ሄ ዋ ን 🌺
❣ :¨·...............:¨·.❣
♥️ ክፍል 13
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Estifanos tekka
ማክ ለአባቱ ሹፌር ደውሎለት በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ እስኪነጋ እንቅልፍ ባይኔ አልዞረም ጠዋት ቁርስ ላይ ለማክ አባቴ በጣም እንደናፈቀኝና ልደውልለት እንዳሰብኩኝ ስነግረው ጥሩ ሀሳብ አለመሆኑን ነገሮኝ ባልደውልለት የተሻለ እንደሆነ አስጠነቀቀኝ ቢሮ ከገባሁ በኃላ ግን ደጋግሜ አባቴን ማሰብ አላቆምኩም
የመጣውን ለመቀበል ራሴን አሳምኜ አባቴ ጋር ደወልኩ ገና ድምፄን ሲሰማ ነበር አንቺ መድረሻ ቢስ ምን ይሁን ብለሽ ደወልሽ አታገኘኝም ነው ... እ ... እንደናቅሽኝ እየነገርሽኝ ነው? ይኼውልሽ እናትሽ የገባችበት ጉድጓድ ብትገቢ አታመልጭኝም መድረሻ ቢስ ሰላም እንደነሳሽኝ እንደዶሮ አንቄ ለሽፈራው ካልሰጠሁሽ ወንድ አይደለሁም አለኝ
ይሄንን ሁላ ሲያወርድብኝ አንድም ቃል አልተናገርኩም ብቻ ባይሆን ድምፁን ስለሠማው ትንሽም ቢሆን ደስ ብሎኛል ወይ አባ ምን ብትደብቅ ነው ሰላም አተህ ሰላም የነሳኸኝ አልኩ ለራሴ ስልኩን ዘግቼ ማክን ከሹፌሩ ጋር ሲገናኙ አብረን ብናገኘውስ ብዬ ልጠይቀው ስላሰብኩ ወደሱ ሄድኩ ማክ ቢሮ አልነበረም... ፀሀፊውን ስጠይቃት ተቻኩሎ እንደወጣ ነገረችኝ ደወልኩለት ስልኩን አያነሳም ሱማክ የትም ቢሄድ ለኔ ሳይነግረኝ አይሄድም ስልኩን አለማንሳቱ ይበልጥ አስጨነቀኝ ተረጋግቼ መቀመጥ አልቻልኩም ደጋግሜ ብደውልም አይነሳም... በጭንቀት ራሴ ተወጠረ ማክ ከቢሮ ከወጣ 4 ሰዓታት ተቆጠሩ በዛ ሁኔታ ቢሮ ምንም ስለማልሰራ ወደቤት ሄድኩ... ለተጨማሪ 1 ሰዓት ጠበኩ ምንም የለም የማክ ስልክ አይነሳም... በመጨረሻም ሁሉም የማክ ጓደኞች ጋር ደወልኩ ከማንም ጋር አልተገናኘም መልሶ ካልደወለ እንድደውልላቸውና ለፖሊስ እንደምናመለክት ነገሩኝ ሁለቱ ጓደኞቹ እንደሚመጡ ነግረውኝ ስልኩን እንደዘጋሁ ስልኬ ጠራ ማክ ነበር
ማክ የኔ ፍቅር የት ሆነህ ነው ለምንድነው የማታነሳው በጭንቀት ልትገድለኝ አስበህ ነው... የጥያቄ መዓት አደራረብኩበት...
