መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿

Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Esoterics

☑ ከጥንት አባቶቻች በተቸረን ሰሎሞናዊ ጥበብ ተፈጥሮ ያበቃላቸው የእፅዋት መድሀኒቶችን በመጠቀም ክፉ ዓይነ ጥላ ፣ በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፉ መናፍስት መፍትሔዎቻቸው ይተነተናሉ።
☑ አድራሻ ቁጥር 1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ቁጥር 2 አ/አ እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንልካለን
📞#0918834904
📞#0915310455
መልዕክት ካለዎት @merigetaamedeberhan

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Esoterics
Statistics
Posts filter

✝️መልክዓ ዘካርያስ ✝️

👉🏾መፍትሔ -ሃብት ወግርማ -ሞገስ ወመፍትሔ -ሥራይ መጽሐፍ ነው::
👉🏾ድንቅ ከሆኑት የፈጣሪ ልዩ እና ሕቡዕ ስሞች ተቀናጅቶ ልዩ መፍትሔ የሚሰጥ የጥበብ መጽሐፍ ነው::
👉🏾ወደ 35 የሚጠጋ ገቢር አለው እጅ በእጅ ከብራና መጽሐፍ በጥራት የተገልበጠ የጥበብ መጽሐፍ ነው::
👉🏾ይህ መጽሐፍ በእውነት መጠቀም የሚሻ ሰው ቢኖር በአድራሻየ መሰረት በመምጣት ሃርድ ኮፒውን መውሰድ ያልቻላችሁ እንሆ!
🙏ፍፁም የእግዚአብሔርን ሕግጋትን አይጻረርም::
ገቢሮቹ በውስጥ መስመር የምልክላችሁ ይሆናል::

👉አድራሻችን
አዲስ አበባ አየር ጤና ወደ ዓለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጣያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ትራንስፖርት ማሰልጠኛው አጠገብ እንገኛለን
👉 ዋና መገኛ ቦታዬ ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከመናኸሪያው ወደ ሽዲ መሄጃ መስመር ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ አገኛለሁ።
☎️#0918834904
☎️#0915310455

✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigetaamedeberhan
✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigeta_amedebrhan

✅ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/profile.php?id=100076378898155

✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/mergeta_amdebrhan

✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
t.me/mergeta_amdebrhane

✳️የቲክቶክ ቻናላችን
http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan

👉የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።

🌱🌱🌱 ለገበያ ፦ 🌱🌱🌱
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_፩_አምላክ
ጸሎት በእንተ ምስሀበ ንዋይ ወምስሀበ ንዋይ ወምስሀበ ገበያ ጀርጅር አጀርጅር አንጀር አንጀርጅር አንፈስፍስ ልቦናሆሙ ልቦሙ ለነጋድያን ወለነጋ ድያት ሊተ ለገብርከ ዕገሌ
አልጅም ፯ መልጅም ፯ ማቂም ፫ አማቂም  ፫ አንፍስ አንፈስፍስ አስተራውጽ ልቡናሆሙ ለነጋ ድያን ወለነጋድያት ከመ የሀቡኒ ንዋዮም ከመ እሲጥ ወእሳየጥ በላዕለ ምስያጥ ወገበያ እገሌ

ገብርከ ፦ ዕገሌ በዕፅ ሳቤቅ፡ ቀለም ፣ በሴት ቀስት ብዕር ጽፈህ ፯ ጊዜ ደግመህ ያዝ ለወንድ ለሴት ይሆናል

        🌱🌱መፍትሔ ሀብት 🌱🌱
ሎፍሐም ፫ ወሐፍሎን ፫ ንምሎስ ፫ ማሎስ ፫ ኤያቡኤል ፫ አዮራስነ ፫ አየባአሰ ፫ መሐጅን ፫ ምምዕዋደን ፫ በሄራን ፫ ስምከ ተማኅፀንኩ አነ ገብርከ እገሌ
ይብራህ ገጽየ ከመ ፀሐይ ብሩህ መከመ ይጥእሞሙ ነገርየ እምፀቃውዓ መዓር መሦከር ምስለ ነፍሶሙ ይውደዱኒ ሕዝብ ወአሕዛብ ታሕተ መከየደ እገርየ ይስግዱ ወይሳአዱ ወየሀቡኒ ነዋየ መብልዓ ወመስቴ ቶቤ አታቤ ቅናሽኸር ዱላዋጀን ደነዋጃጀን ሐሰት መጅርግ ፍታሕ ፍትሖ ወጀፍ ወቅትል ልቦሙ ለሰብአ ዛቲ ዓለም በፍቅረ ዚአየ ሊተ ለገብርከ እገሌ ፫ ጊዜ በሜሮን ደግመህ ተቀባ ።

        🌱🌱ዐቃቤ ርእስ 🌱🌱
ወድድደርሙኒ አሽሙናይን ሸሹሙናይን ሸሹላይን ላዮንጋ አድኀነኒ እምፀርየ ወእምጸላእትየ ለኩሎሙ ደቂቀ አዳም ወሔዋን ሊተ ለገብርከ እገሌ በቅብአ ቅዱስ ፯ ጊዜ እፍ እያልክ ድገም ከመሐል እጅህ ላይ ጠብ አድርገህ መሐል ግንባርህን ተቀብተህ ሂድ ።

፤፤፤፤፤፤፤ የጉበት በሽታ(ሄፕታይተስ)፤፤፤፤፤፤፤
ጉበት ደምን እያጣራ አስፈላጊ ወደሆኑት ክፍሎች የሚያሰራጭና የሚያከፋፍል አካል ነው ።
ጉበት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሊመረዝ ይችላል ፤
የጉበት በሽታ ያዘው ሰው ሰውነቱ ይጠቁራል ፤
ደሙ ይደፈርሳል ፤ ሆዱ ያብጣል ፤ አይኑ ቢጫ ይሆናል ፤ ሽንቱ የጠጅ አንቡላ ይመስላል ፤
ቅባት ያለበት ምግብ በሚመገብበት ጊዜ ያቅለሸልሸዋል ፤ ምግብን በደምብ አይመገብም ይከለክለዋል ፤ እራሱን ያዞሩዋል ምግብንም እንደልብ ካለመውሰዱ የተነሣ በጣም ይከሳል ይጠወልጋል ፤
የጉበት በሽታ ሕመም አንዳንድ ሰዎች የወፍ በሽታ እያሉ ይጠሩታል ።
      ይህንን በሽታ ለመከላከል ፤
የአቱች ስር
የአቆራራጭ ስር
የአላኩ ቅጠል
የእንጆሪ ቅጠል
የዕፀ መንዳ ቀንበጥ
የማአንጠል ሥር
የሎሚ እሸት ሥርና ቅጠል
የቄስ ባቄላ ሥር
የገትን የሥሩ ቅርፊት
የጦስኝ ቅጠል
እነዚህን ዕፅዋቶች በአንድነት ወቅጦ የፍየል ወተት ወይም የበግ አሞት ከዕፀዋቶቹ ጋር ቀላቅሎ በሻይ ማንኪያ አንድ ጨምሮ ጠዋት ጠዋት ከማር ጋር እያፈሉ መጠጣት ነው

✅ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/profile.php?id=100076378898155

✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/mergeta_amdebrhan

✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
t.me/mergeta_amdebrhane

✳️የቲክቶክ ቻናላችን
http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan

👉የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።

✔️✔️የዳዊት ገቢር
#ለአቃቤ_ዕርስ
❤️መዝሙር፭ #ቃልየ፧አጽምዕ፧እግዚኦ፧ወለቡ፧ጽራሕየ.... ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም
#ገቢሩ..በየብስም,ባሕርም,በመንገድም እህል ሳትቀምስ በቅባ ቅዱስ ,በሜሮን,ውሀ ባልነካው ቅቤ ..በማንኛውም ቅባት ላይ ፯ ጊዜ ደግመህ ተቀባ #ከሞት ይጠብቅሀል
እንዲሁ #ለራስ_ምታት በቅቤ ፯ ጊዜ ደግመህ ተቀባ ።
#አይኑን_ለታመመ
❤️መዝሙር ፮
#እግዚኦ፣በመዓትከ፣ኢትቅሥፈኒ፣ወበቅሠፍትከ፣ኢትገሥጸኒ.... ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም
#ገቢሩ .. መዝሙሩን ፯ ጊዜ ደግሞ ፅፎ መያዝ እንዲሁ በቅቤ ፯ ጊዜ ደግሞ የታመመውን አይን መቀባት ያድናል ።
#ደግሞም ለምትፈራው ነገር ሁሉ ከቤት ሳትወጣ ማንኛውንም ሽት ቤት ሳትጠቀም ከሰው ሳትነጋገር የምትፈራውን ሰው ስም ከነእናቱ  ስም እየጠራህ ፯ ጊዜ ድገም ከእሱ ትድናለህ ።

#አስማት_ለተዋለበት_የአጋንንት_ቁራኛ_ለያዘው_ሰው
❤️መዝሙር ፯
#እግዚኦ፣አምላኪየ፣ብከ፣ተወከልኩ፣ኢትግድፈኒ....ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም ።
#ገቢሩ .. ፀሀይ ከማታየው ጉድጓድ ውሀ ቀድተህ ከዕለቱ ከዕለቱ ሐፁረ መስቀል ፣ አርድእት ፣ ባርቶስ ጋር ፰ ቀን ፯ ፯ጊዜ ደግመህ አጥምቀው በእግዚአብሔር ቸርነት ይድናል ።  ይህንንም ስታደርግ ደርግ ልጅና ከብት ማንኛውንም ሰው ከሌለበት ሜዳ ነው ።  ከቤትም ከመንገድም አትድገም
#እንደዚሁ ባሏ ለጠላት ሴት በቅቤ ፯ ጊዜ ደግመህ ሰውነቷን ትቀባ ባሏ ይወዳታል ።

#ለታመሙ_ሕፃናት
❤️መዝሙር ፰
#እግዚኦ፣እግዚእነ፣ጥቀ፣ተሰብሐ፣ስምከ፣በኩሉ፣ምድር..ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም ።
#ገቢሩ መዝሙሩን ጽፈህ አሲዘው ይፈወሳል ።
#እንዲሁ ለታሰረ ሰውም በኅብስት ላይ ጽፈህ ስጠው በእግዚአብሔር ቸርነት ይፈታል
#እንዲሁ በዝርግ ሳህን ላይ ጽፈህ በዓሣ መረብ ከተህ ከባህር ብትጥለው ብዙ አሳ ይያዝልሃል ። 
#እንዲሁ ለገበያ በእንቧጮ አርጩሜ ፯ ጊዜ ደግመህ የምትሸጠውን  እቃ ፯ ጊዜ ብትመታው ይሸጣል
#እንዲሁ ጥሬ ጨው በማር ለውሰህ ፯ ጊዜ ደግመህ ብትበላ ከሰው ጋር በፍቅር እና በሰላም ለመኖር ያስችልሃል ።

#ጠላት_በበረታብህ_ጊዜ
❤️መዝሙር ፱
#እገኒ፣ለከ፣እግዚኦ፣በኩሉ፣ልብየ ... ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም ።
#ገቢሩ .. የራሱን የእናቱን ስም እየጠራህ ፫ ፫ ጊዜ ብትደግም ይታገስሃል ።
#እንዲሁ ሀገር ቢጠላህ ፯ ጊዜ በሊት ውሀ ደግመህ በ፬ቱ ማዕዘን እርጭ ሰው ሁሉ ይወድሃል።

✔የመዝሙረ ዳዊት ገቢር
1. መዝሙር 2- ለጠላት በብር ቀለበት 7ጊዜ ደግመህ ያዝ
2. መዝሙር 3- የጸሎት- በጫት ልምጭ 7 ጊዜ ደግመህ ምታ እቃ ለመሸጥ
3. መዝሙር 5 - ለአቤቱታ ስትሄድ ጧት 7 ጊዜ ድገም
4. መዝሙር 7- የጠላት መከላከያ የሚደገም
5. መዝሙር 18- ጌታህ በተቆጣ ጊዜ 7 ጊዜ ድገምና ተቀባ
6. መዝሙር 19 - መዳመጫ ላይ ሆነህ 49 ጊዜ ድገም እግዚአብሔር ያሰብከውን ሁሉ ይፈጽምልሃል
7. መዝሙር 20 ለበረከት በውሃ ድገምና ቤቱን እርጨው 49ጊዜ ነው የሚደገመው

8. መዝሙር 22 በታሰርክ ጊዜ በዉሃ 7 ጊዜ ድገምና እግርና እጅህን ታጠበው
9. መዝሙር 29- ህልም ለማየት 7 ጊዜ ደግመህ ተኛ
10. መዝሙር 31 -ለምትሰራው ሁሉ በወይን 7 ጊዜ ደግመህ ጠጣ

11. መዝሙር 32 መኪና ላይ በተቀመጥክ ጊዜ በከርቤ 7 ጊዜ ደግመህ ተቀመጥ
12. መዝሙር 33- ሲሳይና ረድኤት ስታጣ ፀሐይ ሳይወጣ 7 ጊዜ ድገም
13. መዝሙር 36- በገንዘብህ በቀኑብህ ጊዜ ብቻህን ሆነህ በቀስታ 7 ጊዘዜ ድገም
14. መዝሙር37- በአደባባይ በቀስታ ድገም ንግግር ያቆማል በአደባባዩው
15. መዝሙር41- ሴት ስትጠላህ 7 ጊዜ ደግመህ ቀባት መመለሻው መዝሙር 42 ነው
16. መዝሙር 46 ሰው አልታዘዝም ባለህ ጊዜ በሸክላ ላይ ቆመህ 7 ጊዜ ድገም
17. መዝሙር 49- ሰው በከንቱ በተነሳብህ ጊዜ 7 ጊዜ ጠዋ ቆመህ ድገም።
18. መዝሙር 51 - ሰው ከሳት( ጠላት) ሲነሳብህ ከ 7 ቀለማት ፅፈህ ከደጅ ቅበር።
19. መዝሙር 61- ጠላት በተነሳብህ ጊዜ የቀብር አፈር 16 ጊዜ ደግመህ ከባህር ጣል፡፡

