ከደረጃ በታችና የተጭበረበሩ መድኃኒቶችን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በአዳማ ከተማ በተካሄደው የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ምግብን መድኃኒት ባለስልጣን የመድኃኒት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ እንደተናገሩት የአለም ጤና ድርጅት በ2017 ባወጣው ጥናት መሰረት በታዳጊ ሀገራት ከ10 መድኃኒቶች አንዱ ከደረጃ በታችና የተጭበረበሩ እንደሆኑ ገልፀው ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ የሆነ አለም አቀፋዊ ትብብር፣ የግንዛቤ ማስጨበጫና ያላሰለሰ ስራ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
ባለስልጣኑ ከደረጃ በታችና የተጭበረበሩ መድኃኒቶች ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የድርጊት መርኃ ግብር ማዘጋጀቱን ገልፀው ጉዳይ የተወሰኑ ተቋማትን ትብብር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካላትና አለም አቀፋዊ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀው ባለስልጣኑ ለሁሉም መድኃኒቶች ልዩ መለያ ኮድ ለመጠቀም ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተዘጋጀው የድርጊት መርኃ ግብር ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ኢንተርፖል፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የሙያ ማህበራት፣ የፍትህ አካላት፣ የመድኃኒት አምራቾችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ውይይት ውጤታማ ያደረጉ ሲሆን ከተሳታፊዎች በተነሱ አስተያየቶች መሰረት የተዘጋጀው የድርጊት መርኃ ግብር የባለድርሻ አካላትን አስተያየት መሰረት አድርጎ በቅርቡ ወደስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።