የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ለሀገር ውስጥ ባንኮች ዕድል ወይስ ስጋት?
*************************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከተጀመረ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ እድሜ አለው።
በእነዚህ ጊዜያትም ያጋጠሙትን መልካም እድሎች እና ፈተናዎች ተሻግሮ ዛሬ ላይ ደርሷል።
የዛሬ ቁመናውም ቢሆን የእድሜውን ያህል እንዳልሆነ በዘርፉ የተሠማሩ ምሁራን ይናገራሉ።
ይህንን እውነታ ለመለወጥ መንግሥት የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረግ የሚያስችል አዋጅ አርቅቆ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ እንዲጸድቅ አድርጓል።
የሕጉ መጽደቅ በብዙ የሚጠበቅ ቢሆንም፤ አሁንም ዜጎችም ሆነ በመስኩ የሚገኙ ምሁራን የመነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ ነው።
የውጭ ባለሀብቶች በባንክ ዘርፍ እንዲሠማሩ የሚፈቅደው አዋጅ ለሀገር ውስጥ ባንኮች ምን ይዞ ይመጣል፤ ተስፋ ወይስ ስጋት? በሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የሚኖረው ጠቀሜታስ ምን ይመስላል በሚለው ሃሳብ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች ምላሽ ሰጥተውናል፡፡
አቶ ክቡር ገና ይባላሉ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ናቸው። አዋጁ መጽደቁ የውጭ ባንኮች ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ የሚጋብዝ መሆኑን፤ ባንኮቹ ሊሠሩ የሚችሉትንና የማይችሉትን በዝርዝር ማስቀመጡን ይናገራሉ፡፡
የአዋጁ አቀራረብ ባንኮቹ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ሊያደርግ የሚችል ነው ወይስ አይደለም የሚለው ወደፊት ተግባራዊ ሲሆን የሚታይ ነው፡፡ የለውጡ ሂደት…
https://press.et/?p=143333