የጉብሬና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል 🇸🇦


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


📲 የአምስተኛው ዙር የ1000 ቆራጥ ሰዎች የ 200 ብር ቻሌንጅ ተጀመረ!

በወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ሰለፍይ ተማሪዎች ጀመዓ የመሬት ግዢ እና የመስጂድ ማስገንቢያ ግሩፕ ላይ የ1000 ቆራጥ ሰዎች የ 200 ብር ዘመቺያ ፕሮግራም አምስተኛው ዙር ተከፈተ። እነሆ ዘመቻው እስከ ሌሊቱ 06:00 የሚቀጥል ሲሆን‌‌ በርካቶች እንደሚሳተፉ ተስፋ እናደርጋለን።

እንደሚታወቀው ዛሬ ረመዷን 12 ላይ ነው የምንገኘው። ስለዚህ በዚህ ወር ላይ የሚገኝን የሶደቃ ትልቅን ትሩፋት በማሰብ ለጨለማው ቤታችን ለቀብርና ለዘላለማዊው ሀገራችን የሚበቃንን እንከስብ። መድረኩ የሶደቀቱል ጃሪያ መድረክ ነውና በአላህ በጎ ፈቃድ ከሞትንም ቡሀላ በመስጂዱ ከሚሰሩ ኸይር ስራዎች ሁሉ በቀጣይነት የምንመነዳ ይሆናል።

📲 የአካውንት ቁጥር
1ኛ, የ C.B.E 1000619092175
ሙሀመድ, አ/ሀሚድ, ኢብራሒም
2ኛ, የ አቢሲኒያ 192421349
ሙሀመድ, አ/ሀሚድ, ኢብራሒም

ወደ ግሩፑ ለመቀላቀል
https://t.me/welkiteunver
https://t.me/welkiteunver


📜 ማርች 8 የማጭበርበሪያ እና የትዝብት ቀን!

     በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ማርች 8 (እንደሚሉት ከሆነ) በየአመቱ እንደ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተብሎ የሚከበርበት ቀን ነው። በዚህ ቀን በርካታ መድረኮች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ስለ ሴቶች ክብር፣ መብት እና እኩልነት የመሳሰሉትን ያወራሉ። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ኢስላምን እና ከሴቶች ጋር ያለው የተባረኩ ህግጋቶችን ይተቻሉ። ይህንን የኢስላም ህግን የሚጠብቁ ሀገሮችን፣ ተቋሞችን እና ቤተሰቦችን በጭቆና እና በመብት መንፈግ ይተቻሉ።

ኢስላም ማለት በየትኛውም ቦታ፣ ዘመን እና ሁኔታ ለሰው ልጆች የሚመጥ እና ዘመን የማይሽራው ሀይማኖት ነው። በዱንያም ይሁን በአኼራ ለሰው ልጆች መንፈሳዊም ይሁን ገሀድዊ ደስታ እና ስኬት መሰረት ነው። ከኢስላም ውጪ የሰዎች ጥቅም የሚያስጠብቅ ጉዳትን ደግሞ የሚያስወግድ እና የሚከላከል ሀይማኖት በጭራሽ የለም። ፈጣሪም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ከአደም ጀምሮ ከሰማይ የተዘረጋ ብቸኛ ሀይማኖት ኢስላም ነው። አይሁዳዊነት፣ ክርስትና እና ሌሎችም ሀይማኖቶች በሰውልጆች ጠባብ አእምሮ መሰረት የተፈበረኩ ድርሰቶች ናቸው።

ኢስላም ለሴቶች (በተለይም ለእናት) ለየት ያለ እይታ አለው። ለሴቶች ወደር የሌለው እንክብካቤ አለው። ለመጀመርያ ግዜ የድንቁርናውን ዘመን የጭቆና ቅንበርን ከሴት ልጅ ጫንቃ ላይ ያነሳው ኢስላም ነው። ኢስላም ለሴቶች ያለው ትኩረት ትልቅ ለመሆኑ በቁርአን ውስጥ በነሱ ስም «የሴቶች ምእራፍ» የሚባል ምእራፍ መኖሩ ማሳያ ነው። በየትኛውም ሀይማኖት ውስጥ ባልታየ መልክ በመርየም ስምም ሱራ አለ። ለሴት ልጅ የሚገባትን እንክብካቤ እና ክብር እንዲሰጣት ያደረገው ኢስላም ነው። ኢስላም ለሴቶች ያለውን ክብር እና ቦታ ለማወቅ የፈለገ ሰው የታላቁን ፈጣሪ መፅሀፍ ቁርአንን እንዲሁም የነብያዊ ጥቅሶችን በንፁህ አእምሮ ያጥና። በተጨማሪም በርካታ የሆኑ የሊቃውንቱን ድርሰቶችን ያጥና።

