የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣንና ኢምፓወር ስዊስ ሳርል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
የካቲት 6/2017 አዲስ አበባ፡- በፊርማው ስነስርዓት ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ በአፍሪካ ውስጥ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የቀጠናው የስልጠና ማዕከል ለመሆንም በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በሐገሪቱ ከሚገኙ 12 ክልሎች እና ሁለት ከተማ መስተዳደሮች ስር ከሚገኙ ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በመቀናጀት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ ኢምፓወር ስዊስ ሳር መግባቢያ ሰነዱ እንዲዘጋጅ ለሰሩት ስራ እንዲሁም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስምምነቱን እንዲፈረም ላደረጉት አስተዋፅኦ አመስግነዋል።
የኢምፓወር ስዊስ ሳርል ዳይሬክተር እና መስራች ፕሮፌሰር ፖል ላልቫኒ በበኩላቸው ከስድስት ወራት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመመጣት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ፍላጎቶች ማጥናታቸውን የገለፁ ሲሆን ይህ ስምምነት ለባለስልጣኑ እና ኢምፓወር ስዊስ ሳርል ብቻ ሳይሆን ከተቋማት የዘለለ ጥቅም እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ ይህ ትብብር ለሁለቱም ወገኖች ጥቅም እንደሚያስገኝ እምነታቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የወክሉት ወ/ሮ ሃይማኖት አበራ ሚኒስቴሩ በዘርፉ የሀገሪቱን ፍላጎቶች በተገቢው ሁኔታ ለማሟላት ከባለስልጣኑ ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ተናግረዋል፡፡