በምዕራብ ጎንደር ዞን 23 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ጥጥ እየተሰበሰበ መሆኑ ተገለፀ
****
(ኢ ፕ ድ)
በምዕራብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት 23 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ጥጥ በጥራት እየተሰበሰበ መሆኑ ተገለጸ።
በዞኑ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማትና ጥበቃ ባለሙያ አቶ ደግሰው አየለ ፤ እየተሰበሰበ ያለው የጥጥ ምርት በጥራት ተሰናድቶ ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት እንደሚቀርብ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በመኸሩ ወቅት በጥጥ ከለማው አጠቃላይ መሬት ውስጥ 12 ሺህ 300 ሄክታር የሚጠጋው በባለሃብቶች፤ ቀሪው ደግሞ በአርሶ አደሮች የለማ መሆኑን አስረድተዋል።
የምርት አሰባሰቡ ሂደት እስከ ተያዘው ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ታቅዶ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አመልክተው፤ አጠቃላይ ከለማው መሬት ከ422 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች ከተገነቡ የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካዎች እና የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ጥጡ የሚቀርብ መሆኑን ገልጸዋል።
በመኽር ወቅቱ 4 ሄክታር መሬት ላይ ጥጥ የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ የተናገሩት ደግሞ በመተማ ወረዳ ኮኪት ቀበሌ አርሶ አደር ቢሰጥ አየናቸው ናቸው።
ባለፉት ዓመታት በጥጥ ምርት ላይ የገበያ ችግር እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ግን ጥጥን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋታቸው ተፈላጊነቱ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።
በዚሁ ወረዳው የደለሎ ፋና ቀበሌ አርሶ አደር ደሴ አሻግሬ፤ በመኽር ወቅት በጥጥ ከሸፈኑት 3 ሄክታር መሬት ውስጥ 1 ሄክታር የሚሆነውን መሰብሰባቸውን ገልጸዋል።
ካለሙት መሬት ከ50 ኩንታል በላይ የጥጥ ምርት እንደሚጠብቁ ጠቅሰው፤ከምርት ሽያጭም የተሻለ ጥቅም አገኛለሁ ብለዋል።
ጥር 8 ቀን 2017 ዓም