20. መዝሙር 69- ሰው እንዳይመታህ ጧት ጧት 7 ጊዜ ድገም
21. መዝሙር 72- ለፍቅር በቅባ ቅዱስ 4/9 ጊዜ ደግመህ ገፅህን ተቀባ
22. መዝሙር 73- ለብር በተነሳብህ በፍየለፈጅ ተቀጽላ ደግመህ በክንድህ ያዝ
23. መዝሙር 74 -ጠላት ከተነሳብህ በሎሚ 7 ጊዜ ደግመህ ፊትህን ተባበስ (ተቀባ)
24. መዝሙር 75- ሰው በሐብት ነገር በተነሳብህ ጊዜ ከበቀል ድንጋይ ቆመህ 7ጊዜ ድገም
25. መዝሙር 79- ገንዘብክን በወሰዱብክ ጊዜ ሲነጋ 14 ጊዜ ድገም ይመለስልሃል
26. መዝሙር 80 ወደ አረመኔ ሀገር ስትሄድ 7 ጊዜ ደግመህ ሂድ
27. መዝሙር 81- ጋኔን የያዘው ሰው በውሃ 7 ጊዜ ደግመህ አጥምቅ
28. መዝሙር 82 - በታሰርክ ጊዜ 7 ጊዜ ድገም
29. መዝሙር 83- ለሥራይ በአቱችና በፍየል ቅቤ ደግመህ ጠጣ

30. መዝሙር 57- ከብት እንዳይበላ ለጅብ መከላከያ ቦኑ አጋፍሬ ለፃድቃን አለው ድረስ 7 ጊዜ ድገም
31. መዝሙር 84- ማደርያ ስታጣ ከታቦት ፊት ቆመህ 7 ጊዜ ድገም
32. መዝሙር 85- ንጉሥ በተቆጣህ ጊዜ እህል ሳትቀምስ 7 ጊዜ ድገም
33. መዝሙር 87- ወደምስራ በሚፈስ ዉሃ 7 ጊዜ ደግመህ ታጠብ ከመኪና አደጋ ትድናለህ
34. መዝሙር 88- ልጅህና አሽከርክን በካዱህ ጊዜ ሌት ብቻህን ክህልህን ይዘህ ድገም
35. መዝሙር 90 ማታ 3 ጊዜ ጧት 3 ጊዜ ድገም ከመኪና አደጋ ትድናለህ
36. መዝሙር 92- ፍቅር ስታጣ በውሃ 30 ጊዜ ተባበሰው ጠጣ ደግመህ በምራቅህ ተቀባ
37. መዝሙር 94- የቤት ሰው አላፈቅር ሲልህ በርግብ ደም 32 ጊዜ ደግመህ ቤቱን እርጭ
38. መዝሙር 97 -ስደትና መኪና ባገኘህ ጊዜ በበግ ደም 3 ጊዜ ደግመህ ቤቱን እርጭ
39. መዝሙር 100- ባልንጀራህ እንዳይከዳህ ከከከርቤ 9 ጊዜ ደግመህ ተቀባ

40.መዝሙር በክፉ ወር- በዘበ 4.4.ጊ
41. መዝሙር 101- ሀብትህን በወሰዱብህ ጊዜ 7 ጊዜ ድገም
42. መዝሙር 111-ንብረትህን ለማብዛት በዶቅማ ተቀጽላ 7 ጊዜ ደግመህ ከቤት አስቀምጥ
43. መዝሙር 112- ሰው በናቀህ ጊዜ ዕለት ዕለት 7 7 7 ጊዜ ድገም
44.መዝሙር 115- ሲይዙህና ስትታሰር በውሃ ደግመህ ጠጣ
45. መዝሙር 117- ለሥራይና ጥላ ወጊ 47 ጊዜ ደግመህ ጠጣ
46.መዝሙር 118-መንገድ ስትሄድ ደግመህ ሂድ ጥሩ ነው
47. መዝሙር 119-- ክፉ ነገር ሲነሳብህ ድንጋይ ተሸክመህ 3 ጊዜ ደግመህ ጠጣ
48.መዝሙር 125- ለምትሰራው ስራ ሁሉ እንዲቀናህ 7 ጊዜ ድገም
49.መዝሙር 133- ከመኝታህ ተነስተህ 3 ጊዜ ድገም
50. መዝሙር 14 - ለመንገድ 7 ጊዜ ድገም
51. መዝሙር 49 ለምጥ 7 ጊዜ ደግመህ በብርሌ(በጠርሙስ) አጠጣ

👉አድራሻችን
አዲስ አበባ አየር ጤና ወደ ዓለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጣያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ትራንስፖርት ማሰልጠኛው አጠገብ እንገኛለን
👉 ዋና መገኛ ቦታዬ ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከመናኸሪያው ወደ ሽዲ መሄጃ መስመር ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ አገኛለሁ።
☎️#0918834904
☎️#0915310455

   ✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
          @merigetaamedeberhan
    ✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
           @merigeta_amedebrhan

#መርጌታ_አምደ_ብርሃን_የባህል_ህክምና
#መዝሙረ_ዳዊት_በውስጡ_ያዛቸው_ጥበቦች ።
ከመዝሙረ ዳዊት ህእቡ ስሞች ጋር በማወዳጀት የሚጸለይ ጥበብ እንዳለ ሁኖ ትንሽ ስለ መዝሙረ ዳዊት ግንዛቤ ይፈጥርልን ዘንዳ ነው ይህንን ማቅረቤ!🌿
👉ይነበብ👇
❤️የመዝሙረ ዳዊት ዓይነቶች እንዴት መለየት እንችላለን? መዝሙራት በምን ዓይነት ሁኔታ ይከፈላሉ? አመዳደባቸውስ እንዴት ነው?❤️

👉የመዝሙራት ዓይነቶች መለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ቀጥሎ የተጻፈው መረጃ ሊመራን ይችላል፡፡
የምስጋና መዝሙሮች ፦

👉ሀ) የእግዚአብሔርን ስም የሚያመስግኑ(መዝ 8፤ 20፤30፤34፤65፤68፤75፤76፤83፤87፤88፤91፤95፤107፤136)፡፡
ለ) ከመከራ ማዳኑን የሚያወድሱ (መዝ 18፤30፤34፤65፤75፤115፤116፤118፤138)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች ዋና ትኩረታቸው እግዚአብሔርን ማመስገንና ማወደስ ነው፡፡ የሚያመሰግኑትም እግዚአብሔር ለፍጥረት ሁሉ ስላደረገውና እያደረገው ስላለው ድንቅ ሥራ ነው፡፡

👉ኃጢአተኛ በኃጢአቱ የሚያዝንበት(መዝ 6፤ 32፤38፤51፤102፤130፤143)፡፡
የዚህኛው ክፍል ዋና ትኩረት የኃጢአተኛ ሰው መጸጸትና ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ልመና ነው፡፡ ኃጢአተኛው እግዚአብሔርን እንዳሳዘነ አምኖ በመገንዘብ ስሕተቱን ይቀበላል፤ ያዝናል፤ ይጸጸታል፤ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ምሕረት ይለምናል፡፡
በመከራ ያለ ሰው የሚጸልይበት (የሚጽናናበት)(መዝ 3፤5፤7፤17፤20፤30፤31፤54፤59፤142)፡፡
በመከራ ውስጥ ያለ ሰው ስለደረሰበት መከራ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል፤ ይመጸናል፤ መከራውን ለእግዚአብሔር ይናገራል፤ መከራ እንዲደርስበት ያደረጉት ሰዎችን ይራገማል፤ በመከራ ውስጥ እያለ እግዚአብሔር ለምን ዝም እንዳለው ይጠይቃል፤ ከመከራው እንዲያወጣውም ይማጸናል፡፡

