የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


Contact= +251901629875
✍️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ
✍️ የቤተክርስትያኗን ትክክለኛ አስተምህሮዋን የያዙ መጽሐፍት
✍️ አጭርና ተከታታይ ትምህርቶች
✍️ ለመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ
✍️ ወቅታዊ መረጃዎች
✍️ ስብከቶችን የሚያቀርብበት ገፅ ነው፡፡
በመርሐግብሩ ላይ አስተያየት ፥ ሐሳብ ፥ ጥያቄ ካለዎት ይጻፉልን @gibigubae_hasab_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


አስደሳች ዜና 🎉

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ተደራሽነቱን አስፋፍቶ በተለያዩ ማኅበራዊ ድኅረ-ገፆች ብቅ ብሏል።

የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ፣ መዝሙሮችን እና ወቅታዊ መረጃዎች በሚከተሉት አማራጮች ማግኘት ይችላሉ።

🎥 TikTok: https://www.tiktok.com/@aastugibigubaea

📸 Instagram: https://www.instagram.com/aastu_gebi_gubae/

▶️ YouTube: https://youtube.com/@aastugebigubae?si=GT67fzUYiaeoRnqc

ቤተሰብ ይሁኑ!!!

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን


✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።



ኑ እናገልግል!!!



በአገልግሎት ክፍላት መሳተፍ ለምትፈልጉ የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች በሙሉ!!

ከታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ እና እርስዎ በወደዱት ሰዓት መጥተው ያገልግሉ።


ለመመዝገብ 👉 Link

ማንም የማይቀማንን በጎ ዕድል በግቢ ጉባኤያችን እናግኝ!!!!!

  
ለበለጠ መረጃ፡- በ 0901629875
ወይም በ @gibigubae_hasab_bot ያናግሩን።

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን


የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ የተለያዩ መንፈሳዊ መርሐግብሮች የሚለቀቁበት የinstagram ገፃችንን በ https://www.instagram.com/aastu_gebi_gubae?igsh=YnkwY2o2NGdyc2M3 ይከታተሉ።

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን




“ስለ ምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው።”
ሉቃስ 22፥46


🌿🌿🌿🌿የምህላ ፀሎት 🌿🌿🌿🌿

ውድ የግቢ ጉባኤያችን ቤተሰቦች እነሆ ሁላችንም በጉጉት የምንጠብቃት አቤቱ ማረን፤ ይቅር በለን ብለን በህብረት እግዚአብሔርን የምንማፀንባት ምህላ ፀሎታችንን በነገው እለት የምንጀምር ሲሆን ሁላችሁም ከእህት፣ ወንድም ፣ጓደኞቻችሁ ጋር ተቀሳቅሳችሁ እንድትገኙ ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።

✨ዘወትር ከሰኞ -ዓርብ
✨ሌሊት 10:00 ብሎክ 2 ኮንቴነሮች ፊት ለፊት እንገናኝ

🔅እንዲደወልላችሁ የምትፈልጉ
+251904401279 ላይ 
ስማችሁን ከባች ጋር አድርጋችሁ ደውሉልኝ ብላችሁ መልዕክት አስቀምጡልን ።

መሐረነ አብ - ሃሌ ሉያ
ተሣሀለነ ወልድ - ሃሌ ሉያ
መንፈስ ቅዱስ መሐሪ ተዘከረነ በሣህልከ


▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን


ዝግጁ ናችሁ??

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔


የረቡዕ የአንድነት ጉባኤ

የሚኖሩን መርሐግብራት ፦
         ➫ጸሎት(ውዳሴ ማርያም )
         ➫መዝሙር በተጋባዥ ዘማሪ
         ➫ትምህርት በተጋባዥ መምህር
        

📆  ነገ ረቡዕ የካቲት 19 
⌚ 11:30
🗺️ ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን

✍️ ኹላችንም ከጓደኞቻችን ጋር ተቀሳቅሰን በጊዜ እራት በልተን እንገኝ።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን


እንኳን ለ0ብይ ጾም አንደኛ ሳምንት "ዘወረደ" በሰላም አደረሳቹ!!!

