የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊዎች የመስህብ ስፍራዎችን እንዲጎበኙት በማድረግ ቆይታቸው ማረዘም ያሰፈልጋል
*******
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶች የመስህብ ስፍራዎችን እንዲጎበኙት በማድረግ ቆይታቸውን ለማረዘም የተለያዩ ጥቅሎች መዘጋጀታቸውን የኢትዮጵያ ቱሪዝምና ሆቴል ማርኬት ማህበር አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጠቀሜታ እንድታገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
የማህበሩ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሀስማ መፍቱ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊዎች የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝትና የባህላዊ ጥቅሎች ተዘጋጅቷል፡፡
በሀገሪቱ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን እንዲጎበኙና በማድረግ ቆይታቸውን ለማረዘም እየተሰራ ነው ብለዋል።
የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለእንግዶች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ግዴታቸው ነው ያሉትዳይሬክተራ ለ38ኛው የአፍሪካ ህብረት ተሳታፊዎች በቋንቋቸው ከማስተናገድ ጀምሮ ሌሎች የዝግጅት ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡
የማሪዎት ሆቴል ረዳት የሽያጭ ማናጀር ተወዳጅ ሙሉጎጃም በበኩላቸው፤ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የጉባኤውን ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ባህል በሚገልጽ መልኩ ተቀብለን ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ስንሰራ ቆይተናል ብለዋል፡፡
38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ሁለንተናዊ ዝግጅት መደረጉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በጉባዔው ከ15 ሺህ በላይ እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቋል።
በማርቆስ በላይ እና በሄለን ወንድምነው
የካቲት 4 ቀን 2017 ዓም