ሊቨርፑል ቶተንሃምን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ተጠባቂ ጨዋታ ሊቨርፑል ቶተንሃምን 6 ለ 3 አሸንፏል።
የቀያዮቹን የማሸነፊያ ግቦች ዲያዝ (2)፣ ማክ አሊስተር፣ ስቦዝላይ እና ሳላህ (2) ከመረብ አሳርፈዋል።
ቶተንሃምን ከሽንፈት ያላዳኑትን ግቦች ደግሞ ጄምስ ማዲሰን፣ ኩሉሴቭስኪ እና ሶላንኬ አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎም ሊቨርፑል በ39 ነጥብ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ማጠናከር ችሏል።
ቀደም ሲል በተካሄዱ ጨዋታዎች ቦርንማውዝ ማንቼስተር ዩናይትድን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ፥ ቼልሲ እና ኤቨርተን ደግሞ 0 ለ 0 ተለያይተዋል።