የግቢ ጉባኤያት ተቋማዊ ለውጥ ብቁ ዜጎችን በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ።
ጥር ፴/፳፻፲፯ ዓ.ም
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን በግቢ ጉባኤያት ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት ለቤተ ክርስቲያን ብሎም ለሀገር የሚጠቅሙ ዜጎችን ለማፍራት ማኀበረ ቅዱሳን ሥራዎችን እየሰራ ሲሆን አሁን ላይ ተቋማዊ ለውጥ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በማኀበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲያቆን ጌትነት መሠረት እንደገለጹት ተቋማዊ ለውጡ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ግቢ ጉባኤያቱ ከደረሱበት አሁናዊ ሁኔታና ከዓለም ዓቀፍ ሁነቶች አንጻር አገልግሎታቸውን በምን መልኩ መፈጸም እንደሚገባቸው ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች ሙሉ ስብዕናቸውን የሚገነባ ትምህርቶችን በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊያን እንዲሆኑ : በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መዋቅር ውስጥ እንዲሳተፉ : በማኀበራዊ፣በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እንዲያገለግሉ ለማድረግ የተቋማዊ ለውጡ ዓላማ ነው ሲሉ በማኀበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ምክትል ሰብሳቢ አቶ በረከት መሠረት ገልጸዋል፡፡
መጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ በማኀበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል የግቢ ጉባኤያት አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ በበኩላቸው የግቢ ጉባኤያት ዓላማቸው ተተኪ ትውልድ ማፍራት ነው ያሉ ሲሆን ለውጡ እንዲሳካ ሁሉም የራሱን አስተዋፅዖ እንዲያበረክት አሳስበዋል፡፡