︎ ከምር ሳያነበው ያለፈ ይቆጭበታል
አልወዳትም ግን አገባኋትያገባኋት እህቷ ናት ብዬ ስላሰብኩ ነው። ሁለቱም ኒቃብ ለባሽ ናቸው። እሷን ለማግባት ከመወሰኔ በፊት የታላቃ እህቷን ስም አለመጠየቄ ስህተት ነበር።
ስህተቴን ያወቅኩት ከተጋባን በኋላ ነው
በጣም ከመፀፀቴ የተነሳ አጠገቧ አልተኛም ፣ ግንባሯን ስሜያት አላውቅም ፣ አፈቅርሻለሁ ብያትም አላውቅም።
ሁሌም እንደማልወዳት እንዲሰማት አደርጋለሁ ትዳራችንን ለማፍረስ ፍላጎት እንዲኖራት በማሰብ ፤ ሰላት እንድትሰግድ አልቀሰቅሳትም ፤ ይልቁንም እሷ ሁል ጊዜ ትቀሰቅሰኛለች። እኔ ግን ኢማሟ ለመሆን ፊቷ አልቆምም።
እሷ ግን...
እንደ ሚስቴ ሁሉንም ነገር ለማድረግ ትሞክራለች ፣ ከሚገባኝ በላይ ትንከባከበኛለች።
ውስጧ እንደተጎዳ ባውቅም ፈገግታዋ ሁሌ አለ።
ጧት ፣ ከሰአት በኋላ እና ልንተኛ ስንል "እወድሀለሁ" ትለኛለች ፣ ከርቀት አብራኝ ሰላቷን ትሰግዳለች።
እስከ አንድ ቀን ድረስ.. የምወደውን ቲሸርት እንዳጋጣሚ ስታበላሽብኝ ጮህኩባት። ከማቀርቀንና ከማልቀስ ውጪ ምንም አላለችኝም። የሆመ ድምፅ ሰማሁ እና ወደሷ ስዞር ራሷን ስታለች እግሬን ማንቀሳቀስ አቃተኝ በጣም ፈራሁ ሳላውቀው እንባዬ ወረደ ፣ ልቤ በፍጥነት ይመታል ፣ መተንፈስ ሁሉ በጣም ከባድ ሆነብኝ
ሱብሀነላህ!
ወደሷ ሮጥኩ ለመቀስቀስ ስሟንብዙ ጊዜ ልጠራት ሞከርኩ ግን አይኖቿን አልከፈተችም። ለጎረቤቶቻችን እርዳታ ጮህኩ እናም ሆስፒታል ስንደርስ እና ዶክተሩ የተናገረውን ስሰማ ባዶ እንደሆንኩ ተሰማኝ " ይህ እውነት አይደለም።" ለራሴ ደጋግመዋለሁ
"በመጨረሻ ደረጃ ላይ ትገኛለች" አለ ዶክተሩ
"የመጨረሻው ደረጃ?" ዶክተሩን ጠየቅኩት
"ካንሰር አለባት እኛን ከጎበኘችበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እየተከታተልናት ነው አሁን ግን የምታሸንፈው አይመስልም።" አለ
"እንዴት ሆነ?!! ውሸት መሆን አለበት!!" አልኩ በቁጣ
"ባሏ መሆን አለብህ ፤ በአንተ ምክንያት መዳን እንደምትፈልግ ፣ ካንተ ጋር መኖር እንደምትፈልግ ፣ አንተን እንድትንከባከብ ፣ የበለጠ ለመኖር የምትፈልግበት ምክንያት አንተ ብቻ እንደሆንክ ነግራናለች። ስትሰቃይ ኖራለች ፣ ከእንግዲህ ወዲህ ማድረግ የምንችለው ዱአ ብቻ ነው ፣ እነዚያን የማይቻሉ ነገሮች እንዲፈፀሙ ማድረግ የሚችለው አላህ ብቻ ነው ፣ አንተ ብቻ እምነት ይኑርህ" አለኝና ትከሻዬን መታ መታ አድርጎ ሄደ።
ሀኪሙ የተናገረውን እያስታወስኩኝ ..
እኔ በጣም መጥፎ ባል ነኝ!! ጭራቅ ነኝ! እየተሰቃየች መሆኗን ሳላውቅ እንዴት እንዲህ አደርጋታለሁ?!! እንዴት?!!
