ገደብ አልባ ፍቅር
አንተ አይሁድ ሆነህ እኔ ሰማሪያ
በሰው የተጠላሁ የሆንኩ ማስተማሪያ
ገደብን ሁሉ አልፈህ ስትገባ መንደሬ
ሕይወቴን ለውጠህ ልትሆን መምህሬ
ሕግጋትን ሽረህ መጣህ ወደ ቤቴ
ደፍርሶ የነበረው ጠራልኝ ሕይወቴ.
ለአንዲቷ ነፍስ ስለኔ ተጨንቀህ
ማለፍ ግድ ቢልህ ድንበር አቋርጠህ
በዛ በቀትር ከቀኑ ስድስት ሰዓት
ውሃ የሚቀዳ ማንም በሌለበት
ከጉድጕዱ አጠገብ ብቻህን ቁጭ ያልከው
ታሪኬን ለውጠህ አባት ልትሆነኝ ነው.
መች ጠምቶህ ሆነና ውሃ ስጪኝ ያልከው
ከኔ ተቀብለህ ልትጠጣ ያሰብከው
ወደ ተዘጋው ልብ የሚስጥሬ ጕዳ
ልትገባ ነው እንጂ ፈልገህ ቀዳዳ.
ልክ እንደ ልማዴ ሰዓቴን ጠብቄ
ውሃ ልቀዳ ብመጣ እርቄ
የሕይወቴን ጌታ በዛ አገኘውት
ልቤን ከፍቼ ከቤቴ አስገባውት.
አይሁድ ነህ ብዬ ችላ ያልኩት ሰው
ያውቀኛል ብዬ ከቶ ማልጠብቀው
ጉዴን ሁሉ ነግሮ ወንጌል አሰበከኝ
ውሃ አጠጪኝ ብሎ የሕይወት ምንጭ ሆነኝ.
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳቸዋለ💙
---------------------------------------------------------
SHARE
@gitim_alem @gitim_alem
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8
አንተ አይሁድ ሆነህ እኔ ሰማሪያ
በሰው የተጠላሁ የሆንኩ ማስተማሪያ
ገደብን ሁሉ አልፈህ ስትገባ መንደሬ
ሕይወቴን ለውጠህ ልትሆን መምህሬ
ሕግጋትን ሽረህ መጣህ ወደ ቤቴ
ደፍርሶ የነበረው ጠራልኝ ሕይወቴ.
ለአንዲቷ ነፍስ ስለኔ ተጨንቀህ
ማለፍ ግድ ቢልህ ድንበር አቋርጠህ
በዛ በቀትር ከቀኑ ስድስት ሰዓት
ውሃ የሚቀዳ ማንም በሌለበት
ከጉድጕዱ አጠገብ ብቻህን ቁጭ ያልከው
ታሪኬን ለውጠህ አባት ልትሆነኝ ነው.
መች ጠምቶህ ሆነና ውሃ ስጪኝ ያልከው
ከኔ ተቀብለህ ልትጠጣ ያሰብከው
ወደ ተዘጋው ልብ የሚስጥሬ ጕዳ
ልትገባ ነው እንጂ ፈልገህ ቀዳዳ.
ልክ እንደ ልማዴ ሰዓቴን ጠብቄ
ውሃ ልቀዳ ብመጣ እርቄ
የሕይወቴን ጌታ በዛ አገኘውት
ልቤን ከፍቼ ከቤቴ አስገባውት.
አይሁድ ነህ ብዬ ችላ ያልኩት ሰው
ያውቀኛል ብዬ ከቶ ማልጠብቀው
ጉዴን ሁሉ ነግሮ ወንጌል አሰበከኝ
ውሃ አጠጪኝ ብሎ የሕይወት ምንጭ ሆነኝ.
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳቸዋለ💙
---------------------------------------------------------
SHARE
@gitim_alem @gitim_alem
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8