ምእራባውያን የኢስላምን ትልቅነትንና መለኮታዊነት ባወቁ ግዜ የሚችሉ መስሏቸው ኢስላምን ለማጣጠል እና ለማንቋሸሽ ብለው ካጠመዷቸው በርካታ ወጥመዶች መካከል አንዱ ማርች 8 ነው። ብዙ ሰዎች (በተለይም ሴቶች) በዚህ ቀን ማላዘብ የምር ለሴቶች ክብር እና መብት የተጨነቁ ይመስላቸዋል። አመቱን ሙሉ የሚደረገው የመብት መግፈፍ እና ጭቆናን በአንድ ቀን መዝሙር ይረሱታል። በተቃራኒ ደግሞ ያለውን ተጨባጭ እና እውነታ የሚያውቁ በርካታ ሰዎች አመቱን ወደሃላ በማሰብ ይህንን ቀን እና የዚህ ቀን ወሬን ታዝበው ያልፋሉ።

ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጭቆናዎች በጣም በርካታ ናቸው። በየቦታው የሚታየው የብዙሀኑን ሴት መብት የገፈፈው የኒቃብ መልበስ እገዳ እና ከሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ በርካታ እገዳዎች (ለምሳሌ የት/ት እገዳ) ማሳያ ናቸው። መልበስ ተፈጥሯዊ እና ሰብአዊ መብታቸው አልነበረም ለምን ይታገዳሉ?! በብስለት ላጤነ ሰው ሴት ልጅን እንድትራቆት፣ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ልቅ የሆነ መስተጋብር እንዲኖራት እና ከወንደንዶች ጋር የተለያዩ መድረኮችን እንድትጋራ መፍቀድ ከዚህ በላይ ክብሯን ዝቅ ማድረግ የለም። ከዚህም ባሻገር በየሆስፒታሉ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ተገቢውን ክትትል ባለማግኘት እና የሴት አዋላጆች እጥረት ምክንያት በርካታ እናቶች ህይወታቸው ያልፋል። በየመስሪያ ቤት ስራ ፍለጋ ከቀረበች ወይ ውድድር ውስጥ ከገባች በተለይ ሙስሊም ከሆነች ካልተገላለጠች፣ ሴትነቷን ካልሸጠች ወይም ሌላ መጥፎ ነገር ውስጥ ካልገባች ስኬታማ አትሆንም። አረ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆና ብዙ ነው። ይሄ ሁሉ በሚታይበት የሴቶች መብት እያሉ ማላዘብ ማጭበርበሪያ እንጂ ምንም አይደለም።

በዚህ ዘመን የሴት ልጅን መብት እናስከብራለን በሚል ሽፋን እንድትገላለት፣ እንድትራቆት፣ ከወንድ ጋር እንድትቀላቀል፣ ሚዲያ ላይ እንድትወጣ፣ በቴሌ-ቪዥን መስኮት እንድትታይ ወዘተ የሚያደርጉ ሰዎች እያረከሷት ነው። ከዚህም አልፎ በተለያዩ ምርቶች ላይ ፎቶዋን በመለጣጠፍ ማሻሻጪያ ብልጭልጭ አድርገዋታል። ይሄ ሁሉ ባለበት ማርች 8 የበለጠ ከዚህ በላይ እንድትረክስ የሚደረግበት እንጂ ሌላ አይደለም። ሴትን ልጅ ወደ ክብሯ ወደ ልእልትነቷ መመለስ የሚቻለው ወደ ኢስላም በመዞር ቢቻ ነው። የሷን መብት እና ልቅናን ማስጠበቅ የሚቻለው ወደ መሸፋፈኗ፣ ከጥፋት ስፍራ በመራቋ፣ ሴትነቷን በመጠበቋ እንዳጠቃላይ የኢስላምን መርህ በጠበቀ መልኩ ሲሆን ቢቻ ነው።


ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


👆👆👆
🔈
#በደካማ ሀዲስ የመስራት ፍርድ እንዲሁም ለዱዓቶች እና ለኸጢቦች ምክር!

🔶 በአዲስ አበባ አል- ወሰጢየህ መርከዝ እና መድረሳ ከሚሰጥ ደርስ የተወሰደ።


🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan


አላህን የመፍራት ትሩፋቶች ብዙ ናቸው።

1, ከተለያዩ ጭንቆች መውጫ መፍትሔ (ቀዳዳ) ማግኘት።
2, ከማናስበው በኩል የአላህ ሲሳይ መምጣት።
3, ጎዳዮችን አላህ ገር ያደርግልናል።
4, የአላህ እርዳታን ማግኘት።
5, እውቀት እና ጥበብን ማግኘት።
6, የወንጀል መማር እና የምንዳ መተለቅ።
7, ከአላህ አስፈሪ ከሆነው ቅጣት መዳን።
8, ለታማኝነት መገጠም።
9, የአላህን ውዴታ ማግኘት።
10, ስኬትን እና ሀሴትን ማግኘት።
11, ለአላህ ፈሪዎች የተዘጋጀውን ጀነት ማግኘት።
12, ምፅዋታችን ተቀባይነት ያገኛል።
13, ከአደጋ መጠበቅ።
14, የእለተ ትንሳኤ የበላይነትና ልቅና ማግኘት።
15, ስጋት እና ፍራቻ መወገዱ።