የኔ ቆንጆ ስላስጨነኩሽ ይቅርታ እየመጣሁ ነው አለኝ በደከመ ድምፅ ማክ የት ነህ የሆንከው ነገር አለ ድምፅህ ልክ አይደለም ምንድነው የተፈጠረው ያለህበት ልምጣ አልኩት እያለቀስኩ አያስፈልግም ማሬ እየደረስኩኝ ነው ትንሽ ታገሺኝ አለኝ ልቤ በሀይል ይመታል በጣም እያለቀስኩ ነው ምን እንደማደርግ ግራ ተጋብቼ ግቢ ውስጥ ወዲያና ወዲህ እያልኩ የማክን መምጣት መጠባበቅ ጀመርኩ ከግማሽ ሰዓት በኃላ የመኪና ድምፅ ስሰማ እየሮጥኩ ወደበሩ ስሄድ የማክ ጓደኞች ነበሩ ... አዲስ ነገር ካለ ሲጠይቁኝ የሆነውን ነግሬያቸው ማክን አብረን መጠበቅ ጀመርን ትንሽ ቆይቶ ሌላ የመኪና ድምፅ ስንሰማ ሁላችንም ወጣን ዘበኛው በሩን ሲከፍተው መኪናው ውጪ እንደቆመ ነው ማንም ጋቢና የለም እየሮጥኩ ወጥቼ ሳይ ማክ በደም ተነክሮ ከኃላ ተኝቷል እየጮህኩ ጓደኞቹን ለርዳታ ጠራኻቸው ወደሆስፒታል ንዳው ብዬ አንዱ ጓደኛው ላይ ጮህኩኝ... ማክ በደከመ ድምፅ ደህና ነኝ የኔ ፍቅር አለኝ ማክ ማነው እንደዚህ አድርጎ አምጥቶ የጣለህ ማክ ክፉ ሰው ነው አንተ ላይ እንደዚህ ያደረገው እያልኩ ያለማቋረጥ አለቅሳለሁ እሱ እንደዛ ሆኖ እኔን ለማፅናናት ይሞክራል ጓደኞቹም እንድረጋጋ እየለመኑኝ ሆስፒታል ደረስን ህክምና ተደረገለት የማክ እጁ ላይ ቅጥቅጥና ግንባሩ ላይ ጉዳት ከመድረሱ ውጭ የከፋ ነገር እንደሌለውና ግንባሩ መሰፋት እንዳለበት ዶክተሩ ነግሮኝ ወጣ
ከሰዓታት በኃላ ወደቤታችን ተመለስን የማክ ጓደኞች ተሰናብተውን ከሄዱ በኃላ ማክን በጥያቄ አጣድፈው ጀመር... ሄዊ የኔ ቆንጆ ተረጋጊ አባቴ ነው በቃ እንደዚህ ያደረገው ሹፌሩ ከኛ ጋር መሆን አልቻለም ከኔ ጋር ቀጠሮ እንዳለው ላባቴ ነግሮት ነው አባቴ ከሱ ምን እንደፈለግን አውቋል በር ላይ ጥሎኝም የሄደው ሹፌር የሱ ነው አሁን መኖሪያችንን አውቋል መጠንቀቅ አለብሽ ግን አንቺን በአካል ማግኘት ነው የሚፈልገው ይሄን ደግሞ እኔ አልፈቅድም አለኝ እና እንዴት ልጁን ጨክኖ እንደዚህ ያደርጋል በጣም ተናዶብኛል ሰዎቹ ሲደበድቡኝ እንኳን ለማየት አልደፈረም ውጪ ቆሞ ነበር አንቺን እንድመልስሽ ለማስፈራራት እንጂ ሌላ ነገር ማድረግ ቢፈልግ ይችል ነበር አሁን እሱን እርሽው የኔ ማር የምትፈልጊውን ነገር በየትኛውም መንገድ አደርጋለሁ አንቺ ግን ራስሽን አደጋ ላይ የሚከት ተግባር እንዳትፈፅሚ
አባቴ ቢያገኝሽ አንዴ እጁ ከገባሽ አይለቅሽም እስረኛው ነው የምትሆኚው እኔም ላድንሽ አልችልም ቢቻል ራስሽን አሳምነሽ ከዚህ አገር እንውጣ ካልሆነ ግን ታገሽ አለኝ የማክ ንግግር ጠንካራ ነበር፡፡ እኔም ያለኝን እንደማደርግ ቃል ገባሁለት ከዛን ቀን በኃላ ለሳምንት ስራ አልገባንም ነበር በጣም ደስ የሚል የፍቅር ጊዜ እያሳለፍን ነው፡ የሁለታችንም ፍቅር ጨምሯል ፍቅር እንጂ እኛ ጋር ፀብ የለም ከማክ ጋር በጣም ነው የምንዋደደው ሁለታችንም ደስተኞች ነን... ዛሬ የማክ እውነተኛ ሚስት የመሆን ፍላጎቴ ጨምሯል የምንጋባበት ጊዜ ገና ገደብ የለውም ሽፈራው እስከሚፈታኝ ከታገስን ልናረጅ ነው ብቻ በቃ ከፍቅረኝነት የሚስትነት ህይወት አማረኝ ..እኔና ማክ እንደባልና ሚስት አንድ ላይ እንኑር እንጂ ገና መጋባታቸውን የሚጠባበቁ ፍቅረኛሞች ነን እኔና ማክ ለመጋባት የሚከለክለን የአባቱ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ደሞም ለማክ አባት የወረቀት ሚስት እንጂ የእውነት የትዳር አጋሩ አይደለሁ ይሄንንስ አምላክ ከሀፂያት ይቆጥርብኝ ይሆን አልኩ ለራሴ
አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ እየተፋቀርን አንተን ፈርተን እስካሁን ቆይተናል አሁን ግን የትግስቴ ጥግ ላይ ደርሻለሁ አንተ ማረኝ አልኩ በልቤ በጣም ጣፋጭ እራት በራሴ እጅ አዘጋጅቼ ቤቱን ሮማንቲክ አደረኩት.....
✎ ክፍል አስራ አራት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
✨#ህይወቴ✨
🥀 @hiwote_love_story 🥀
🥀 @hiwote_love_story 🥀
┄┄┉┉✽»🌺✿🌺»✽┉┉┄┄