትፍቶ ያስተምርሀል፡፡