❓❓❓ይህን ያውቁ ኖርዋል❓❓❓

🎯🎯🎯🎯 የ 6:00 ና የ 9:00 ፃም ስትመዘገቡ ግቢ ጉባኤን እያገዙ አንድም ነዳያንን እየረዱ ነው፤ በጾም በቀላሉ ብዙዎች የሚመኙትን በጎ ስራ በዚህ መልኩ እየሰጡ ነው።

ጠዋት ጠዋት የግቢ ጉባኤ አባላት ዳቦውን በማውጣት እንደ ገቢ ምንጭነት ነዳያንን ለማስፈሰክ እና ግቢ ጉባኤውን ለመደገፍ ያውሉታል።

📌📌📌 መመዝገብ ፋልገዋል ?

ID በነፃ copy በማረግ ካፌ በር ላይ ምሳ እና ራት ሰዓት መጥተው ይመዝገቡ


ለበለጠ መረጃ፡ +251942865679

Non-Cafe ለሆናችሁ ይህ አገልግሎት አይሰጥም።

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን




“ስለ ምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው።”
ሉቃስ 22፥46


🌿🌿🌿🌿የምህላ ፀሎት 🌿🌿🌿🌿

ውድ የግቢ ጉባኤያችን ቤተሰቦች እነሆ ሁላችንም በጉጉት የምንጠብቃት አቤቱ ማረን፤ ይቅር በለን ብለን በህብረት እግዚአብሔርን የምንማፀንባት ምህላ ፀሎታችንን በነገው እለት የምንጀምር ሲሆን ሁላችሁም ከእህት፣ ወንድም ፣ጓደኞቻችሁ ጋር ተቀሳቅሳችሁ እንድትገኙ ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።

✨ዘወትር ከሰኞ -ዓርብ
✨ሌሊት 10:00 ብሎክ 2 ኮንቴነሮች ፊት ለፊት እንገናኝ

🔅እንዲደወልላችሁ የምትፈልጉ
+251904401279 ላይ 
ስማችሁን ከባች ጋር አድርጋችሁ ደውሉልኝ ብላችሁ መልዕክት አስቀምጡልን ።

መሐረነ አብ - ሃሌ ሉያ
ተሣሀለነ ወልድ - ሃሌ ሉያ
መንፈስ ቅዱስ መሐሪ ተዘከረነ በሣህልከ


▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን


“ከብር ይልቅ ትምህርትን ፥ ከተፈተነ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ።”

      ▬ ምሳሌ 8፥10 ▬


✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨


ሁላችሁም በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው የ2ኛው ሴሚስተር የ1ኛ እና የ2ኛ ዓመቶች ኮርስ ነገ ማክሰኞ ይጀመራል።


2ተኛ ዓመቶች በዚህ ሴሚስተር የኮርስ ቀናቹ ወደ ማክሰኞ የተዘዋወረ በመሆኑ ይህን አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን።


⛪️ ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን
🗓 ማክሰኞ፡ 18/06/2017 ዓ/ም
🕰 10:45 - 12:30

ኹላችሁም ተቀሳቅሳችሁ በጋራ እንድትመጡ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን


እውነት እውነት እላቹሃለሁ ንስሓን ከማይሹ ጻድቃን ይልቅ ንስሐን በሚገባ አንድ ኃጥዕ ሰው በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል:: ሉቃ15:10

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

🌿🌿🌿🌿የንስሐ ሳምንት 🌿🌿🌿🌿

ውድ የልዑል_እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ!!
እንኳን ለታላቁ ዓቢይ ፆም በሰላም አደረሳችሁ እያልን ግቢ ጉባኤያችን ከየካቲት 17-የካቲት 29 የንስሐ ሳምንት ማዘጋጀቱን ስንነግራችሁ በታላቅ ደስታ ነው ።ከእናንተ የሚጠበቀው ንስሐ አባታችሁ ጋር ሄዳችሁ ንስሐ መግባት ፤ ንስሐ አባት ያልተመደበላችሁ ደግሞ ከታች በተጠቀሰው ስልክ ደውላችሁ ማሳወቅ ነው።

🔊በተጨማሪም ይህን መልእክት ለሁሉም እያዳረሳችሁ የሐዋርያነት ኃላፊነታችሁን ተወጡ!!!

