የባለስልጣኑ ሐዋሳ ቅርንጫፍ ባለፉት 2 ወራት መመሪያ በተላለፉ 33 መድኋኒት ተቋማትና ጤና ተቋማት ላይ ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እርምጃ መውሰዱን ገለፀ
24/01/2017 ሐዋሳ፡- ቢሮው ሐዋሳ ከተማን ማዕከል በማድረግ በሲዳማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች፣ በኦሮሚያ 8 ዞኖችና 5 ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በሶማሌ ክልል በሊበንና ዳዋ ዞኖች የቁጥጥር ስራ እየሠራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሐዋሳ ቅርንጫፍ ባለፉት ሁለት ወራት ባከናወናቸው የቁጥጥር ስራዎች ከ73 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የዕርዳታ መድኃኒቶች፣ 79 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የዕርዳታ የህክምና መሳሪያዎችና ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ለሚገመቱ የመዋቢያ ግብዓት ጥሬ እቃዎች ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ የመልቀቂያ ፈቃድ መስጠቱን የቅርንጫፉ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ንማኔ ገልፀዋል፡፡
ኃላፊው ጨምረው እንደገለፁት ህጋዊ መስፈርቱን አሟልተው ከተስተናገዱት ባለጉዳዮች በተጨማሪ ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ እንዲሁም ከተቋም ተሰርቀው የወጡ ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችንና የመዋቢያ ግብዓቶችን የያዘ ሲሆን መመሪያ በተላለፉ 33 የመድኋኒት ተቋማትና ጤና ተቋማት ላይ ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል፡፡
ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ቁጥጥር በሚያደርግባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተቆጣጣሪ አካላትን አቅም ለመገንባት በአራት ክልሎች ለሚገኙ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና የሠጠ ሲሆን ከጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በተለያየ ቀናት በጪጩ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ በቁጥጥር ስር የሚውሉትን መድኃኒቶች ቦታዉ ድረስ በመገኘት የመለየት እና ሙያዊ ማብራሪያ እየሠጠ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