🍂🍂ክፍል-➎- አምስት🍂🍂
🌿🌿"ጤዛዉ ፍቅሬ"🌿
🌻🌻(ኑዕማን ኢድሪስ)🌻🌻
❥............🍃💐💐🍃..............❥
.... ብዙ የፍቅር አይነቶች ቢኖሩም የሀቢብ አይነት ፍቅር ግን መጀመሪያዉኑም ፍቅር ሊያስብለዉ የሚችል አልነበረም፡፡
ሀምዛ በሀቢብ ንግግር ወደ መናደዱ እየሄደ ነዉ፡፡ ሀምዛ ሀቢብና ፎዚን ሊያስማማ፤ በሁለት ባለትዳሮች መካከል የነበረን ጥላቻ አስወግዶ እርቅ ለማስፈን ነበር አካሔዱ፡፡ ነገር ግን የሀቢብ ንግግር ወደ ድርድር የሚያስገባ ሳይሆን መቃቃርን የሚፈጥር እንደ ስድቡ 'ርካሽ ቃላትን የሚመርጥ 'ርካሽነቱን የሚያንፀባርቅ ባህሪ አወጣ፡፡
..."ጓደኛዬ (አለዉ ሀምዛ... ለዘብ ባለ ንግግር) ... እየዉልህ ሀቢብ በርግጥ አንተ ከፎዚ በፊት ብዙ ሴቶችን ታዉቃለህ፤ ከብዙ ሴቶችም ጋር ነበርክ፡፡ እነዚያ ጋር የነበርከዉ ብዙ አመታት ግን ፎዚ ጋር እንዳለህ የትዳር ዘመን የተባረከ ሳይሆን የረከሰ ጊዜ ነበር፡፡ ፎዚ ጋር አዲስ ህይወት ከጀመርክ ሰነባበትክ የመጀመሪያ ሰሞን ደስተኛ ነበርክ፡፡ አሁን ምን ተፈጥሮ ነዉ የተቀየርከዉ ሀቢብ...!?" ብሎ ጠየቀዉ፡፡ ሀምዛ በሚያወራበት ጊዜ ግን የሀቢብ ሀሳቡ በሙሉ በጥላቻ የመረዘዉ ልቡን ተጠቅሞ ጥላቻን እየሰነቀ ነበር፡፡
....."ሀቢብ!!? ሄይ... ወደ የት ነጎድክ?" አለዉ ከተጓዘበት አለም እየመለሰዉ፡፡
....."ሀምዛ እየሰማሃኝ ነዉ፡፡ አንተ ፎዚን ልትወዳት ትችላለህ እኔ ግን... እጠላታለሁ?" ሀምዛ የሀቢብ ነገር አዝማሚያ የገባዉ ይመስላል፡፡ ሀቢብ ወሬዉን ቀጠል አደረገና፡፡
..."ለመሆኑ ከፎዚ ጋር ከመቼ ጀምሮ ነዉ መገናኘት የጀመራችሁት?" ..." ያዉም እኔ ባለቤቷ ሳላዉቅ?? ... እ??" ብሎ ዉስጡ ያለዉን ስሜት ቀስ እያለ ያወጣዉ ጀመር፡፡
"ሀቢብ.." አለዉ ሀምዛ በተምስጦ አይኑን እየተመለከተ ..."የኔና ያንተ ጓደኝነት ዛሬ አልተጀመረም፡፡ ፎዚያን ከማግባትህ በፊት ብዙ ችግሮችንና ፈተናዎችን አሳልፈናል፡፡ አያሌ የደስታ ቀኖችን አብረን ቦርቀናል፡፡ እኔም እነዚያን መልካም ጊዜዎች በማስታወስ የተለመደዉን የጓደኝነቴን ከጎንህ ልሆን ስለፈለኩኝ፣ ትዳርህ የሰመረና በባለቤትህ ደስተኛ እንድትሆን እንጂ
ሌላን ነገር አስቤ አልነበረም፡፡" ብሎ መለሰለት በተረጋጋ መንፈስ፡፡ ሀቢብ ግን ለትዳሩ መስመር፣ ለህይወቱ መቃናት የሚጥርለትን ጓደኛዉን ዛቻም ጭምር እየተናገረዉ ነዉ፡፡
..."ሰማሃኝ ሀምዛ... ምንም እሰብ ምን ከዚያች ሴት ሴት ጋር ያለህ ግንኙነት ጤነኛ አይደለም፡፡" አለዉ፡፡ መደዋወላቸዉንና ግንኙነታቸዉን እንዲያቋርጥ በማስጠንቀቅ፡፡
..."እሺ ይቅርታ ጓደኛዬ...." ብሎ ከሀቢብ ጋር የያዘዉ ሙግት መፍትሄ እንደሌለዉና እንደማይበገርለት አወቀ፡፡
.
.
.