👉ዘማሪው እግዚአብሔርን ፣ ሕጉንና ቤቱን የሚናፍቅበት(መዝ 16፤ 17፤ 19፤ 40፤ 42፤ 45፤ 63፤ 73፤ 84፤ 119፤ 122፤ 128፤ 132)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች የሚያተኩሩት በእግዚአብሔር ሕግ ፣ በቤተ መቅደስና በኢየሩሳሌም ከተማ ዙሪያ ላይ ነው፡፡ ቤተ መቅደስ እንደ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቦታ የተጠቀሰበትም አለ፡፡ ስለዚህ ዘማሪው ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመሄድ እንደሚናፍቅና እንደሚደሰት ይናገራል፡፡ ዘማሪው እግዚአብሔርን ለማየት እንደሚናፍቅ በተለያየ መልኩ ይገልጻል፤ ለምሳሌ ዋለያ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ ይላል(መዝ 42፡ 1)፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር ሆይ ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች ይላል(መዝ 63፡ 1)፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ሕግ እንደ ብርሃን ሆኖ ሰዎች የሚመራ ስለሆነ መከበር እንዳለበትና የሚያከብሩትም በረከት እንደሚቀዳጁ የሚናገር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ መዝሙር 128 ላይ እግዚአብሔር የሚያከብሩና ትእዛዛቱን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው እያለ ይዘምራል(መዝ 128፡ 1)፡፡ በተጨማሪም ቃልህ እንደ መብራት ይመራኛል፤ ለመንገዴም ብርሃን ነው እያለ የእግዚአብሔር ሕግ ወደ እውነተኛው መንገድ እንደሚመራ ይናገራል(መዝ 119፡ 105)፡፡
ስለ መሲሕ የሚናገሩ(መዝ 2፤ 8፤ 16፤ 22፤ 40፤ 45፤ 69፤ 72፤ 110)፡፡
ይህ የሚያተኩረው እግዚአብሔር ስለሚልከው መሢሕና ስለዘሚያደርግለት ጥበቃና እንክብካቤ ላይ የሚናገር ነው፡፡ ይህ መሢሕ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ(መዝ 2፡ 7) ፣ በቀኙ እንደሚያስቀምጠውና(መዝ 110፡ 1) እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን እንደሆነ ይናገራል(መዝ 110፡ 4)፡፡
ለትምህርት የሚሆኑ (መዝ 37፤ 49፤ 50፤ 52-55፤ 60፤ 74፤ 78፤ 89፤ 104፤ 119፤ 127)፡፡
እነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ብዙ ምክር አዘል አባባሎችና ትምህርቶች ተካተዋል፤ እነዚህም አባባሎችና ምክሮች መጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ ከተገለጹት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡ የሰዎች ትዕግሥት ፣ ታማኝነት ፣ ትሕትና ፣ በጎ ተግባራትና የመሳሰሉት ባሕርያት ወይም ክንውኖች ለሰው ልጅ መንፈሳዊ እርካታ እንደሚያሰጡና ከእግዚአብሔር ዘንድ ጸጋ እንደሚያቀደጁ ይናገራል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ክፉ ማድረግና የእግዚአብሔር ትእዛዝ መዘንጋት ወደ ጥፋት እንደሚመራና ከእግዚአብሔርም ጋር እንደሚያቈራርጥና መጨረሻውም እንደ በረሓ አበባ በፍጥነት መርገፍ እንደሆነ ያስተምራል(መዝ 37፡ 20)፡፡

👉ካህናት የቤተ መቅደስን ደረጃዎች ሲወጡ የሚዘምሩአቸው የመዐረግ መዝሙሮች (መዝ 120-134)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች በተለያየ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው፡፡ የእነዚህ መዝሙሮች አብዛኛው ትኩረት የእግዚአብሔር ጠባቂነት ለማግኘት ቢሆንም ሌሎች አሳቦችም በመዝሙሮች ውስጥ በጸሎትና በልመና መልክ ተካተዋል፡፡
👉ሃሌሉያ ብለው የሚጀምሩት የሃሌል መዝሙሮች (የስብሐት መዝሙሮች) (መዝ 111-113፤ 146፤ 148-150)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች ከሌላው ክፍል የሚለዩበት ዋናው ምክንያት ገና ከመዝሙሩ ጅማሬ እግዚአብሔርን ያመስግናል፡፡ መዝሙሮቹ ሲጀምሩ "እግዚአብሔር ይመስገን" ወይም "እግዚአብሔርን አመስግኑት" በማለት ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ መዝሙሮቹ የምስጋና መዝሙሮች ተብለው ይታወቃሉ፡፡

።።።።።።።።። ሥራይ።።።።።።።።።።።።።።።
የሥራይ በሽታ በልዩ ልዩ ምክንያት ሊመጣ ይችላል
ሥራይ ለዓይን በማይታዩ እረቂቃን ሚክሮቦች ክፍት በሆነ ምግብ እና ውሀ ላይ እንቁላላቸውን ጥሉው እንቁላሎቹ በዚያው ምግብ ላይ እየተፈለፈሉ የተራባውን ጀርም ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ጋራ በመመገብና በመጠጣ ሊመጣ ይችላል ።
የሥራይ በሽታ ምራቅ በአፍ እየሞላ እየነፋ በማቅለሽለሽ ይጀምራል ፤ ከዚያም በሆድ ውስጥ እያደገና እየተስፋፋ ሲራባ በሆድ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ መገለባበጥ ይጀምራል ።
ከዚህ በኋላ ከሆድ ተነስቶ ወደ ልብ እየወጣ ይበጠብጣል
የሁለገብ ስር
የዕፀ መናሄ ስር
የመካን እንዶድ ስር
የአሜራ ስር
የሆሣዕና ስርና ፍሬ
የሽንብራ ስር
የቁንዶ በርበሬ ፍሬ
የአይበደሙ ስርና ቅጠል
የአብስራ ሥር
የዕፀ ድብልቅ ስር
በአንድነት ደቁሶ ሲልም አሬራና ጠጅ እኩል እኩል በማለት አሬራውን 3 ብርጭቆ ጠጁንም ስስት ብርጭቆ አድርጎ ከጠጁና ከአሬራው ጋር እስከ ሰባት ቀን ድረስ ጧት በባዶ ሆድ አንዳንድ ስኒ መጠጣት ነው ።

,,,,,,,,,,,,,,,,እንቅልፍ _ ማጣት ,,,,,,,,,,,,,,,,,
እንቅልፍ ማጣት በልዩ ልዩ ምክንያት ሊመጣ ይችላል ፤ የስራ ብዛት ፤ ብስጭትና የእምሮ እረፍት ማጣት ፤ የደም ማነስና መታወክ ሁሉ መንስኤ ሊሆን ይችላሉ ።

ይህ ሕመም ባስቸገረ ጊዜ በመጀሪያ ወደ ሐኪም ቤት ሄዶ መመርመር ያለበለዚያም ለዚህ በሽታ
የዕፀ መፍርህ ሥር
የዕፀ ጳጦስ ሥር
የግመሮ ተቀጽላ

