ኸጥ አል ሙስነድ
(በድጋሚ የቀረበ)
ከ3000 አመታት በፊት ጥንታውያን የየመን ሰበኢዮች (ሳባውያን) ፣ሒምየሮችና ከህላን ይጠቀሙበት የነበረው ፊደል ቅርፅ ከአማረኛ ጋር እጅግ ይመሳሰላል። እጅግ ጥቂት መለያየት ያለባቸው ፊደሎች ከመኖራቸው ጋር፣ አብዛኛዎቹ ወይ እንዳሉ አማረኛውን ሲመስሉ፣ ካልሆነ ደግሞ ተገልብጠው ወይ ተንጋደው ነገር ግን ከአማረኛ ጋር የሚያመሳስላቸውን ይዞታ ሳይለቁ አሉ። እርግጥ ነው ስነ ፅሁፋቸው እንደ ዓረብኛ ከቀኝ ወደ ግራ ከመሆኑ ጋር። አማረኛም በመሰረቱ ከቀኝ ወደ ግራ እንደነበረና ከግዜ ቡኃላ እንደተቀየረ የቋንቋ ሊቆች ያወራሉ። አማረኛ ማንበብ የሚችል ሰው አንዴ የሳባእ ፊደላትን ካስተዋለ በኋላ ማንበብ ለመጀመር ብዙ ጥናት አይፈልግም።
ለምሰሰሌ المسند ወይም ሙስነድ ብለው ለመፃፍ (ለማንበብ ከቀኝ ወደ ግራ መሆኑን አትርሱ)
( 𐩣𐩪𐩬𐩵 )
መ እና ደ ተገልብጠዋል የቅርፅ ለውጥም ይታያል። ሌሎች ግን እንዳሉ ናቸው።
ሌላ መለያው ቃላቱ ሁሉ "በግእዝ ቤት" (የመጀመሪያ ፊደል) ብቻ ነው የሚፃፈው። ለምሳሌ "የውሀ ወረቀት ነው" ብሎ ለመፃፍ (የወሀ ወረቀተ ነወ) ተብሎ በዚህ መልኩ👇👇 (ከቀኝ ወደ ግራ) ይፃፋል
𐩺𐩥𐩠 𐩥𐩧𐩤𐩩 𐩬𐩥
ሱብሀነላህ!!
ሰበኢያዎች ምንም እንኳ ቋንቋቸው አማረኛ ወይም ግእዝኛ ያልነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሁሉም የሴም ቋንቋዎች (ሴማቲክ) መሆናቸው ምን ያህል እንደሚያቀራርባቸው ተመልከቱ!!!
የቤት ስራ
የሚከተለውን ዐ.ነ አንብቡና ኮሜንት ላይ ፃፉ
(እንዳትረሱ ከቀኝ ወደ ግራ ነው ሚነበበው)
𐩱𐩨𐩨 𐩨𐩪 𐩨𐩡☀️ሁዳ መልቲሚዲያ
t.me/huda4eth