ተመድ በሞት አፋፍ ላይ ያሉ 2 ሺህ 500 ህፃናት ለአስቸኳይ ሕክምና ከጋዛ እንዲወጡ ጠየቀ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከአሜሪካ ህክምና ባለሙያዎች ጋር ተገናኝተው ህፃናቱ ለሞት አደጋ መጋለጣቸውን ካረጋገጡ በኋላ፣ 2 ሺህ 500 ህፃናት ሕክምና እንዲያገኙ በአስቸኳይ ከጋዛ እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ለተመድ ማረጋገጫ የሰጡት አራቱ ዶክተሮች በጋዛ ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ባፈናቀለው እና የጤና ጥበቃ ሥርዓትን ባወደመው ለ15 ወራት በዘለቀው ጦርነት ወቅት በፈቃደኝነት የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ ናቸው።
በፈረንጆቹ ጥር 19 ቀን 2025 የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከመደረሱ ከቀናት በፊት፣ ከ12 ሺህ የሚበልጡ ታካሚዎች ለሕክምና ሊመውጣት እየተጠባበቁ እንደሆነና በስምምነቱ ሊወጡ እንደሚችሉ ተስፋ አድርጎ እንደነበር የዓለም ጤና ድርጅት አመላክቷል።
ይሁንና ከካሊፎርኒያ የመጡት የድንገተኛ ቀዶ ጥገና ሐኪም ፌሮዜ ሲድዋ እንደተናገሩት፣ አስቸኳይ ሕክምና ከሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች መካከል 2 ሺህ 500 ሕፃናት ይገኙበታል።
ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ የሰጡት ሲድዋ፣ እነኚህ 2 ሺህ 500 ህፃናት በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሊሞቱ እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡
አንዳንዶቹም አሁን ህይወታቸውን እያጡ እንደሆነ፣ አንዳንዶቹም ነገ ሊሞቱ እንደሚችሉ እና አንዳንዶቹ ደግሞ በቀጣዩ ቀን ህይወታቸው ሊያልፍ እንደሚችል ማመላከታቸውንም ሬውተርስ ዘግቧል።