ወዘተ… በጣም ብዙ ነው። ስለዚህ አላህን እንፍራ።

https://t.me/abuzekeryamuhamed


Forward from: ጄጄ ቴክኖሎጂ_ለሰለፊዮች
base (13).apk
54.2Mb
🚨 አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
   
📱 አድስ አፕሊኬሽን ተለቀቀ
      〰〰〰〰〰〰〰

ረመዷንን በእውቀት እንቀበለው

በሚል ርእስ የተዘጋጀ አፕ ነው።

↪️ የኪታቡ ስም ⬇️
📚ሙኽተሰሩን ፊ' አህካሚ ሲያም
📚 ወጃአ ሸህሩ ሯመዷን
📚 ከይፈ ነስተቅቢሉ ሸህሯ ሯመዷን

 ሶስት ኪታብ  54MB
ሶስት ኪታቦችን ባአንድ ለይ የያዘ አፕሊኬሽን ነው


ሼር በማድረግ የድርሻችንን እነወጣ!


╭🎙የደርሶች አቅራቢ:___
├─┈┈┈✑ኡስታዝ መሀመድ አል ወልቂጢይ
╰──────────────
                  
╭🎙አዘጋጅ_
├─┈┈ጄጄ ሰለፊይ App Developer
╰──────────────
ለሌሎችም ሼር
├─┈┈┈✑ በማድረግ የአጅሩ
ተካፍይ ይሁኑ!   https://t.me/technologybyAbdu
╰──────────────

📨 አፖችን በትእዛዝ ለማሰራት ይህን የግለ  አድራሻችንን ይጠቀሙ
          @Abdurejj
│       @Abdurejj
╰─────

ከዚህ በፊት የተለቀቁ አፖችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀላሉ 👇👇👇👇

t.me/technologybyAbdu

t.me/technologybyAbdu

t.me/technologybyAbdu


Forward from: ጄጄ ቴክኖሎጂ_ለሰለፊዮች
📲 አፑ አልወርድም ያላችሁ ወንድም እህቶች በቀይ የተከበበውን በመንካት ማውረድ ትችላላችሁ።


Forward from: ጄጄ ቴክኖሎጂ_ለሰለፊዮች
🍎 አርበዑነ አልለተሚያ
   የተከበራችሁ የሱና ወንድምና እህቶች የሚታወቅን ማስተዋወቅ ክብሩን መንካት እንዳይሆንብኝ እየሰጋሁ ሸይኻችን ሽይኽ ዐ/ሐሚድ የፃፉት በይዘቱ አነስ ያለ በውስጡ የያዘው ድልብ ከፍ ያለ በሰለፍያ ኑሱሶች ያሸበረቀ በሰለፍይ ዑለሞች ተዕሊቃቶች የታጨቀ ለጀማሪም ሆነ በእውቀት ለሄዱት ጠቀሜታው ከፍ ያለ ኪታብ ላስተዋውቃችሁ ወደድኩ ።
   ይህ ኪታብ ከላይ ለመግለፅ እንደ ሞከርኩት ሸኹ  ወዳጅ ሳይሆን ጤነኛ አእምሮ ያለው ጠላት የሚመሰክርላቸው አላህ የሰጣቸው የእውቀት ባልተቤት ናቸው ። እውቀታቸውን ለየት የሚያደርገው አላህ ባገራላቸው ሒፍዝ የታጀበ መሆኑ ነው ። ይህ ከመሆኑ ጋር በዚህ ኪታባቸው ከብርቅዬ የሰለፍ ዑለሞች ንግግር ውጪ አንድም የራሳቸው ማብራሪያ አላካተቱበትም ። ሚዛናዊ ለሆነ ሰው ይህ የማንነታቸው ማሳያ ነው ። ኪታቡ ይዘቱ ትንሽ ከመሆኑ ጋር በውስጡ የያዛቸው ሐዲሶች አመራረጣቸው የርእስ አሰጣጣቸው የሸኹን የዒልም ጥልቀት ማሳያዎች ናቸው ። ቀለል ባለ አቀራረብ ከባባድ መርሆችን የሚያሲዝ በአይነቱ ለየት ያለ ኪታብ ነው ። በየትኛውም ቦታ ያላችሁ ሰለፍዮች በተለይ የዲን ተማሪዎች የመርከዝና የመድረሳ ኡስታዞች ይህን ኪታብ በሒፍዝ እንዲሸመደድ በማድረግና ራሳችሁም እንድትጠቀሙበት አደራ እላለሁ ። አላህ ሸይኹን ሐያታቸውን አርዝሞ በሱና ላይ አፅንቶ ኢስላምንና ሙስሊሞችን የሚጠቅሙ ያድርግልን ። የዚህ ስራ ምንዳቸውን በመልካም ስራ መዝገባቸው ላይ ያኑርላቸው አሚን ።
https://t.me/bahruteka


Forward from: ጄጄ ቴክኖሎጂ_ለሰለፊዮች
base (12).apk
59.3Mb
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
   
📱 አድስ አፕሊኬሽን ተለቀቀ
      〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የኪታቡ ስም ⬇️
     📚  አርበዑነ አል-ለተሚየህ ፊ' ዐቃኢዲ ወልመናሂጂ አልሰለፊየህ

