የምሽት ጂኒ
(✍ሙከረም ሙስጦፋ)
ምሽት ላይ ነው ወቅቱ
ተሽከርካሪ ይዤ
እየተንፈላሰስኩ ስንኳለል ባ'ስፓልቱ
ከሩቁ አየኋት ፡ ፈዘዝኩኝ እሷን ሳይ
እንዴቱን ላሽከርክር ፡ ተደቅና አይኔ ላይ
እንደምንም ብየ....
ጠጋ አልኩኝ ወደሷ በተሽከርካሪዬ
ፍቀጂልኝና እስካሻሽ ልሸኝሽ...?
.....ወዴት ነሽ...?....... እሙዬ😍?
ብዬ ስጠይቃት...
ሳታቅማማ መጣች
ከጋቢና ገባች
እኔም ዝም
እሷም ዝም
ስንሄድ.....ስንሄድ....ስንሄድ...
ሰበረች ዝምታን ፡ ተንቀሳቀሰ አፏ
በምስጋና ቃላት ፡ ተሰናበተችኝ ስትደርስ ከደጃፏ
ምን እዳስነካችኝ ኧረ ጉዱን እንጃ
ግንስ ትቻት ልሔድ አቃተኝ እርምጃ
ባ'ማላይ ውበቷ ማልዬ ቀረሁኝ
እሷን ትቼ ከቤት መመለስ ተሳነኝ
አሷም እንዲህ አለች ሁኔታየን አይታ
አይተኸው ተመለስ የቤቴን ገፅታ
ከቤቷ አጠገብ መኪናየን ትቼ
ገባሁ ከርሷ ጋራ እስካየው ጓጉቼ
😮 Wow! wow! የቤቷ ፅዳቱ
ደስ የሚል መዓዛ
ቀልብን የሚገዛ
የሚያማምር ምንጣፍ
ውበትን ሚያጎናፅፍ
ጌጡ የግድግዳው
ምርጡ የተዋበው
ቤቷን አሳምሮ አጊጦ ሞሸረው
መርታኝ እጄን ይዛ ወደ መኝታ ቤት
አዳሬ እዛው ሆነ ጠልፎኝ የሷ ውበት
😱😱😱😱😱😱😱😱
ወይኔ😳.....ጠዋት ስነቃ ግን ያገጠመኝ ክስተት
እጅግ አስደንጋጭ ነው የሚያስቅ ሲያልፍበት
ከቆሸዎች መንደር አህያ ታቅፌ
ራሴን አገኘሁት ስነቃ ከ'ንቅልፌ
ዞር ዞር ብየ ስፍራውን ሳስሰው
መኪናየን አየሁ መሀል ላይ ከቆሼው
እንዴ😳.... አይኔን አላመንኩም
ያ የሚያምር ግቢ ማራኪው ቤትሳ...?
ማታ ቆንጆ አቅፌ ከልቤ ስደሳ
ጠዋቱን ስነቃ...
ታቅፌ ተገኘሁ የአህያ ሬሳ
እንዴት ሊሆን ቻለ...?
እኔማ በምሽት
ችክ አገኘሁ ብዬ ሳሳድድ ልበላት
ለካስ ይቺ ቆንጆ
ሰው መሆኗ ቀርቶ የምሽት ጂኒ ናት 😱
አኡዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧኒ ረጂም😬
____________
ቀን 26/11/2014
ምሽት / 5:36
------------------------
@mengeshaye
(✍ሙከረም ሙስጦፋ)
ምሽት ላይ ነው ወቅቱ
ተሽከርካሪ ይዤ
እየተንፈላሰስኩ ስንኳለል ባ'ስፓልቱ
ከሩቁ አየኋት ፡ ፈዘዝኩኝ እሷን ሳይ
እንዴቱን ላሽከርክር ፡ ተደቅና አይኔ ላይ
እንደምንም ብየ....
ጠጋ አልኩኝ ወደሷ በተሽከርካሪዬ
ፍቀጂልኝና እስካሻሽ ልሸኝሽ...?
.....ወዴት ነሽ...?....... እሙዬ😍?
ብዬ ስጠይቃት...
ሳታቅማማ መጣች
ከጋቢና ገባች
እኔም ዝም
እሷም ዝም
ስንሄድ.....ስንሄድ....ስንሄድ...
ሰበረች ዝምታን ፡ ተንቀሳቀሰ አፏ
በምስጋና ቃላት ፡ ተሰናበተችኝ ስትደርስ ከደጃፏ
ምን እዳስነካችኝ ኧረ ጉዱን እንጃ
ግንስ ትቻት ልሔድ አቃተኝ እርምጃ
ባ'ማላይ ውበቷ ማልዬ ቀረሁኝ
እሷን ትቼ ከቤት መመለስ ተሳነኝ
አሷም እንዲህ አለች ሁኔታየን አይታ
አይተኸው ተመለስ የቤቴን ገፅታ
ከቤቷ አጠገብ መኪናየን ትቼ
ገባሁ ከርሷ ጋራ እስካየው ጓጉቼ
😮 Wow! wow! የቤቷ ፅዳቱ
ደስ የሚል መዓዛ
ቀልብን የሚገዛ
የሚያማምር ምንጣፍ
ውበትን ሚያጎናፅፍ
ጌጡ የግድግዳው
ምርጡ የተዋበው
ቤቷን አሳምሮ አጊጦ ሞሸረው
መርታኝ እጄን ይዛ ወደ መኝታ ቤት
አዳሬ እዛው ሆነ ጠልፎኝ የሷ ውበት
😱😱😱😱😱😱😱😱
ወይኔ😳.....ጠዋት ስነቃ ግን ያገጠመኝ ክስተት
እጅግ አስደንጋጭ ነው የሚያስቅ ሲያልፍበት
ከቆሸዎች መንደር አህያ ታቅፌ
ራሴን አገኘሁት ስነቃ ከ'ንቅልፌ
ዞር ዞር ብየ ስፍራውን ሳስሰው
መኪናየን አየሁ መሀል ላይ ከቆሼው
እንዴ😳.... አይኔን አላመንኩም
ያ የሚያምር ግቢ ማራኪው ቤትሳ...?
ማታ ቆንጆ አቅፌ ከልቤ ስደሳ
ጠዋቱን ስነቃ...
ታቅፌ ተገኘሁ የአህያ ሬሳ
እንዴት ሊሆን ቻለ...?
እኔማ በምሽት
ችክ አገኘሁ ብዬ ሳሳድድ ልበላት
ለካስ ይቺ ቆንጆ
ሰው መሆኗ ቀርቶ የምሽት ጂኒ ናት 😱
አኡዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧኒ ረጂም😬
____________
ቀን 26/11/2014
ምሽት / 5:36
------------------------
@mengeshaye