#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
#ትንሽ_ስለ..!ክፍል - ፫
.
.
.
የህይወት መንገዷ ሰፊ ነው፤ ገደሏ ጥልቅ ነው፤ ወንዞቿ ለሁሉም እኩል አይፈሱም፤ ተራራዎቿ ሁሉን አይማርኩም!! አየህ ላንተ የተፈጥሮ ድንቅ ውበት ያልከው ተራራ የሌላ ሰው አድካሚ መመላለሻ መንገድ ነው!!
እሩቅ ሳንሄድ እዚሁ ከሰፈራችን እንኳ ባለፈው ጫማ እያስጠረኩ ሰማዩ ማንጎዳጎድ ጀመረ ከዚያም "እሰይ ተመስገን ዝናብ ሊዘንብ ነው በቃ ወደ ቤት ሄጄ ወይ መጽሐፍ አነባለሁ ወይ ጥሩ እንቅልፍ እተኛለሁ!" አልኩ። ይሄኔ ታዲያ ጫማዬን የሚያፀዳው ፈላ ፊቱን ኩስኩስ አድርጎ "እኔ ግን እንዳይዘንብ እማፀናለሁ ምክንያቱም ከዘነበ የኔና የወንድሜን ምሳና እራት ይቀማናል!" አለኝ።
እኔም በመገረም 'እንዴት?' አልኩት..
እርሱም.."ትናንት ሲዘንብ ውሎ ለቁርስና ምሳ ምንም ስላልሰራን ፆማችን ነው የዋለን!! አሁን እሚዘንብ ከሆነ ደግሞ በዝናቡ መስራት ስለማንችል ምሳና እራታችንን ይቀማናል!" አለኝ።
በህይወቴ እንደዚያን ቀን አፍሬ አላውቅም!!
.
.
(ከ
#ትንሽ_ስለ..! ተከታታይ ልቦለድ የተቀነጨበ)
👇👇👇👇👇👇👇
t.me/YelbeDrset 👆👆👆👆👆👆👆
ቤተሰብ ይሁኑ!