╭───የኪታቡፀሓፊ─────────
   فَضِيلَةِ الشَّيخِ عبد الحميد بن ياسين السني السلفي السلطي اللتمي «حفظه الله ورعاه»
╰───────────────────


╭───────────────────
│  🎙የደርሱ አቅራቢ:
├─┈┈┈✑ኡስታዝ አብራር አወል አለህ ይጠብቀው
╰─────────────

╭───────────────────
│      የኣፑ አዘጋጅ_
├─┈┈ጄጄ ሰለፊይ App Developer
╰──────────
╰───────────────────

╭ለሌሎችም ሼር
├─┈┈┈✑ በማድረግ የአጅሩ
│ተካፍይ ይሁኑ!  
https://t.me/technologybyAbdu
╰──────────────

╭📨 አፖችን በትእዛዝ ለማሰራት ይህን የግለ  አድራሻችንን ይጠቀሙ
          @Abdurejj
│       @Abdurejj
╰─────

ከዚህ በፊት የተለቀቁ አፖችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀላሉ 👇👇👇👇

t.me/technologybyAbdu

t.me/technologybyAbdu

t.me/technologybyAbdu


ጫት የዱዓ መሳሪያ ሳይሆን የውድመት መሳሪያ ነው!

⚠️ ጫት ውድ የሆነውን ግዜ ይገድላል።
⚠️ ጫት ያጀዝባል።
⚠️ ጫት ያጃጅላል።
⚠️ ጫት አላማ ቢስ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ነዝናዛ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ኪስን ያከሳል።
⚠️ ጫት ወንድነትን ያከስማል ብልት ያኮላሻል።
⚠️ ጫት ቤተሰብን ይበትናል።
⚠️ ጫት ያልከሰክሳል።
⚠️ ጫት ሌባ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ወስላታ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ልብን ያደርቃል።
⚠️ ጫት የሰው እጅ ያሳያል/ለማኝ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ያደሀያል።
⚠️ ጫት ያሳብዳል።
⚠️ ጫት እንቅልፍ ይከላክላል።
⚠️ ጫት ለቢድዓ እና ሽርክ ይዳርጋል።
⚠️ ጫት ፈሪ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ጥርስን ያዳሽቃል።
⚠️ ጫት አፍን ያገማል።
⚠️ ጫት ቡቱቶ ያስለብሳል።
⚠️ ጫት ጨጓራ በሽታ ያመጣል።
⚠️ ጫት ውበት ያበላሻል።
⚠️ ጫት ያደነዝዛል።
⚠️ በዲንህ ደዩስ እንዲትሆን ያደርግሃል።

📌 በጥቅሉ ጫት ትውልድ ገዳይ አደገኛ ቅጠል ነው። ወጣቶቻችን ሆይ ንቁ ኤሄን ቅጠል እያኘካችሁ ውድ የሆነውን ግዜያችሁን አታውድሙ። ለጉዳቶቹ ሰለባ አትሁኑ።

👌 የሆነ ቦታ ዞር ዞር ስል ያገኘሁት ነው የተወሰነ ጨማምሬበት አቀረብኩላችሁ። እስቲ ለጫት ቃሚዎች ከእውቀታቸው ላይ ይጨምሩበት ላኩላቸው። እንጂማ ጉዳቱን የማያቁ ሁነው አይደለም

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


Forward from: Muhammed Mekonn
📌 إِنَّا لِلّهِ وَإِنَّـا إِلَيْهِ رَاجِعونَ  ጥንቃቄ

🔎 በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት የቴሌግራም ስሙን Allah ብሎ ለፃፈው ሰው የተወለደበት ቀን ሲደርስ It′s Allah′s  birthday today! ❨ዛሬ የአላህ ልደት ቀን ነው!❩ በሚል ወደተለያዩ ሰዎች ይላካል! ይህ ክህነት ለመሆኑ ከየትኛውም ሙስሊም አይሰወርም።

👉 የትኛውም ሙስሊም ሶላት ይሰግዳል። የሚከለክለውን ምዕራፍም በቃሉ ይሸመድዳል።

↩️ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
↪️ በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡»

↩️ اللَّهُ الصَّمَدُ
↪️ «አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡»

↩️ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
↪️ «አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡»

↩️ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ
↪️ «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡»


👌 ያልወለደ እና ያልተወለደ እንዲሁም አንድም ቢጤ የሌለው ሀያል ጌታ አላህ የልደት ቀን የለውም። ግልፅ ክህደት መሆኑ ከማንም አይሰወርም

👉 በመሆኑም እናንተ ሙስሊሞች ሆይ ተጠንቀቁ በናንተ ሰበብ ይህ ክህደት እንዲሰራጭ ሰበብ ላለመሆን የቴሌግራም ስማችሁን በአላህ ስም አትፃፉ

👉 በተለይ ሴቶች ማንነታችሁን ለመደበቅ ሲባል ስማችሁን ከመፃፍ ይልቅ ሌላ ነገር ትጠቀማላችሁ። ይህ ጥሩ ነው።
ነገር ግን በአላህ ስምና ተያያዥ በሆኑ ቃላት መፃፍ የለባችሁም። መክፈቱ አስፈላጊ ከሆነ በባላችሁ ስም ክፈቱ! አለቀ

👉 ለምታውቁት ሁሉ ሸር (Share) በማድረግ አላዋቂዎችን ከጥፋት እንከልክል! እኔ በሁሉም ግሩፕ እና ቻናሎች እንዲሁም በግል Contacts እልካለሁ እናንተም ወደ ስራ!