🌿የንስሐ አባት ከፈለጉ በእነዚህ ስልኮች ደውለው አስተባባሪዎችን ማናገር ይችላሉ።

☎️ስልክ:- 0955001943
       0940442282


▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬
➣የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን


መሐረነ አብ ጸሎት.pdf
349.7Kb
የምኅላ ጸሎት ጊዜ የሚባለው የመሐረነ አብ ጸሎት

ኹላችንም በርትተን በሌሊት 10:00 ብሎክ 2 ጋር እንገናኝ።
የያዕቆብ ሌሊት ያድርግልን!!!

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን


“ስለ ምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው።”
ሉቃስ 22፥46


🌿🌿🌿🌿የምህላ ፀሎት 🌿🌿🌿🌿

ውድ የግቢ ጉባኤያችን ቤተሰቦች እነሆ ሁላችንም በጉጉት የምንጠብቃት አቤቱ ማረን፤ ይቅር በለን ብለን በህብረት እግዚአብሔርን የምንማፀንባት ምህላ ፀሎታችንን በነገው እለት የምንጀምር ሲሆን ሁላችሁም ከእህት፣ ወንድም ፣ጓደኞቻችሁ ጋር ተቀሳቅሳችሁ እንድትገኙ ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።

✨ዘወትር ከሰኞ -ዓርብ
✨ሌሊት 10:00 ብሎክ 2 ኮንቴነሮች ፊት ለፊት እንገናኝ

🔅እንዲደወልላችሁ የምትፈልጉ
+251904401279 ላይ ደውሉልኝ ብላችሁ መልዕክት አስቀምጡልን ።

መሐረነ አብ - ሃሌ ሉያ
ተሣሀለነ ወልድ - ሃሌ ሉያ
መንፈስ ቅዱስ መሐሪ ተዘከረነ በሣህልከ


▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን


#የካቲት_16
#ኪዳነ_ምሕረት (#የሰባቱ_ኪዳናት_ማሕተም)

የካቲት ዐሥራ ስድስት በዚችም ዕለት የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም አማላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓልን ያደርጋሉ። በዚች ዕለት መታሰቢያዋን ለሚያደርግ ስሟን ለሚጠራ ለድኆችና ለችግረኞች እስከ ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጥ የክብር ባለቤት ከሆነ ከተወደደ ልጅዋ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተቀብላለችና።

ይህችም የከበረች እመቤታችን ልጅዋ ንጹሕ ሥጋዋን ተዋሕዶ ከብቻዋ ኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ ፈጽሞ ስለእኛ መዳን ወዶ ያደረገውን መከራ ተቀብሎ ሙቶ ተነሥቶ ከዐረገና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ እርሷን እናቱን ማርያምን በደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ዘንድ ትቷት ነበር እነሆ ልጅሽ እርሱንም እነሆዋት እናትህ ብሎ አደራ እንዳስጠበቀው።

ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ማርያም ትጸልይ ዘንድ ያለ ማቋረጥ ወደ ልጅዋ መቃብር ሁል ጊዜ ስትሔድ ኖረች ይኸውም ጎልጎታ ነው።