በአንድነት ወቅጦ ሰልቆ አንድ ስኒ ለክቶ በፍየል ወተት እያፈሉ እስከ ሶስት ቀን ድረስ ጠዋት ጠዋት አንዳንድ ብርጭቆ መጠጣት ነው ።

,,,,,,,,,,,,,,,,,, እንቅልፍ - ለሚበዛበት ,,,,,,,,,,
እንቅልፍ ሊበዛ የሚችለው እንደሚባለው በቆዳ ደም ሥሮች ላይ የሚገኙ እጢዎች ሥራቸውን ሲያቆሙ ነው ይባላል
ይሁን እንጂ የነርቭ በሽታም ይህንን ህመም ሊያባብሰው ይችላል ።
የዚህ አይነት እንቅልፍ መብዛት በየግዜው ተመርምሮ ካልታከሙት በስተቀር ቸል ከተባለ ወደ ሌላ ጠንቅ ከማምራቱም በላይ አካላትን እያደከመ ይጎዳል ።
እንቅልፍ ሲበዛ ፤
የዕፀ ዘዌ ሥር
የዕፀ መፍርሕ ሥር
የግመሮ ተቀጽላ
የዕፀ የሀዩ ሥር
የዕፀ መናሄ ሥር
የደብዛ ተቀጽላ
በአንድነት ወቆጦ ሲልም አንድ ስኒ ለክቶ በፍየል ወተት እያፈሉ በየሶስት ቀን መጠጣት ነው።

,,,,,,,,,,,,,,,, ለሚደነግጥ - ሕፃን ,,,,,,,,,,,,,,,,
ይህ ሕፃናትን የሚያስደነግጥ በሽታ የቅዠት በሽታ ይባላ
እንደአጋጣሚ ሆኖ አንዳንድ ሕፃናት ተኝተውም ሆነ ተቀምጠው ሣለ ሣያስቡት እያባነነ የሚያስጮህና የሚያስደነግጥ አንድ ዓይነት የመናፍስት እርኩሣን በሽታ ነው ።
  ይህ በሽታ ሳይባባስና ሣይቆራኝ ፤
የቀበርቾ ሥር
የጠለንጅ ስር
የጀበራ ሥር
የፍየለ ፈጅ ሥር
የአጋም ሥር
በአንድነት ወቅጠህ በሻይ ማንኪያ አንድ ለክቶ በጣዝማ ማር አዋህዶ ጠዋት ጠዋት በባዶ ሆድ ማብላት ነው ።

🌱🌱ዕፀ አንግሥ ምንድነው🌿🌿

📖#እፀ_አንግሥ የሚደገመው የሚደገመው በእጽዋት ለይ ሲሆን ....
🪴ከባህላዊ ህክምና ውጪ ማለትም እፅዋቶች በእራሳቸው ከሚሰጡት ተፈጥሮአዊ ጥቅም በተጨማሪ ሌላ መንፈሳዊ ሀይልን እንዲቀናጁ በእጽዋቶች ላይ የሚደገመው #እፀ_አንግሥ ይባላል ።
👉 ይህ ፀሎት እፅዋቱን ከመቁረጣችን በፊት ለፈለግነው አላማ እንዲውል #ለዚህ_ሁነኝ ብሎ #እፀ_አንግሡን ደግሞ መቁረጥ ነው ።
👉በ #እፀ_አንግሥ የሚቆረጡ #እፅዋቶች ጥቂት ናቸው ።
👉ብዙ ቦታም በቅለው አይገኙም
👉በርሀማ ቦታ ላይ / ተራራማ ቦታ / በወንዝ ዳርቻ / በገደላ ገደል ቦታ ብዛት በቅለው የሚገኙ ሲሆን
ለሰዎች ለመኖር በማይመች / ሰዎች በማይኖሩበት ቦታ ለይ በጥቅጥቅ ጫካ በቅለው ይገኛሉ ።
👉 የሚሰጡት ጥቅምም እረቂቅ እና አስማታዊ ጥበብን ያካተተ ነው ።
👉እነዚህ #እፅዋቶች ጥቂት ከመሆናቸውም ባሻገር ከስራቸው ጠባቂ መልአክ አላቸው ተብሎ ይታመናል !!!
ለዚህም ነው አንዳንድ ዕፅዋቶች ዝም ተብለው የማይቆረጡት
👉በቅድሚያ ከስራቸው ካሉ ጠባቂ መልአክ ጋር መዋረስ / መወዳጀት / መወሐድ ያስፈልጋል ።
👉ይሄን ለማድረግ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች ያሉት ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የሚያስፈልጉ ነገሮች አሉ እነሱም #ጢሶች #እጣን #ከርቤ #ሉባንጃ እያጤሱ
#የኑግ #የቆሎ ዓይነት ... የመጠጥ አይነት አቅርቦ ማርና ወተት ከእፅዋቱ ስር አፍስሶ ,,, አንቺ እፅ ,,, በተጠጉሽ ,, በሚጠብቁሽ ,, በፈጠረሽ ,, #አምላክ ይሁንብሽ !!! ፍቃዴን ፈፅሚልኝ ?
እየተባለ ወይም የ #እፀ_መላክ #እፀ_አንግስ ደግመህ ማንገሻውን ፀሎቱ ለይ የሚጠይቀውን ግብር አቅርበህ ....
,,, ግብርህ እሄውልህ ,,
ለኔም በዚህ እፅዋት ስም ጉዳዬን ፈጽምልኝ / አድርግልኝ እየተባለ ደጋግሞ መቁረጥና ለተባለው ነገር መሞከር ነው ።
👉ከዚህ ውጪ በድፍረት እፅዋቱን ካለምንም ነገር ካለገቢር ለመቁረጥ ቢሞክሩ አልያም ቢቆርጡት ሁለት ነገሮችን ያስከስታል።
1 . እፅዋቱ ለታሰበው አላማ ሳይውል ይቀራል የመስራት እድል አይኖረውም
👉ምክንያቱም ከላይ እንደገለፅኩት የእፅዋቶች የበላይ ጠባቂ ስላላቸው የእነሱን ፍቃድ በ #ገቢሩ ወይንም #እፀ_አንግሡ መሰረት መጠየቅ አለባችሁ
2 . እፅዋቶች በበላይ ጠባቂ ስለሚጠበቁ ለመቁረጥ አደለም ለመንካትም የሚያሰጉ እፆች ይገኛሉ ።
ስለዚህ በድፍረት ቢነኩዋቸው ሆነ ቢቆርጡአቸው ,, አምእሮን የመንሳት ,, ነውነትን ሽባ የማድረግ ,, ቡዳ ያደርጋሉ ,,መጋኛ ያስመታሉ ,, በመናፍስት ያስጠቃሉ ,,,,,,
መጠንቀቁ የሚበጅ ይመስለኛል ።
👉ሌላው በአንድ ጊዜ በአንድ ቀን ገብሬ #እፀ_አንግስ ደግሜ ያሰብኩትን እሆናለሁ / አሳካለሁ ማለት አይቻልም ።
በአንድ ቀን የመምህርን የዶክተርን ሞያ አውቄ አደርጋለሁ ማለት እስካልቻለ ድረስ
ለእፅም ባንድ ቀን ለምን አልሰራም ብሎ ተስፋ መቁረጥ የለም ።
መለማመድ ወይም የሚፈልጉትን ነገር እስከሚያገኙ ድረስ ከጠበብት ሊቃውንት አባቶች በማማከር ውጤት ይገኛል ።

,,, ለክፉም ለደጉም ይሆናል ብዬ ለእናተ ለጥበብ ወዳጆች አካፍዬአችኃለው።

,,, ጥበብ በራሱ ክፋት የለውም ጥሩም መጥፎም የሚያደርገው የደጋሚው እና የአስደጋሚው ሀሳብ ነው ።

Video is unavailable for watching
Show in Telegram

፯ቱ፤7ቱ፤ሰብዓቱ፤ሰባቱ፤ የቅመም ዓይነቶች ለጨጓራ መፍትሔ ሲውሉ!!!