📝 ወንድማችሁ አቡ ዒምራን

🏝 👉 🔎 👌 ➴➴➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/10087


🚨 ሰበር የብስራት ዜና ለጉብሬና አካባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰቦች በሙሉ!

የተከበራችሁ በጉብሬ ክፍለ ከተማ እና በአካባቢው የምትገኙ ሙስሊም ማህበረሰቦች እነሆ የሰለፍዮች የአይን ማረፊያ የሆነው ውዱ መስጂዳችን አቡ ሁረይራ የፊታችን እሁድ ቀን 30/ 06/ 17 ማታ ከኢፍጣር ቡሀላ 01:40 ሰዓት ጀምሮ እስከ 03:00 ድረስ ማለትም እስከ ዒሻእ እና ተራዊህ ሶላት ድረስ የሚቆይ የሆነ በአይነቱ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ይጠብቃቹሀል።

* ተጋባዥ እንግዳ

ለእለቱ ሰርፕራይዝ ይቀመጥ

ይህን ፕሮግራም እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል። ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ ስነ-ምግባር ነው!!

* አዘጋጅ ፦ የአቡ ሁረይራ መስጂድ አስተዳደር ቦርድ አባላት

* አድራሻ፦ ጉብሬ አቡ ሁረይራ መስጂድ

t.me/gubreahlelsunajemea
t.me/gubreahlelsunajemea


📙 መንሀጅን በተመለከተ ጠንከር ያሉ ምክር አዘል ንግግሮች!

* قال ﺍﻟﻌﻼﻣﺔ ﺍﻟﻤﺤﺪِّﺙ ﻣﻘﺒﻞ ﺍﻟﻮﺍﺩﻋﻲ - ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ تعالى -

”ﻓﺎﻟﺪﻋﻮﺓ ﻋﻨﺪﻧﺎ ﺃﻋﺰ ﻣﻦ ﺃﻧﻔﺴﻨﺎ ﻭﻣﻦ ﺃﻫﻠﻴﻨﺎ  ﻭﺃﻣﻮﺍﻟﻨﺎ ﻭﻣﺴﺘﻌﺪﻭﻥ ﺃﻥ ﻧﺄﻛﻞ ﻭﻟﻮ ﺍﻟﺘﺮﺍﺏ ﻭﻻ ﻧﺨﻮﻥ ﺩﻳﻨﻨﺎ ﻭﺑﻠﺪﻧﺎ ﻭﻻ ﻧﺘﻠﻮﻥ ﺍﻟﺘﻠﻮﻥ ﻟﻴﺲ ﻣﻦ ﺷﻴﻤﺔ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺴﻨﺔ“اﻫـ .

* የየመኑ ሊቅ ሙቅቢል አል-ዋዲዒይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

«ዳዕወቱ-ሰለፊያ እኛ ዘንድ ከነፍሳችን፣ ከቤተሰቦቻችን እና ከንብረቶቻችን በላይ ናት። (ብናጣ) አፈር ለመብላት ዝግጁ ነን። ዲናችንን አንከዳም። ሀገራችንን አንከዳም። አንቀያየርም። መቀየያር ከሱና ሰዎች መገለጪያ አይደለም።»

ﺍﻟﺒﺎﻋﺚ ﻋﻠﻰ ﺷﺮﺡ ﺍﻟﺤﻮﺍﺩﺙ ص ٥٧.

* وقال العلامة ابن العطار - رحمه الله:

”لا بد من البيان وعدم الكتمان وإظهار الحق وتبيين الكذب من الصدق والله تعالى يعلم المفسد من المصلح والملبس من الموضح“ اﻫـ .

* ኢብኑል ዐጣር የተባሉት እውቁ ሊቅ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

«(ሀቅን) ግልፅ ማድረግ፤ አለ-መደበቅ ግዴታ ነው። ሀቅን ፍንትው ማድረግ እና ውሸቱን ከእውነቱ ለይቶ ግልፅ ማድረግ (ግዴታ ነው)። አላህ ደግሞ አበላሹን ከአስተካካዩ እንዲሁም የሚያለባብሰውን ከሚገልፀው ለይቶ ያውቃል።»

رسالة السماع له ص - ٤٨.


* وقال العلاّمة أحمد النجمي - رحمه الله:

”أما الذين سكتوا عن بيان الحق للناس فإنهم ﻻ يعذرون بسكوتهم ولو قالوا نحن لسنا معهم فإنهم ﻻيعذرون“ اﻫـ .