..... ፎዚ የቤቱ ስራ አድክሟት ምንም ሳትተጣጠብ በስራ ልብሷ ቤቷ ቁጭ የማትመለስበት በሚመስል ያለፈ ትዝታዋ ላይ ተተክላ በሀሳብ ባህር ሰምጣለች፡፡ የትዝታን ቅኔ እያዜመች፤ እጆቸቿን አገጯ ላይ እንዳስደገፈች አይኖቿ ላይርገበገቡ ምለዉ የልጅነት ምኟቷን፤ የኮረዳነት ደስታዋን ማስታወስ ይዛለች፡፡ አሁን የተማረረችበትን ህይወት በትዝታ እንኳ ትደሰትበት እንጂ...፡፡
በዚህ መካከል ሀቢብ ከጓደኛዉ ሀምዛ ጋር የነበራቸዉን እሰጥ አገባ ጨርሰዉ ባለመስማማት ተለያይተዉ ወደ ቤቱ መጣ፡፡ ቤቱ እንደደረሰ በሩን ሳያንኳኳ ከፍቶ ገባ፡፡ ፎዚያ ከበሩ ፊት ለፊት ሶፋዉ ላይ ተቀምጣ ሀቢብ በሩን ከፍቶ ሲገባ አላስተዋለችዉም፡፡ ደትዝታን ባህር እየቀዘፈች ነበርና አዮታዉ ሳታየዉ ቀረች፡፡ አይኖቿ ሀቢብን በር ከፍቶ ሲገባ ቢያዩትም ልቧ ከትዝታዋ ጋር ነበርና ሳታስተዉለዉ ቀረች፡፡ 'ልብ ካላዬ አይን አያይም' አይደል ተረቱስ፡፡
ሀቢብ የበሩን እጄታ ይዞ መልሶ ከዘጋ በኃላ እየተንጎራደደ ወደ ፎዚያ ተጠጋ፡፡ እሷ ግን አሁንም አላየችዉም፡፡ ወደ እሷ የሚጠጋዉ ሰዉ ይሁን ሌላ ነገር አላስተዋለችዉም፡፡ ወደ እሷ ተጠግቶ ከተቀመጠችበት ሶፋ ፊት ለፊቷ ካለዉ ሶፋ ተቀምጦ ..."ፎዚ አላት" እሷ ግን አልሰማችዉም፡፡ አዉቃ ዝም እንዳላለችዉና በሀሳብ እንደተዋጠች በአቀማመጧና ከሁኔታዋ አስተዉላሏል፡፡ እጁን በፊቷ ላይ እየወዘወዘ "ሄይይ ኧረ ፎዚ..." ሲላት ፎዚያ ከእንቅልፏ እንደሚነቃ አይነት ሰዉ ብትት ብላ ..." እ ሀቢቢ መጥተሃል እንዴ? ልብስ ሳጥብኮ ቆይቼ ድክም ብሎኝ ነዉ፡፡" እያለች ክስም ብሎ የነበረ ፊቷን በፈገግታ አደመቀችዉ፡፡ ሀቢብም ለጠጥ ብሎ ሶፋዉን እንደ መደገፍ እያለ ..."እ ... ነዉ?" ብሎ ወሬዉን አሳጠረዉ፡፡
..."አዎ! ሁቢ ደግሞ ሶፊ ጋር ደዉዬ ስናወራ ቆዬን" ብላ ስትነግረዉ .."ለምን እሷ ጋር ደወልሽ?" ብሎ ጮኸባት፡፡ (ሶፊያ የሀቢብ እህት፤ የፎዚያ ደግሞ የግቢ ጓደኛዋ ናት!)፡፡ በዚህ ጊዜ ፎዚያ ደንገጥ ብላ ደህና ሆኖ የነበረዉን ለምን አሁን እንዲህ ብዬ ለምን አስከፋሁት ብላ ለራሷ አሰበች፡፡ 'ግን ሶፊ ጋር እንድደዉል ለምን አልፈለገም፡፡' ብላም ራሷን ጠየቀች እንደገና መለስ ብላ 'አይይ እንደፈለገ!' አለች፡፡
..."ሀቢቢ የስራ ልብሴን ሳልቀይር እንኳ መጣህ... ቆይ ልብስ ቀይሬ ልምጣ" ብላ ከተቀመጠችበት ስተትነሳ
..."ተቀመጭ..." አላት፡፡ ደንገጥ ብላ
..."እ..." አለችዉ፡፡
..."ተቀመጭ" ብሎ ቃሉን ደገመዉ፡፡
..."እ...እ እሺ " ብላ ተቀመጠች፡፡ ፊቱ ሳይፈታ እንደተኮሳተረ ቆጣ ብሎ...
..."እንድናወራ የምፈልገዉ ጉዳይ አለ" አላት፡፡
╔═══❖•🌺🌺•❖═══╗
ይ ቀ ጥ ላ ል
╚═══❖•🌺🌺•❖═══╝
❥............🍃💐💐🍃..............❥
@maraki_lyrics