♦ትህትና ለኢትዮጵያ ልጆች!
♦መዋደድ ለመላው የዓለም ህዝብ!
♦አንድነት ለኢትዮጵያ ህዝብ!

#ከሊቅ እስከ ደቂቅ ብዙ ጊዜ ከአንደበታችን የማይለይ የጨጓራ በሽታ ተጠቂ ኖት?

♥የጨጓራ ባክቴሪያ ወይም ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ(♥

📌የጨጓራ ባክቴርያ የባክቴሪያ አባል ሲሆን ወደ ሰውነታችን በመግባት በምግብ ጉዞ መንገድና ጨጓራ ውስጥ መኖር የሚችል ነው፡፡

የጨጓራ ባክቴርያ የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡-
📌 የሆድ መነፋት፣
📌ግሳት፣
📌የረሃብ ስሜት አለመሰማት፣
📌ማቅለሽለሽ፣
📌ማስመለስ፣
  📌ያለምክንያት ክብደት መቀነስ ሊታዩ ይችላሉ፡፡

✔️በጨጓራ ውስጥ የሚያጋጥም ቁስለት ደም ወደ ከርሳችንና አንጀታችን እንዲፈስ ሊያደርግ ይችላል፤ ከባድ የሚባል የጤና ችግርም ሊፈጥርብን ይችላል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉት ምልክቶች ከታዩን ወደ ሕክምና በመሆድ የምንገኝበትን ሁኔታ መመርመር አለብን፡፡
📌የሰገራ መጥቆርና ደም መቀላቀል ካለ፣
📌ለመተንፈስ መቸገር ካጋጠመን፣
📌ያለስራ የመልፈስፈስና የድካም ስሜት ከተጫነን፣
📌የቆዳ መገርጣትና ራስን የመሳት ሁኔታ ከታየብን፣
📌የተፈጨ ቡና የመሰለ ነገር የሚያስመልሰን ከሆነ፣
📌 ከባድ የሆድ ህመም ካለን የጨጓራ ባክቴሪያ ሊሆን ስለሚችል መታየት አለብን፡፡

✔️አልፎ አልፎ ደግሞ የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራ ካንሰር ሊያስከትል ይችላል፤ እንዲያ ሲሆን በመጀመሪያ አንዳንድ ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፤ ለምሳሌ ማቃር ሊበዛን ይችላል፡፡ በመቀጠል ግን የሆድ ሕመምና ማበጥ፣ ማቅለሽለሽ፣ ያለመራብ ስሜት፣ ትንሽ ከተመገብን በኋላ በጣም የጠገብን የሚመስለን ስሜት መሰማት፣ ማስመለስና ምክንያቱ ያልታወቀ የክብደት መቀነስ ሊታይብን ይችላል፡፡

🙏ምክር
የጨጓራ ባክቴሪያን ለመከላከል የምንወስደው እርምጃ ሌሎች ጀርሞችን ለመከላከል ከምንወስደው የጥንቃቄ እርምጃ ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ይኸውም እጅን በሳሙና ከምግብ በፊትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ በደንብ መታጠብ፣ በፅዱ ሁኔታ ያልተዘጋጀ ወይም የቀረበ ምግብና መጠጥ አለመጠቀም፣ ያልበሰሉ ምግቦችን አለመጠቀም ናቸው፡፡ እንዲሁም ጭንቀትና ውጥረት፣
♦ቅመም የበዛባቸው ምግቦችና♦
ሲጋራ ማጨስ ለጨጓራ ቁስለት የማይዳርጉን ቢሆንም ሁኔታውን ግን ሊያባብሱ ስለሚችሉ ቢያንስ ከቁስለት እስከምንድን ድረስ መጠቀም ወይም ማድረግ የለብንም፡፡
❓ልብ በሉ ቅመም የጨጓራ ህመም እንደሚያባብስ ሁላ ቅመማቅመም የጨጓራ መዳኛ ሲሆኑም እናያለን።

✅የጨጓራ ባክቴርያ፣አሲድ የመርጨት ችግር፣መፍትሔዎቻቸው✅

🌿የጥቁር አዝሙድ ፍሬ
🌿የኮረሪማ ፍሬ
🌿የጤና አዳም ፍሬ
🌿የሰሊጥ ፍሬ
🌿የእንስላል ፍሬ
🌿የፌጦ ፍሬ
🌿የቁንዶ በርበሬ ፍሬ

✅እነዚህ የቅመም ዝርያዎች ከምግብነት ማጣፈጫ አልፈው ለየቅልም ቢሆኑ እጅግ ፍቱን እና ውስብስብ ያሉ ችግሮችን የመፍታት ዓቅም ያላቸው አሁን ደግሞ በሕብረት ሁነው የጨጓራ በሽታን ለማከም በሰፊው የጥበብ ድህረገጻችን በኔ ጋባዥነት ብቅ ብለዋል።

✅የቅመሞቹ አዘገጃጀት እና አጠቃቀም!
በቅድምያ በንጽሕና ለየብቻ እንዲደርቁ ማድረግ የደረቀ ከገዛንም ለየብቻ  በንጽህና መፍጨት።

✅ከዛ በመቀጠል ንፁህ ሩብ ኪሎ ማር ማዘጋጀት ለስኳር ታማሚዋችም ይሆናል።የስኳሩ መጠኑ ቅመሞቹ ስለሚያቀዘቅዙት አትስጉ!

#ከላይ ያስቀመጥናቸው የቅመም ዓይነቶች ግማሽ ግማሽ የስኳር ማንኪያ ከ ሰባቱም ቅመማቶች በመለካት ወደ ተዘጋጀው ሩብ ኪሎ ማር ማቀላቀል።

#በመቀጠል አንድ ላይ በንጽህና በደንብ አድርገው ማዋሃድ!
ይህ የቅመሞች ውህድ ጧት ጧት አንድ አንድ የስኳር ማንኪያ በመለካት በባዶ ሆድ መብላት።

#መድኃኒቱ ከወሰዱ ከ አንድ ሰዓት በኃላ የሚስማማዎት ምግብ መመገብ ይችላሉ።

#ይህ መፍትሔ ልዩ ከመሆኑ የተነሳ በጨጓራ ምክንያት ለዓስርት ዓመታት የሚያቃጥሉ ነገር፤ስጋ፣ዶሮ ወጥ፤ስንዴ ነክ፣ መብላት የማይችሉትን ማከም የቻለ ልዩ ውህድ ነው።

#ፍቱን ነው።
📌መፍትሔውን ተጠቅመው ምስክር ይሁኑ፡፡

#ውድ የዚህ ድህረገጽ ቤተሰቦች ስለ ሰባቱ ቅመማት ሌላ እና ልዩ ምስጢራቸው በሌላ ጊዜ የማጋራችሁ ይሆናል።

#ይህ ማለት አንድ የጮጓራ በሽተኛ ታደጋችሁ ማለት ነው።
✅SHARE✅ እናድርግ የሰከንድ ስራ ናትና!