* እውቀተ-ብዙዉ አህመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

«እንዚያ ሀቅን ለሰዎች ግልፅ ከማድረግ ይልቅ ዝም ያሉትማ ዝምተኛ ናቸው በማለት አይመካኝላቸውም። እኛ (ከባጢል) ሰዎች አይደለንም! ቢሉ እንኳ አይመካኝላቸውም።»

تحذير السلفي من منهج التميع الخلفي ص - ٣١١.

* وقال شيخ الإسلام بن تيمية رحمه الله:

"وصاحب الهوى يعميه الهوى ويصمه فلا يستحضر الله ورسوله في ذلك ولا يطلبه ولا يرضى برضا الله ورسوله ولا يغضب لغضب الله ورسوله بل يرضى إذا حصل ما يرضاه بهواه ويغضب إذا حصل ما يغضب له بهواه"

* የኢስላም ባለውለታው ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላል፦

«ስሜትን የሚከተል ሰው ስሜቱ አሳውሮ ያደነቁረዋል። ስሜቱን ሲከተል አላህ እና መልእክተኛው በልቡ አይሰየሙም (አይፈራም)። መፍራትም አይፈልግም። የአላህ እና የመልእከተኛው ውዴታም አያስደስተውም። የአላህ እና የመልእክተኛው መቆጣት አያስቆጣውም። እንደውም እሱ የሚወደው ነገር ሲገኝ ለስሜቱ ሲል ይደሰታል። እሱን የሚያስቆጣው ነገር ሲገኝ ለስሜቱ ሲል ይናደዳል።»

منهاج السنة له ٢٥٦/٥.

* قال الحافظ ابن القَيِّم - رحمه الله:

 ”ﻭﻣﻌﻠﻮﻡ ﺃﻧﻪ ﺇﺫﺍ ﺍﺯﺩﻭﺝ ﺍﻟﺘﻜﻠﻢ ﺑﺎﻟﺒﺎﻃﻞ ﻭﺍﻟﺴﻜﻮﺕ ﻋﻦ ﺑﻴﺎﻥ ﺍﻟﺤﻖ ﺗﻮﻟﺪ ﺑﻴﻨﻬﻤﺎ ﺟﻬﻞ ﺍﻟﺤﻖ ﻭﺇﺿﻼﻝ ﺍﻟﺨﻠﻖ“ اﻫـ .

* የሳቸው ኮከብ ተማሪ የሆኑት ኢብኑል ቀዪም (ረሒመሁላህ) ደግሞ እንዲህ ይላሉ፦

«እንደሚታወቀው ባጢልን ከማስተማር እና ሀቅን ግልፅ ከማድረግ ዝም ማለት የተቆራኙ ግዜ በመካከላቸው የሀቅ አለ-መታወቅ እና ፍጥረትን ማጥመም ይፈጠራል።»

الصواعق المرسلة ص - ٥٢.

* وقال العلاّمة ابن عثيمين - رحمه الله:

”ﺇﻥ ﻛﻨﺖ ﻭﺣﻴﺪﺍ ﻓﻲ ﺑﻠﺪﻙ ﺗﺪﻋﻮﺍ إلى ﺍﻟﺴﻨﺔ ﻭﺍﺗﺒﺎﻉ ﺍﻟﺴﻠﻒ ﻭﻛﺜﺮ ﺍﻷﻋﺪﺍﺀ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﻳﺪﻋﻮﻥ ﺇﻟﻰ ﻣﺬﻫﺒﻬﻢ ﺍﻟﺒﺎﻃﻞ ﻓﺎﻟﻮﺍﺟﺐ ﺃﻻ ﺗﻨﻬﺰﻡ لأﻧﻚ ﺇﺫﺍ ﺍﻧﻬﺰﻣﺖ ﻓﻘﺪ ﻫﺰﻣﺖ ﺍﻟﺤﻖ ﺑﻞ ﺍﺛﺒﺖ ﻭﻣﺎ ﺃﺭﻋﺐ أﻋﺪﺍﺀﻙ ﺇﺫﺍ ﺭﺃﻭﻙ ﺛﺎﺑﺘﺎ“ اﻫـ .

* የዘመኑ ሊቅ የነበሩት ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

«ሀገርህ ውስጥ ቀደምቶችን ወደ-መከተል እና ወደ-ሰለፍያ የምትጣራ ብቸኛ (ዳዒ) ከሆንክ እና ወደ-ጥመታቸው የሚጣሩ ጠላቶችህ ከበዙ ባንተ ላይ ግዴታው አለ-መሸነፍ ነው። ምክንያቱም አንተ እጅ ከሰጠህ (ባንተ ሲመራ የነበረው) ሀቅ ይወድቃል። እንግዲያውስ ፅና። ጠላቶችህ ፀንተህ ሲያዩህ ለነሱ ምንኛ አስፈሪ ነው?! (ፍርሀት ይወድቅባቸዋል።)»

ﺷﺮﺡ ﺍﻟﻜﺎﻓﻴﺔ ﺍﻟﺸﺎﻓﻴﺔ ٢٠١/١.


t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


🚨 ሰበር የብስራት ዜና ለጉብሬና አካባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰቦች በሙሉ!