አይሁድም በአዩዋት ጊዜ ቍጣንና ቅናትን ተመልተው በድንጊያ ሊወግሩዋት ወደዱ እግዚአብሔርም ከዓይናቸው ሠወራት ከዚህም በኋላ ዳግመኛ መጥታ በዚያ እንዳትጸልይ ተማክረው ከመቃብሩ ዘንድ ጠባቂዎችን አኖሩ እርሷ ግን በየዕለቱ መሔድን አላቋረጠችም ጠባቆችም አያይዋትም የልጅዋ የጌትነቱ መጋረጃ ሠውርዋታልና መላእክትም መጥተው ያገለግሏታል ጌታችንም ዘወትር ይጐበኛታል የምትሻውንም ይፈጽምላት ነበር።

ከዚህም በኋላ መላእክት ወደ ሰማይ አሳረጓትና የጻድቃንን ማደሪያዎች አሳዩዋት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብም ወዳሉበት አደረሱዋት ከአዳም ጀምሮ እስከዚያ ዕለት በአካለ ነፍስ ያሉ አባቶች ሁሉ አንቺን ከሥጋችን ሥጋን ከዐፅማችን ዐፅምን ለፈጠረልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአምላክ ልጅ ከአንቺ ሰው በመሆኑ በአንቺ ድህነት አግኝተናል ከጥፋትም የሕይወት ወደብ ሆነሽልናልና እያሉ ሰገዱላት።

ከዚያም ወደ ተወደደ ልጅዋ የእሳት መጋረጃ ወደተተከለበት ወደ ጌትነቱ ዙፉን አደረሷት ጌታችንም እጇን ይዞ ወደ ውስጠኛው መጋረጃ አስገብቶ ከጌትነቱ ዙፋን ላይ አውጥቶ ከእርሱ ጋር አስቀመጣት ያዘጋጀላትንም ዐይን ያላየው ጆሮ ያልሰማው በሰው ልቡና ያልታሰበ ተድላ ደስታን ሁሉ ነገራት።

ከጌትነቱ ዙፋንም በታች የእስራኤል ንጉሥ አባቷ ዳዊትን የነቢያትና የመላእክት ማኀበር እንደ ግድግዳ ከበውት በመሰንቆ ሲያመሰግን አየችው እንዲህም ይላል ልጄ ስሚ በጆሮሽም አድምጪ ወገንሽን የአባትሽንም ወገን ርሺ ንጉሥ ደም ግባትሽን ወዷልና እርሱም ጌታሽ ነውና።

ዳግመኛም የሥቃይን ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ መላእክት ከዚያ ውሰዷት ለሰይጣንና ለሠራዊቱ በእርሱ ጐዳና ለሚጓዙ ሁሉ ወደተዘጋጀ ወደጨለማው ዳርቻ አደረሷት እመቤታችን ማርያምም ወዮልኝ ወደዚያ እንዳይመጡ ለሰው ልጆች ማን በነገራቸው አለች መልአኩም አመቤቴ ቡርክት ማርያም ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኖራልና ለአንቺም ከአንቺ በኋላም በቃል ኪዳንሽ ለሚታመኑ አትፍሪ አላት ከዚህም በኋላ ወደ ቦታዋ መለሷት።

ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ድንግል ማርያም ስለ ኋጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች እንደ ዛሬይቱም የካቲት ዐሥራ ስድስ ቀን በጎልጎታ ቦታ ቁማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች ልጄ ሆይ በእግዚአብሔር አባትህ በክርስቶስ ስምህ ከአንተ ጋርም ህልው በሆነ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ አማፅንሃለሁ ዓለም ሁሉ ሊሸከምህ የማይችል ሲሆን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በተሸከመችህ ማሕፀኔ አማፅንሃለሁ ልጄ ሆይ ያለ ሕማም ያለ ድካም ከእኔ በመውጣትህ በመወለድህ በአሳደጉህ ጡቶቼ በሳሙህ ከንፈሮቼ በአቀፋህ እጆቼ ከአንተ ጋር በተመላለሱ እግሮቼ አማፅንሃለሁ ። በውስጡ በተኛህበት በረት በተጠቀለልክበት ጨርቅ አማፅንሃለሁ የምወድህ ልጄ ሆይ በልቡናዬ ያለውን ሁሉ ትፈጽም ዘንድ የልመናዬን ቃል ሰምተህ ወደእኔ ትመጣ ዘንድ ወዳንተ ፈጽሜ እማልድሃለሁ።

