የኢትዮ-ቴሌኮም ሰራተኞች አቤቱታ ተቀባይነት አገኘ
የቴሌ ሰራተኞች ላለፉት አምስት አመታት በመስሪያ ቤቱ የውስጥ ዝውውር መታገዱን፣ ማደግም ሆነ መዘዋወር ከፈለገ በማናጀሩ ፍቃድ ብቻ እንደሚሰጥ፣ በመስሪያ ቤቱ ከ 15 አመት በላይ ሰርተን አንድ ደረጃ እንኳን ማደግም ሆነ ወደፈለግንበት መዘዋወር ፈፅሞ አይቻልም።
በመሳሪያ ቤቱ የሰራተኞች ህብረት ስምምነት መሰረት መስሪያ ቤቱ ከአመታዊ ዕቅዱ በላይ ሲሰራ እና አመርቂ አፈፃፀም ሲያስመዘግብ መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞች የመስሪያ ቤቱን አቅም ያገናዘበ የማበረታቻ እና የአመታዊ ደሞዝ ጭማሪ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት እንቀፅ 19 ላይ ይደነግጋል።
ነገር ግን ባሳለፍነው ማለትም 2016 አ/ም ስራተኞች በየትኛውም ፈተና ሳንበገር የፀጥታ ሁኔታ ሳይበግረን በመስራታችን መስሪያ ቤቱ የዕቅዱን 103 %ማሳካት ችሎ ነበር ነገር ግን ሰራተኛው ተደርጎ በማያውቀው በመስሪያ ቤቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ዝቅተኛ ማበረታቻ የአንድ ወር ተኩል ደሞዝ ብቻ ነው የተጨመረልን....እና ሌሎችም ቅሬታዎችን በማቅረብ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል።
አሁን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ኢትዮ ቴሌኮም ለሰራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ታውቋል። ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ለተወሰኑ ኢትዮ ቴሌኮም አመራሮች ጭማሪውን በተመለከተ ስሌት ሰርተው እንዲያመጡ ትዕዛዝ እንደሰጡ ተጠቁሟል።