Misrak Terefe ን አገኘኋት።
በቀድሞ አጠራሩ 3ኛ፤ አሁን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሚባለው ውስጥ፦ እስረኛ ሆና አገኘኋት።
ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኘነው የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ምርቃት እለት ነበር። ያኔ፤ እሷ ያሳተመችውን "ምጥቀት በቅኔ አክናፍ" መፅሐፍ በስጦታ አበረከተችልኝ። እና ተጨዋውተን፣ ተሳስቀን፣ ተፎጋግረን ተለያየን።
ዛሬ መታሰሯን አላመንኩም። ከጠዋቱ 3፡ 30 ነው አዲስአበባ ፖሊስ የተገኘሁት።
አላመንኩም ነበር ታሰረች መባሏን። ማታ/ለሊት ያውቋታል ወደምላቸው ሰዎች ስልክ መታሁ። መታሰሯን ማረጋገጥ አልቻልኩም።
እዚያ 3ኛ ግቢ ውስጥ ሳገኛት ነው እርግጠኛ የሆንኩት።
ሳስጠራት እየሳቀች መጣች።
"ቦታ ተቀያየርን አይደል?!" አለችኝ።
"እቅጩን በሃያ ዓመት" አልኳት።
የዛሬ ሀያ ዓመት እኔ እስረኛ ነበርኩ፤ እሷ ደግሞ ጠያቂዬ። አሁን የተገላቢጦሽ እሷ እስረኛ ነበር።
"የእናንተ ጊዜ መጨባበጥ ይቻል ነበር" አለችኝ እየሳቀች።
በመሃላችን ከሁለት ሜትር ርቀት ቢኖርም፣ በ "ነፃነት" አወራን፤ ምክንያቱም እኔ እና እሷ ብቻ ነበርን ተጠያያቂዎች።
"ፖሊሶች የጠየቁኝ አርትስ ቲቪ ላይ ቀርበው በነበሩ፣ ነገር ግን ሰሞኑን በቲክቶክ ላይ ተቆራርጠው በብዛት ሲዘዋወሩ በነበሩ ቪዲዮዎች ነው" አለች።
ገረመኝ።
"ለማንኛውም ፖሊስ የማጣራው ነገር አለ፤ የጊዜ ቀጠሮ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሎ ነበር። ፍርድ ቤት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ 7 ቀን ብቻ የሰጠው"
"ወከባ ምናምን አለ?"
"የለም፤ በጥሩ ሁኔታ ነው የያዙኝ፤ አድናቂዎቼ ሳይሆኑ አይቀሩም" አለችኝ እየሳቀች።
እንዲህ እንዲህ እያልን ለብዙ ደቂቃ አወራን።
ወሬ ሲያልቅብኝ "በቃ ቻው፤ ሰባት ቀን ምን አላት?፤ የዛሬ ሳምንት ስትወጪ ቀጨኔ አበቅየለሽ ቤት እጋብዝሻለሁ" አልኳት።
በዚሁ ተሰነባበትን።
በአጭሩ፤ ምስራቅ ተረፈ ብትታሰርም ከነ ሙሉ ፈገግታዋ ናት።
ከወሰንሰገድ ገ/ኪዳን