የብርሃን እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲህ ብላ በጸለየች ጊዜ እነሆ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ከእርሱም ጋር አእላፍት መላእክት አሉ በዙሪያውም ሁነው ያመሰግኑታል እርሱም እናቴ ማርያም ሆይ ምን ላድርግልሽ አላት እመቤታችንም ለተወዳጅ ልጅዋ እንዲህ ብላ መለሰችለት ልጄ ወዳጄ ሆይጌታዬና ፈጣሪዬ አለኝታዬና መጠጊያዬ በእናቴ ማሕፀንም ሳለሁ ባንተ ጸናሁ አንተም ጠበቅኸኝ ሁልጊዜም ስም አጠራሬ አንተ ነህ።

አሁንም ጸሎቴንና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ እኔም አገልጋይህ የምለምንህ ይህ ነው መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ በስሜ አቢያተ ክርስቲያን ለሚሠሩ ወይም የተራቆተውን ለሚያለብሱ የተራበውን ለሚያጠግቡ የተጠማውንም ለሚያጠጡ የታመመውን ለሚጐበኙ ያዘነውን ለሚያረጋጉ የተከዘውንም ደስ ለሚያሰኙ ወይም ምስጋናዬን ለሚጽፉ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰውም ልቡና ያልታሰበውን በጎ ዋጋ ስጣቸው በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ ከሲኦል ነጻ አድርገው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረኃቡንና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽም ቃል ኪዳን እንዳይታበል በራሴ ማልኩልሽ አላት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን ድንግል ማርያም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን




​​ዘወረደ

የመጀመሪያ የዐቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ «ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3-13

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ”ገላ 4፥4 እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ ፡ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ።

ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው፡፡

ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው። እኛም በዚህ በዐብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀር እንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ።

ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፡፡

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን




✨✨✨ እንኳን አደረሳችሁ !!! ✨✨✨

⚜️⚜️⚜️ መዝሙር ዘዘወረደ ሰንበት ⚜️⚜️⚜️

ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ባዑ  ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕፃዲሁ በስብሐት እመንዎ (እ) ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ (እ) አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት (እ) ምሕረተ ወፍትሐ አሐሊ ለከ እዜምር ወዕሌቡ ፍኖተ ንጹሐ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ።

⚜️ ምስባክ አመ ፲፮ ለወርኃ የካቲት ሰንበተ ክርስቲያን ወበዓለ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት

ዘነግህ
መዝሙር ፻፲፪ ቁጥር ፱-፲
ዘያነብራ ለመካን ውስተ ቤቱ ፤
ወያስተፌሥሓ ለእመ ውሉድ ፤
ዘያነብራ ለመካን ውስተ ቤቱ ።
መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት።

ዘቅዳሴ
መዝሙር ፪ ቁጥር ፲፩ - ፫፪
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ፤
ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ ፤
አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዓዕ እግዚአብሔር ::
ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥
በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና።


⚜️ የዕለቱ ወንጌል
ዘነግህ
የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፭ - ፲፰
በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።
ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።
ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።
እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት። በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር። የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።መልአኩም እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።ደስታና ተድላም ይሆንልሃል በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።
በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል።እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።ዘካርያስም መልአኩን። እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።
ዘቅዳሴ
ዮዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲ - ፳፭
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን
እውነት እውነት እልሃለሁ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን ምስክራችንንም አትቀበሉትም።ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር እየመጡም ይጠመቁ ነበር ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ አልተጨመረም ነበርና።ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ።

በትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ትምህርታዊ ጽሑፍ ዝግጅት ንዑስ ክፍል የቆሎ ተማሪ የቴሌግራም መርሀ ግብር ዝግጅት ክፍል የቀረበ።
▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
        የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥  @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን





20 last posts shown.