እናስተነትን ዘንድ
ክፍል ሁለት
እነሆ ትላንት እንቅልፍ እንዳልተኛ በ ጩኸታቸው እና በንክሻቸው አላስተኛ ያሉኝ ትንኞች ነበሩ። እስኪ ስለ ቢምቢዎች ልንገራችሁ።
ቢምቢ ከ 3000 በላይ ዝርያወች ያሏት ትንኝ ናት። ከነዚህ ውስጥ ትንሾቹ ብቻ ናቸው ከ ሰው ልጅ ደም እሚመጡት። ግን ለምንድን ነው እሚመጡት?!
ደም መጣጭ የሆኑት ቢንቢወች ሴቶች ብቻ ናቸው። ወንድ ቢምቢዎች ምግባቸውን ከአበባ ብቻ ነው እሚፈልጉት። ታድያ ሴቷ ደም ምን ይሰራላታል?!ካላችሁኝ ለ እንቁላሏ እድገት ስትል ነው።
ምን አለ መሰላችሁ የ ሰው ልጅ ደም በ ፕሮቲን እና አሚኖ አሲድ የበለፀገ ስለሆነ ለእንቁላሎቻቸው እድገት ያስፈልጋቸዋል። ለዚያም ሲሉ ሴት ቢምቢወች ደም ይመጣሉ። በነገራችን ካይ ቢምቢወች ከ 1.6 - 2.3 ኪሎ ሜትር በሰአት መብረር ይችላሉ።
ታድያ ከነዚህ ውስጥ anopheles የተባሉት የቢምቢ ዝርያወች ናቸው ወባን እሚያስተላልፉት። ግን ቢምቢወች ሲነክሱን ቆዳችን ላይ እብጠት ይከሰታል ለምንድን ነው?!
መልሱ ቢምቢወች ከሰው ልጅ ደም ለመምጠጥ ቆዳችን እንደበሱ ምራቅ ነገራቸውን ወደ ውስጥ ይለቁታል! በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ሰውነት ወደ ውስጥ ለገባው ምራቅ ነገር ምላሽ ይሰጣል በዚህ ጊዜ እብጠት ነገር ይከሰታል።ቢምቢወች ድምፅ እሚፈጥሩት በ ክንፋቸው ውልብልብታ ነው።
እነዚህ ቢምቢወች መብራት ጠፍቶ እንኳን ሊያገኙህ ይችላሉ። ምክኒያቱ ደግሞ ቢምቢዎች ለ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ (CO2)፣ ለሙቀትና ለጥቁር ቀለም ልብሶች የተሳቡ መሆናቸው ነው።
እንደ healthline ገለፃ ከሆነ ቢምቢወች O blood group (የደም አይነት) ያላቸውን ሰወች ነው በደምብ እሚመገቡት። ደማችሁን እየመጠጡ ዝም ብላችሁ ብትከታተሏቸው እስከ አራት ደቂቃ ሊቆዩ ይችላሉ።
እንደ national institute of health ገለፃ ከሆነ የቢምቢ ትንኞች ከመጠን በላይ ጨውና ፈሳሽ ነገሮችን እሚያስወግድ #ኩላሊቶች አላቸው። ይህንን ቆሻሻም በሽንት መልክ ያስወግዱታል።
ወንዱ ቢምቢ ከ ሴቷ ጋር ግንኙነት ካደረጉ በኋላ በሂወት የመኖር እድል የለውም። ሴቷ ግን ብዙ ጊዜ ልታደርግ ትችላለች በሁሉም የግንኙነት ጊዜ የዘር ፈሳሹን ታጠራቅምና አንዴ ትጠቀምበታለች። ወንዶች ለጉልምስና ጊዜ በኋላ በዛ ቢባል አንድ ወይም ሁለት ሳምንት ይኖራል ሴቷ ግን እስከ መቶ ቀን መኖር ትችላለች።
ለዛሬ ይህን ይመስላል ሌላ ጊዜ በሌላ ነገር እንገናኛለን
@ibnuhasen