የተከበራችሁ በጉብሬ ክፍለ ከተማ እና በአካባቢው የምትገኙ ሙስሊም ማህበረሰቦች እነሆ የሰለፍዮች የአይን ማረፊያ የሆነው ውዱ መስጂዳችን አቡ ሁረይራ የፊታችን እሁድ ቀን 30/ 06/ 17 ማታ ከኢፍጣር ቡሀላ 01:40 ሰዓት ጀምሮ እስከ 03:00 ድረስ ማለትም እስከ ዒሻእ እና ተራዊህ ሶላት ድረስ የሚቆይ የሆነ በአይነቱ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ይጠብቃቹሀል።

* ተጋባዥ እንግዳ

ለእለቱ ሰርፕራይዝ ይቀመጥ

ይህን ፕሮግራም እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል። ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ ስነ-ምግባር ነው!!

* አዘጋጅ ፦ የአቡ ሁረይራ መስጂድ አስተዳደር ቦርድ አባላት

* አድራሻ፦ ጉብሬ አቡ ሁረይራ መስጂድ

t.me/gubreahlelsunajemea
t.me/gubreahlelsunajemea


🚨 ሰበር የብስራት ዜና ለጉብሬና አካባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰቦች በሙሉ!

የተከበራችሁ በጉብሬ ክፍለ ከተማ እና በአካባቢው የምትገኙ ሙስሊም ማህበረሰቦች እነሆ የሰለፍዮች የአይን ማረፊያ የሆነው ውዱ መስጂዳችን አቡ ሁረይራ የፊታችን እሁድ ቀን 30/ 06/ 17 ማታ ከኢፍጣር ቡሀላ 01:40 ሰዓት ጀምሮ እስከ 03:00 ድረስ ማለትም እስከ ዒሻእ እና ተራዊህ ሶላት ድረስ የሚቆይ የሆነ በአይነቱ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ይጠብቃቹሀል።

* ተጋባዥ እንግዳ

ለእለቱ ሰርፕራይዝ ይቀመጥ

ይህን ፕሮግራም እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል። ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ ስነ-ምግባር ነው!!

* አዘጋጅ ፦ የአቡ ሁረይራ መስጂድ አስተዳደር ቦርድ አባላት

* አድራሻ፦ ጉብሬ አቡ ሁረይራ መስጂድ

t.me/gubreahlelsunajemea
t.me/gubreahlelsunajemea


Forward from: ሙሀመድ አል―ወልቂጢይ
🚨 ቁርአን ለመማር እና ለመሀፈዝ የሚጠቅሙን ነጥቦች!

1, አጅሩን ማሰብ በደንብ ለማወቅ መጣር። መንተባተብም ይሁን በደንብ አውቆ መቅራትም አጅር አለው

2, ተገቢውን ልፋት መልፋት አለመሰላቸት፣ ለመማር ሲነሳ  አለማፈር እና አለመኩራት። አሊይ (ረዲየላሁ አንሁ)  እንዲህ አሉ «አንድ ሃርፍ ላስተማረ ባርያ ልሁንለት» ሙጃሂድ (ረሂመሁላህ) የተሰኙ አሊም እንዲህ አሉ «ሀያእ ያለበት እና ኩራት ያለበት እውቀት አይማርም።» አላህ ዐዘ ወጀል እንዲህ ብሏል፦

"وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِيْنَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا"

"እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን።"

3, በደረሰበት መጥፎ ነገር መታገስ። መታገስ ማለት የደረሰብህን ችግር እያሳነስክ ማለፍ ነው።

4, ጓደኛ መምረጥ። ጓደኛህን ንገረኝ እና ማንነትህን ነግርሀለው የሚለው አባባል ትክክል ለመሆኑ ሁለት ሰዎች አይጣሉበትም። ጓደኝነት ፎቶ ኮፒ ነው ስለዚህ ለትልቅ አላማ የሚበጅ ጓደኛ ማፍራት ብልህነት ነው።

5, ግዜ አላማባከን በተለይ የልጅ ነት የወጣትነት ጊዜ ሳይባክን መጠቀም።

6, ደጋግሞ መቅራት ቁርአን ካልተደጋገመ ይረሳል። ኡለማኦች ቶሎ የመረሳቱን ሂክማ ሲገልፁ ደጋግመህ ቀርተህ አጅር እንድታገኝ አላህ እንዲረሳ አደረገው ብለዋል። በርካታ ሰለፎች ከሌላ ሀጃዎቻቸው ግዜን በመቀነስ ቁርአንን ይቀሩ ነበር።

ቁርአንንም ሆነ ሌላን የኢልም ዘርፍ ነካክቶ አለማለፍ ኢልምን መጨረስ ባይቻልም እንኳን ቀማምሶ ማለፍ ግን አለምን ያበላሻል።

https://t.me/sunnatewhid
https://t.me/sunnatewhid


منكرات_إفطار_الشوارع_لللأستاز_أبو_عبدالله_عز_الدين.pdf
911.5Kb
أخيرا12345.pdf
2.4Mb
👉 አዲስ pdf   

عنوان:- الرد الشرعي في منكرات إفطار الشوارع

ርእስ፦ «በጎዳና ላይ ኢፍጣር ጥፋቶች ላይ ሸሪዓዊ መልስ»

للأستاذ الفاضل أبي عبد الله عز الدين بن سراج بن إبراهيم السلطي حفظه الله

✍🏻አዘጋጅ:- ኡስታዝ ዒዙዲን ስራጅ ኢብራሒም አስ’ሲልጢይ አልጫንጪይ (ሀፊዘሁላህ)

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት፣ የምታቀሩም አቅሩት)

#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


ውድ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን አመሻችሁ?!