❤️ሕይወትን ለመታደግ ንቁ ትውልድን እንፍጠር።
❤️መልካምነት ግዴታችን ነው።
❤️ተፈጥሮን በጥበብ እንቃኛት።

✅የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።

👆👆🌿🌿አዝዋሪት አዙር አዙሪት አሸሺ🌿🌿
/ሽዋሺውይት ነፋስ/ ሸውሻውይት አደናግር ጀብር የሚባል ስም አሉት ሲነኩዋቸው አእምሮ የሚያስረሱና የሚያፈዙ እፅዋቶች ብዙ አይነቶች ናቸው ።
ነገር ግን ከነዚህ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በሰጣት የተፈጥሮ ባህሪይ ጥበብ የምታገለግለውን እፅ እፅፋለሁ ።
ከእነርሱም አንዷ ባለሀረግ ስትሆን ሁለተኛዋ ግን ድቃቃ ቅጠል ያላት ሆና ከስርዋ ድንች የመሰለ እንደእንዝርት ክብ ሁኖ አዝዋሪት የአለው ነው ።
በመጀመሪያ በእፀ እስክንድር /ወንዴው ምስርች/ ለበቅእኔ ቀደምኩሽ ሳትቀድሚኝ ብለህ ንካት ከዚያ በፈለከው ነገር ለዚህ ሁኝኝ ብለህ ነጭ ቄብ ዶሮ አርደህ ቁረጥ ከቆረጥክበት ቦታ ዶሮውን ቀብረህ ስሩን ይዘህ ሂድ ።
ገቢሩ....
1.ለመፍዝዝ በጥቁር ዶሮ ቆርጠህ ስሩዋን ያዝ
2.#ለገንዘብ ከሳጥን ውስጥ ማስቀመጥ
3.#ለገበያ ከገቢያ መሃል ቀብሮ ገበያው ሲሞቅ አውጥቶ ከሚሸጡበት ማስቀመጥ
4.#ለመሰውር ከጥቁር ድመት አንግሰህ ቆርጠህ በግራ ጎንህ ያዝ
5.#ለእጣ አርብ ቀን ነቅለህ ከእጣን ጋር አጥነህ ያዝ
6.#ለመስተባርር እገሌን የእገሌን ልጅ ከዚህ አገር ነቅለህ አብረው ብለህ ነቅለህ በጥቁር ድንጋይ ወቅጠህ በጥቁር ዶሮ ጉበት ነስንሰህ ለጥቁር አሞራ ስጥ
7.#ለመንድግ+ለምህሳበ_ንዋይ  የገበሎና የእስስት እራስ ጊንጥ እንዳለች የእፀልባዊት  የእሺኮኮ ጎመን የአዝዋሪት  /አዙሪት/ ስር በጥቁር ዶሮ ደም ለውሶ አድርቆ በጥቁር ፍየል ቆዳ ቦርሳ አሰፍቶ በውስጡ አድርጎ መያዝ ።
8.#ለግርማ_ሞገስ ‛‛ሜኤል አላልኤል’’ 99 ጊዜ ደግመህ ለዚህ ነገር ሁነኝ ብለህ ቁረጥና ከቀጠጥና ከእፀአንበሳ ስር ጋር ደቁሰህ ግማሹን በነጭ ማር ብላ፡ ግማሹን በነጭ ዶሮ ደም ለውሰህ ያዝ ።
9. #የተመኘህው_ነገር_እንዲሳካ ሻኤል 3 ሸማልዳ 3 አሻማሺል 11 ጊዜ በስሯ ደግሞ ቀጥቅጦ በውሀ ዘፍዝፎ ፊትን ታጥቦ መሄድ ነው ።
10. #ገንዘብ_ለማግኘት ‛‛አጂማን 99፡ አጁማን 49፡ አላጁማን 51’’ ጊዜ በፀደል ቀበሮ ብራና ጽፎ በሳጥን ከስርዋ ጋር ማስቀመጥ ነው ።
11. #ለመፍትሄ_ሀብት ለሲሳይ የገዴ እንቁላል ወይም ልብና ጥፍሩዋን ስርዋን በጥጥፍሬና ጥጥ ሸፍነህ በበላዩ በወርቀ ዘቦ ግምጃ ጠምጥመህ ያዝ ።
12. #ለመስተፋቅር የጎርጎሮ ተቀጽላ የከልብ አፈ ማህፀን ከስርዋ ጋር ደቁሶ ለሴት ከጭንዋ ለወንድ ከክንዱ መቅበር ነው ።
13. #ለምህሳበ ንዋይ የጭላት ወይም የጭልፊት ልብ የእፀ ልባዊትና የአዝዋሪት ስር የወርቅ የብር ሙራጂ ጋር ከኪስ ወይም ከሳጥን ውስጥ ማስቀመጥ ነው ።
አዝዋሪት ከዚህ በላይ ለተጻፉትና ያልተጻፉ ከ 70 በላይ ገቢሮችን ለመስራት በመጀመሪያ ከስርዋ ጠባቂ መልአክ ጋር መለማመድ እና መዋረስ ማለት መወሀድ ያአስፈልጋል ይሄም ማለት የተለያዩ ጢሶች እጣን ከርቤ ሉባንጃ አሰያጤሱ የኑግ የቆሎ ዓይነት የመጠጥ አይነት አቅርቦ ማርና ወተት ከስርዋ አፍስሶ አንቺ እፅ በተጠጉሽ በሚጠብቁሽ በፈጠረሽ አምላክ ይሁንብሽ ፈቃዴን ፈጽሚልኝ እየተባለ ወይም የእፅ መላክ የእፅ ንጉስ ምሰህ ግብርህ ይሄውልህ ለእኔም በዚህ እንጨት ስም ጉዳዬን ፈጽምልኝ አድርግልኝ እየተባለ ደጋግሞ መቁረጥና ለተባለው ነገር መሞከር ነው ።
በአንድ ጊዜ በአንድ ቀን ገብሬ እሆናለሁ ወይም በአንድ ቀን የመምህርን የዶክተርን ሞያ አውቄ አድርጋለሁ ማለት እስከ አልተቻለ ድረስ ለእፅም በአንድ ቀን ለምን አልሰራም ብሎ ተስፋ መቁረጥ የለም ።
መለማመድ ወይም ለፈለጉት ነገር ለዚህ ሁነኝ ብሎ መቁረጥ ነው ።
ለክፉም ለደጉም ይሆናል ።

14. #ለምህሳበ_ንዋይ የጠላህ ሰው እንዳያይህ ስሩን ከእሬት ተቀጽላ ጋር በጥቁር ውርንጭላ አህያ በግራ ጆሮ ደም ለውሶ በግራ ኪስ መያዝ ነው ።
15. #ለአቃቤ_ህግ ስሩን በአሳ ሀሞት ለውሰህ ቀብተህ አውስብ

👉የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
መሪ አምደ ብርሃን !
ሌሎች መፍትሔዎች ለምትሹ በሙሉ
ለበለጠ መረጃ 0918834904 ብለው በስራ ሰዓት ይደውሉ።
✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigetaamedeberhan

🌿ለማታ የማቀርብላችሁ እጅግ መልካም የመዝሙረ ዳዊት ከህቡዕ ስም ጋር በማወዳጀት የሚጸለይ ጥበብ እንዳለ ሁኖ ትንሽ ስለ መዝሙረ ዳዊት ግንዛቤ ይፈጥርልን ዘንዳ ነው ይህንን ማቅረቤ!🌿
👉ይነበብ👇
❤️የመዝሙረ ዳዊት ዓይነቶች እንዴት መለየት እንችላለን? መዝሙራት በምን ዓይነት ሁኔታ ይከፈላሉ? አመዳደባቸውስ እንዴት ነው?❤️

👉የመዝሙራት ዓይነቶች መለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ቀጥሎ የተጻፈው መረጃ ሊመራን ይችላል፡፡
የምስጋና መዝሙሮች ፦

👉ሀ) የእግዚአብሔርን ስም የሚያመስግኑ(መዝ 8፤ 20፤30፤34፤65፤68፤75፤76፤83፤87፤88፤91፤95፤107፤136)፡፡
ለ) ከመከራ ማዳኑን የሚያወድሱ (መዝ 18፤30፤34፤65፤75፤115፤116፤118፤138)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች ዋና ትኩረታቸው እግዚአብሔርን ማመስገንና ማወደስ ነው፡፡ የሚያመሰግኑትም እግዚአብሔር ለፍጥረት ሁሉ ስላደረገውና እያደረገው ስላለው ድንቅ ሥራ ነው፡፡

👉ኃጢአተኛ በኃጢአቱ የሚያዝንበት(መዝ 6፤ 32፤38፤51፤102፤130፤143)፡፡
የዚህኛው ክፍል ዋና ትኩረት የኃጢአተኛ ሰው መጸጸትና ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ልመና ነው፡፡ ኃጢአተኛው እግዚአብሔርን እንዳሳዘነ አምኖ በመገንዘብ ስሕተቱን ይቀበላል፤ ያዝናል፤ ይጸጸታል፤ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ምሕረት ይለምናል፡፡
በመከራ ያለ ሰው የሚጸልይበት (የሚጽናናበት)(መዝ 3፤5፤7፤17፤20፤30፤31፤54፤59፤142)፡፡
በመከራ ውስጥ ያለ ሰው ስለደረሰበት መከራ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል፤ ይመጸናል፤ መከራውን ለእግዚአብሔር ይናገራል፤ መከራ እንዲደርስበት ያደረጉት ሰዎችን ይራገማል፤ በመከራ ውስጥ እያለ እግዚአብሔር ለምን ዝም እንዳለው ይጠይቃል፤ ከመከራው እንዲያወጣውም ይማጸናል፡፡

👉ዘማሪው እግዚአብሔርን ፣ ሕጉንና ቤቱን የሚናፍቅበት(መዝ 16፤ 17፤ 19፤ 40፤ 42፤ 45፤ 63፤ 73፤ 84፤ 119፤ 122፤ 128፤ 132)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች የሚያተኩሩት በእግዚአብሔር ሕግ ፣ በቤተ መቅደስና በኢየሩሳሌም ከተማ ዙሪያ ላይ ነው፡፡ ቤተ መቅደስ እንደ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቦታ የተጠቀሰበትም አለ፡፡ ስለዚህ ዘማሪው ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመሄድ እንደሚናፍቅና እንደሚደሰት ይናገራል፡፡ ዘማሪው እግዚአብሔርን ለማየት እንደሚናፍቅ በተለያየ መልኩ ይገልጻል፤ ለምሳሌ ዋለያ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ ይላል(መዝ 42፡ 1)፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር ሆይ ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች ይላል(መዝ 63፡ 1)፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ሕግ እንደ ብርሃን ሆኖ ሰዎች የሚመራ ስለሆነ መከበር እንዳለበትና የሚያከብሩትም በረከት እንደሚቀዳጁ የሚናገር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ መዝሙር 128 ላይ እግዚአብሔር የሚያከብሩና ትእዛዛቱን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው እያለ ይዘምራል(መዝ 128፡ 1)፡፡ በተጨማሪም ቃልህ እንደ መብራት ይመራኛል፤ ለመንገዴም ብርሃን ነው እያለ የእግዚአብሔር ሕግ ወደ እውነተኛው መንገድ እንደሚመራ ይናገራል(መዝ 119፡ 105)፡፡
ስለ መሲሕ የሚናገሩ(መዝ 2፤ 8፤ 16፤ 22፤ 40፤ 45፤ 69፤ 72፤ 110)፡፡
ይህ የሚያተኩረው እግዚአብሔር ስለሚልከው መሢሕና ስለዘሚያደርግለት ጥበቃና እንክብካቤ ላይ የሚናገር ነው፡፡ ይህ መሢሕ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ(መዝ 2፡ 7) ፣ በቀኙ እንደሚያስቀምጠውና(መዝ 110፡ 1) እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን እንደሆነ ይናገራል(መዝ 110፡ 4)፡፡
ለትምህርት የሚሆኑ (መዝ 37፤ 49፤ 50፤ 52-55፤ 60፤ 74፤ 78፤ 89፤ 104፤ 119፤ 127)፡፡
እነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ብዙ ምክር አዘል አባባሎችና ትምህርቶች ተካተዋል፤ እነዚህም አባባሎችና ምክሮች መጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ ከተገለጹት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡ የሰዎች ትዕግሥት ፣ ታማኝነት ፣ ትሕትና ፣ በጎ ተግባራትና የመሳሰሉት ባሕርያት ወይም ክንውኖች ለሰው ልጅ መንፈሳዊ እርካታ እንደሚያሰጡና ከእግዚአብሔር ዘንድ ጸጋ እንደሚያቀደጁ ይናገራል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ክፉ ማድረግና የእግዚአብሔር ትእዛዝ መዘንጋት ወደ ጥፋት እንደሚመራና ከእግዚአብሔርም ጋር እንደሚያቈራርጥና መጨረሻውም እንደ በረሓ አበባ በፍጥነት መርገፍ እንደሆነ ያስተምራል(መዝ 37፡ 20)፡፡

👉ካህናት የቤተ መቅደስን ደረጃዎች ሲወጡ የሚዘምሩአቸው የመዐረግ መዝሙሮች (መዝ 120-134)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች በተለያየ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው፡፡ የእነዚህ መዝሙሮች አብዛኛው ትኩረት የእግዚአብሔር ጠባቂነት ለማግኘት ቢሆንም ሌሎች አሳቦችም በመዝሙሮች ውስጥ በጸሎትና በልመና መልክ ተካተዋል፡፡
👉ሃሌሉያ ብለው የሚጀምሩት የሃሌል መዝሙሮች (የስብሐት መዝሙሮች) (መዝ 111-113፤ 146፤ 148-150)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች ከሌላው ክፍል የሚለዩበት ዋናው ምክንያት ገና ከመዝሙሩ ጅማሬ እግዚአብሔርን ያመስግናል፡፡ መዝሙሮቹ ሲጀምሩ "እግዚአብሔር ይመስገን" ወይም "እግዚአብሔርን አመስግኑት" በማለት ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ መዝሙሮቹ የምስጋና መዝሙሮች ተብለው ይታወቃሉ፡፡

👉የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።

20 last posts shown.