#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
== የብብት ስር ህይወት ==
( ©በሲራክ )
ማነው ፈራጅ አልቦ ጉማ ክፈል ያለኝ
ምንኛ ዳና ነው በቃል የለገተኝ
ቃሉ ህላዌ ነው ምስጢሩን የፈታ
ምስሉ የጀግና ነው ውብ ምድሩን የረታ
.
ይህ ቃል የተባለው
ምስል የታበተው
በመቻል ጎዳና ድልድይ አሻጋሪ
በመግዘፍ ሆክማ ላይ የፋናው ተመሪ
ይህ ቃል የተባለው....
በህላዌ ተስፋ ለሀገር የተሰጠው
እንደዋርካ ቆሞ ስሩ ቢበዛ ነው
.
ምስልም ሚባለው
የጥላሸት ዳና
በጠማሞች ቁና
ተሰፍሮ ያልሞላው
በቀቢፀ ተስፋ ሀገር የበደለው
እምቧጮውን ዋርካ ብለው ቢጠሩት ነው
አረሙን ከሰብል እኩል ሲተክሉት ነው
.
ስለዚህ እንደእኔ
ስለዚህ እንደእኔ
ሀገር እንደ ሕፃን ድኻ የምትቆመው
ፍትህ አደናቅፏት ዛፍ ስር ስትወድቅ ነው
ዛፍ ማለት ህይወት ነው በሲራኮች ቋንቋ
ታዲያ ለዚህች ሀገር የዛፍ ኑረት ብርቋ
.
ታዲያ በዚህች ሀገር
በውዳቂ ልሳን
በሰነፎች ተረት
በሞኝ ወኔ ሽረት
ተጋግሞ ግሞ
ተፋፍሞ ፍሞ
በሀሳብ ተፋጭቶ
ስድብ ቃል ተራጭቶ
ሀገር እየናዱ መሰልጠን ብቻ ነው
ይህ ነው አሀዳችን ይህ ነው ልንገስ ያለው
.
ጥንትም ሚባለው ግን
ለተረዳው ቋንቋ የልቡን ለሚያናኝ
ላልገባው ግን ቋጥኝ
አጀብ ጉድ የሚያሰኝ
ይሄ ማወራለት ፍትህ የተባለው
በጫማችን ገመድ ሀገር የጠለፈው
ሌላ ምንም የለም አሳሪ ቢያጣ ነው
.
በእድገት ጎዳና ጡብ ሆኖ ለድልድይ
ከሆክማው ያራቀኝ የዋርካዬ ሰማይ
ሄራን እኔነቴ አናንያው ጉርሴ
አድፎ የነተበው ዘመኔ ነው ልብሴ
.
ስለዚህ እንደሀገር
ስለዚህ እንደሀገር
እኔ እንደህፃን ድኼ የምቆመው
ፍትህ አደናቅፎኝ ዛፍ ስር ስወድቅ ነው
ለምን ?
እኔ እንጃ ?
-------------- ©ሲራክ ---------------
ጥቅምት ፪፼፲፪ ዓ.ም
@siraaq
@kinchebchabi @kinchebchabi
== የብብት ስር ህይወት ==
( ©በሲራክ )
ማነው ፈራጅ አልቦ ጉማ ክፈል ያለኝ
ምንኛ ዳና ነው በቃል የለገተኝ
ቃሉ ህላዌ ነው ምስጢሩን የፈታ
ምስሉ የጀግና ነው ውብ ምድሩን የረታ
.
ይህ ቃል የተባለው
ምስል የታበተው
በመቻል ጎዳና ድልድይ አሻጋሪ
በመግዘፍ ሆክማ ላይ የፋናው ተመሪ
ይህ ቃል የተባለው....
በህላዌ ተስፋ ለሀገር የተሰጠው
እንደዋርካ ቆሞ ስሩ ቢበዛ ነው
.
ምስልም ሚባለው
የጥላሸት ዳና
በጠማሞች ቁና
ተሰፍሮ ያልሞላው
በቀቢፀ ተስፋ ሀገር የበደለው
እምቧጮውን ዋርካ ብለው ቢጠሩት ነው
አረሙን ከሰብል እኩል ሲተክሉት ነው
.
ስለዚህ እንደእኔ
ስለዚህ እንደእኔ
ሀገር እንደ ሕፃን ድኻ የምትቆመው
ፍትህ አደናቅፏት ዛፍ ስር ስትወድቅ ነው
ዛፍ ማለት ህይወት ነው በሲራኮች ቋንቋ
ታዲያ ለዚህች ሀገር የዛፍ ኑረት ብርቋ
.
ታዲያ በዚህች ሀገር
በውዳቂ ልሳን
በሰነፎች ተረት
በሞኝ ወኔ ሽረት
ተጋግሞ ግሞ
ተፋፍሞ ፍሞ
በሀሳብ ተፋጭቶ
ስድብ ቃል ተራጭቶ
ሀገር እየናዱ መሰልጠን ብቻ ነው
ይህ ነው አሀዳችን ይህ ነው ልንገስ ያለው
.
ጥንትም ሚባለው ግን
ለተረዳው ቋንቋ የልቡን ለሚያናኝ
ላልገባው ግን ቋጥኝ
አጀብ ጉድ የሚያሰኝ
ይሄ ማወራለት ፍትህ የተባለው
በጫማችን ገመድ ሀገር የጠለፈው
ሌላ ምንም የለም አሳሪ ቢያጣ ነው
.
በእድገት ጎዳና ጡብ ሆኖ ለድልድይ
ከሆክማው ያራቀኝ የዋርካዬ ሰማይ
ሄራን እኔነቴ አናንያው ጉርሴ
አድፎ የነተበው ዘመኔ ነው ልብሴ
.
ስለዚህ እንደሀገር
ስለዚህ እንደሀገር
እኔ እንደህፃን ድኼ የምቆመው
ፍትህ አደናቅፎኝ ዛፍ ስር ስወድቅ ነው
ለምን ?
እኔ እንጃ ?
-------------- ©ሲራክ ---------------
ጥቅምት ፪፼፲፪ ዓ.ም
@siraaq
@kinchebchabi @kinchebchabi