በሆስፒታሉ አልጋ ላይ ተኝታ ስመለከት አንድ ነገር እንድገነዘብ አደረገኝ።
እንደምወዳት ተረዳሁ ፤ በእውነትም እወዳታለሁ። ግን ባለማስተዋል ማየት ተሳነኝ! በሷ ላይ የሚሰማኝን ስሜቴን ደበቅኩኝ ፣ ቀደር አሁንም እንዳለ ረሳሁ ፣ እሷን ማግባት ስህተት ሳይሆን ቀደር መሆኑን ዘነጋሁ ፣ ሁሉም ነገር የሆነው ለበጎ ነውና ረስቼው ነበር ፣ የአላህ እቅድ ከፈለግኩት የተሻለ መሆኑን ረሳሁ።
አሁን በጣም ተፀፅቻለሁ።!!
አይኖቿን ከፈተች ዙርያዋን ተመለከተችና ዓይኖቻችን ሲገናኙ የእውነት ፈገግ አለች። "ይቅርታ" አለች በለሆሳስ እንደገና እንባዎቼ ወረዱ አጥብቄ አቀፍኳት
"እኔ ነኝ ማለት ያለብኝ ፣ ይቅርታ !! ለሁሉም ነገር ይቅርታ እባክሽ አትተይኝ ፣ እኔ እወድሻለሁ እባክሽ።" በጣሜ አለቀስኩ
"እንዲህ አትበል ፣ አልተውህም... ስለታመምኩ ብቻ አትዋሸኝ ፣ እህቴን በጣም እንደምትወዳት አውቃለሁ" አለችኝ።
ተመለከትኳት እንዴት አወቀች? ግን በፊት ነበር። ሁሉም ነገር ተለውጧል ግን አላስተዋልኩትም ነበር
"ሃሃ ግልፅ ነው ባሌ እንደዚ ስላየኸኝ እንደምትወደኝ አትንገረኝ ቀደሬ ስለሆነ አትዘንልኝ ለረጅም ግዜ ልንከባከብህ ፈልጌ ነበር ግን ከዚ በላይ የምችል አይመስለኝም እስክናረጅ ድረስ ሁል ጊዜ እወድሃለሁ ማለት ፈልጌ ነበር ግን ከአሁን ቡሀላ ማድረግ አልችልም አንተን በማግባቴ በጣም እድለኛ ሴት እንደሆንኩ እንደሚሰማኝ እንዲሰማህ እፈልግ ነበር ሁሌ አላህን ፈጅር ልቀሰቅስህ ባልችል እንኳን አዛን ወደ ነፍስህ ውስጥ ደርሶ እንዲቀሰቅስህ ዱአ አደርጋለሁ" አለችኝ አሁንም ፈገግ ብላ
"አይ እኔን መተው አትችይም እባክሽን" ስል ለመንኳት ፈገግ ብላ ግንባሬን ሳመችኝ "በነቃህበት ግንባርህን ስስምህ የመጀመሪያዬ ነው በምትተኛበት ጊዜ ግን ግንባርህን ሁሌ እስምሀለሁ... አንድ ውለታ ልጠይቅህ እችላለሁ? አለች
"ሰላታችንን አብረን እንስገድ ለመጨረሻ ጊዜ ኢማሜ ሁን" አለችኝ ፈገግ ብላ እንባዬን መግታት አልቻልኩም ላቆመው አልቻልኩም የመغሪብ ሰአት ስለደረሰ አብረን ልንሰግድ ተነሳን.. ኢማም ሆኜ ሰላቴን በመስገድ ላይ እያለሁ እንባዬ እየወረደ ነው
"አሰላሙአለይኩም" ብዬ ዞር ስል ከሱጁድ ላይ አልተነሳችም...አትንቀሳቀስም ወደሷ መሮጥ ፈልጌ ነበር ግን ዱአዬን ቀጠልኩ አላህን ጀነት እንዲያስገባት ለመንኩት እንደሄደች አውቃለሁ ግን ለሷ ያለኝ ፍቅር ለዘላለም ይኖራል
ከህይወት ጋር ሞትም አለ ለሞት ምንም የእድሜ ገደብ የለውም። ጊዜህ ከሆነ ያለምንም ህመም ልትሞት ትችላለህ ሳታረጅም ልትሞት ትችላለህ ዝግጁ ባልሆንክበት ጊዜ ልትሞት ትችላለህ ለምትወዱት ሰው ስትሉ መቆየት ፈልጋቹ አላህ ካልፈቀደው ትሞታላችሁ ሁሉም ነገር የሚሆነው በምክንያት ነው ነገር ግን እነዚህ ምክንያቶች አንድን ነገር እንድትማሩ ሰበብ ናቸው
አንድ ሰው እስከወደደህ ድረስ ምላሽህ ጥሩ ይሁን አመስጋኝ ሁን እና ተመሳሳይ ስሜት እንዲሰማቸው አድርግ ምክንያቱም በእውነቱ ማንም ሰው እዚህ አለም ላይ ለዘላለም አይቆይም። ሁሉም ነገር አላፊ ነው።
@Islamisthis@Islamisthis