ኢትዮጵያ ከ91ሺህ በላይ የሰብል ዝርያዎችን በዘረመል ባንክ አስቀምጣለች
*****
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከ91 ሺሕ በላይ የዝርያ ናሙናዎችን በዘረመል ባንክ በማንበርና በማስቀመጥ ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗ የኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
በኢንስቲትዩት አዝርዕትና ሆርቲካልቸር ብዝኃ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ውብሸት ተሾመ ለኢፕድ
እንደገለጹት፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዝኃ ሕይወት ሀብት በጊዜ ሂደት እየተመናመኑ፣ የአዝዕርትና ሆርቲካልቸር ዝርያዎች መካከል ተለያይነት እየጠፋ ይገኛል።
የተለያዩ ሀገራት አንድ አይነት ዝርያ ለመያዝና ለመጠቀም ተገደዋል። ለከባድ አደጋም ተጋልጠዋል።
ኢትዮጵያ የአዝዕርትና ሆርቲካልቸር ሀብትና ዝርያዎች ተለያይነት ከሚታወቁ ሀገራት አንዷ መሆኗን አመልክተው፤ የኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩትም ይህን ሀብት ዘላቂ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በእጅጉ እየተባባሰ የመጣው የዝርያ ተለያያነት መቀነስ እንደማያሰጋት ጠቁመው፤ በጂን ባንኩ ባለፉት አምስት አስርተ ዓመታት ከመላ አገሪቱ ከ91ሺህ በላይ ዝርያ ናሙናዎች ተሰብስበው ተቀምጠዋል። ይህም ከአፍሪካ አጠቃላይ 240 ሺህ ናሙና ብዛት አንፃር ከአንድ ሦስተኛ በላይ መሆኑንም ተናግረዋል። https://press.et/?p=144691