በአንድ ድንጋይ ሁለት ወይፍ አለ የሀገሬ ሰው እስቲ አስቡት የ 200 ብር ቻሌንጅ (ድጋፍ) በመሳተፋችን በዱንያ መስጂዳችንን በአኼራ ደግሞ የጀነት ውስጥ ቤታችንን መገንባት ትልቅ አድል አይደለም?

አሁንም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ሶደቃ በዱንያ አላህ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይመልስልናል። በአኼራም ሀሰናቱ በ700 እና ከዛ በላይ የተባዛ ነው።

ደግሞ መድረኩ የሶቀቱል ጃሪያ ነው በመስጂዱ ውስጥ በሚሰሩ ኸይር ስራዎች ሁሉ በቀጣይነት የምንመነዳ ይሆናል።

ስለዚህ አይተህ አትለፍ
ባቅምህ በቻልከው ተሳተፍ
ሀሰናትን አከማች አድርገው ከፍ ከፍ

የባንክ ሂሳብ ቁጥር
ንግድ ባንክ 1000619092175
አቢሲኒያ 192421349
ሙሀመድ፣ አብዱልሀሚድና ኢብራሂም




Forward from: Bahiru Teka
👉 በረመዳን ከኛ ምን ይፈለጋል ?

በረመዳን ከኛ ምን እንደሚፈለግ ለማወቅ ረመዳን ለምን እንደ ተደነገገ ማወቅ ያስፈልጋል ። ረመዳን ከኛ በፊትም በነበሩት ህዝቦችና በኛ ላይም የተደነገገው አላህን እንድንጠነቀቀው ( እንድንፈራው ) ነው ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል : –

« يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ »

البقرة ( 183)

" እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና " ፡፡

ይህን አንቀፅ መሰረት በማድረግ ዑለሞች ከፆም የሚፈለገው ዋነኛው ግብ ራስን ከስሜትና ከልማድ ነፃ ማውጣት ነው ይላሉ ። ይህ በጣም ሰፊ ትንታኔ የሚፈልግ አባባል ነው ። ለጥያቄያችንም መልስ ይሰጣል ።
ሁላችንም እስኪ ፍላጎታችንንና ልማዳችንን እንዲሁም በዙሪያችን ያሉ ሰዎችንም ፍላጎትና ልማድን እንመልከት ። የአውሮፓ ሊግ ብሎ ከቴሌ ሺዥን ስር ማፍጠጥ ፣ የሀገር ውስጥ ክለቦች ውድድሮች ለማየት እስታዲየም ማዘውተር ፣ አብዛኛውን ጊዜ ሞባይል ይዞ ጊዜ ማጥፋት ፣ የተለያዩ ፊልሞችና ድራማዎችን መመልከት ፣ በየሱቅ ደጃፍ ተሰባስቦ ወሬ ማውራት ፣ የተሻለ ነው የሚባለው መንዙማ መስማት ፣ ማታውን በጫትና መንዙማ ማሳለፍ ፣ ቀን አብዛኛውን ሳአት ተኝቶ ማሳለፍና የመሳሰሉት ይገኙበታል ።
እነዚህ ልማዶች ፆም ላይ ከቀጠሉ ከፆማችን የምናተርፈው ረሀብና ጥም ነው የሚሆነው ። ልክ እንደዚሁ ፍላጎታችንን መተው ይናርብናል ። የስሜታችን ታዛዥ ከሆንን ፆም የተደነገገበት አላማ አልገባንም ማለት ነው ። በመሆኑም በረመዳን ከኛ የሚፈለገው ከልማዳችንና ፍላጎታችን ተቆጥበን ቀኑን በፆም ለሊቱን በተለያዩ ዒባዳዎች እንድናሳልፍ ነው ።
ጫት መቃም ዒባዳ ሳይሆን እዳ ነው ። ጫት መቃምን ዒባዳ የሚሉ በተለይ የገጠሩ ቤተሰቦቻችን ከዚ ልማዳቸው እንዲላቀቁ መምከር ይኖርብናል ።
አላህ ካገራላቸው ባሮቹ ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka


🔸ረመዷንን በተመለከተ
👆👆👆

🔈
#የነብዩ ﷺ መመሪያ በረመዷን ውስጥ ከክፍል 1_ 3
 
🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

🌐
https://t.me/shakirsultan

20 last posts shown.