በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
# ህልመ ሌሊት
በአፍላ የጉልምስና ወቅት አባለ ዘርዕ ወደ ሙሉ የዕድገት ደረጃ መድረስ ብቻ ሳይሆን መሥራትም ይጀምራል፡፡
በዚህ ወቅት ከኃፍረተ አካል ዘርዓ ብእሲ የተባለ ፈሳሽ ነገር ይወጣል፡፡ የወንድ ወጣቶች ሰውነት ይነስም ይብዛ በየጊዜው "ዘርዓ ብእሲ" ወይም "የወንድ ዘር" ተብሎ የተጠቀሰውን ፈሳሽ ንጥረ ነገር ያስወጣል፡፡ ለዘር የበቁ ወጣቶች ዘር የሚከፍሉት ወይም የሚወጣቸው በልዩ ልዩ መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም በሚያልሙበት ወቅት ነው፡፡ የዚህ አይነቱን ሕልም መጽሐፈ መነኮሳት በአንድ ስፍራ "ሕልመ ጽምረት" በሌላ ቦታ ደግሞ "መስቆርርት ሕልም" ሲለው ይገኛል፡፡ ሕልሙን ያየው ሰው ደግሞ "ዝንየት መታኝ" ወይም "ሕልመ ሌሊት አገኘኝ" ይላል፡፡
"ሕልመ ሌሊት" ኃጢአት ነውን?
በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ የሚከሠት ሕልመ ሌሊትን እንደ ኃጢአት እንዲቆጠርና እንዳይቆጠር የሚያደርጉ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ስለዚህ ህልመ ሌሊትን በጥቅሉ ኃጢአት ነው ወይም አይደለም ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን እንደ ኃጢአት እንዲቆጠር የሚያደርጉ ሁኔታዎችን በመጠኑ መዘርዘር ይቻላል፡፡
1/ አጋንንት የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ መንገድ ክፉኛ ይዋጓቸዋል፡፡ የሰው ልጆች ሲያንቀላፉ አጋንንት ግን ለቅጽበት እንኳን አያሸልቡም፡፡ ያንቀላፋው ሰው እስኪነቃ ድረስ እንኳን አይጠብቁትም፡፡ አጋንንት የሰውን ልጅ በተኛበት ክፉ ክፉ ሕልም በማሳየት ይፈትኑታል፡፡ አንድ ጊዜ የተራቆተ የሴት ገላ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወንድና ሴት አለሌና ባዝራ እየሆኑ ሲጨዋወቱ በምትሐት ያሳዩታል፡፡ በዚህ ጊዜ እርሱም በዝሙት ሐሳብ ይሳብና በሕልሙ ዝሙት ሲፈጽም ያድራል፡፡ በዚህ መልኩ የተከሰተ ሕልመ ሌሊት "ጸዋግ" ወይም "ኅሡም" ሕልም ይባላል፡፡ ክፉ ወይም ጥፉ ሕልም ማለት ነው፡፡ በዚህ መልኩ አጋንንት ሰውን እንደሚዋጉት በመጽሐፈ መነኮሳት እንዲህ ተጽፏል፡፡ "ሰይጣናት የሰውን ልጅ ቀን ቀን ክፉ ሐሳብ በማሳሰብና በማሰራት በሌሊት ደግሞ ዝሙት የሞላበት አስጸያፊ ሕልም በማሳየት ይዋጉታል" ማለት ነው፡፡
★በዚህ መልኩ ሰይጣናት ያቀረቡለትን ረቂቅ ፈተና ከመቃወም ይልቅ ደስ እያለው የሚያጣጥም ማለትም ከመጸጸትና ከመቆጨት ይልቅ በደስታ ስለ ዝሙት የሚያሰላስል፣ የሚዳራ፣ የሚዛለል፣ ወደ ዝሙት ከሚያመሩ ማናቸውም ነገሮች የማይሸሽ ሰው እነዚህ ነቅቶ ሳለ ያልተቃወማቸውን ተግባራት በሕልሙ በሚፈጽማቸው ጊዜ በተግባር እንደፈጸማቸው ያህል ኃጢአት ሆነው ይቆጠሩበታል፡፡ ይህንን የሚያስረዳ እንዲህ የሚል የመጻሕፍት ቃል ይገኛል፡፡ "በቀን ነቅቶ ሳለ ኃጢአትን ወዶ የሚቀበልና ገልጾ የማይናዘዛት ለዚያ ሰው የረከሰች ሐሳቡ፣ ሕልሙ ኃጢአት ሆና ትቆጠርበታለች፡፡" ማለት ነው፡፡
በተጨማሪም "በንሥሐ ሥራ የማይደክም (ንሰሐ የማይገባ)፣ በቀደመው ኃጢአቱ እግዚአብሔር ይቅር በለኝ የማይለው ለዚያ ሰው የሚያጸይፉ ሕልሞቹ ዕዳ ሆነው ይቆጠሩበታል፡፡" ማለት ሲሆን ይህ የሆነበት ምክንያት ሰውየው የነዚህ ሥራዎች ተቃዋሚ ባለመሆኑ ነው፡፡ ይህም ንስሐ ባለመግባቱ ይታወቃል፡፡ እነዚህን ኃጢአቶች የማይቃወም ሰው ደጋፊ ስለሆነ በነዚህ ኃጢአቶች ለምን እጠየቃለው ለማለት አይችልም፡፡
ከስራ ብዛት ሕልም እንደሚታይ ጠቢቡ ሰሎሞን "ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል" በማለት የተናገረው ቃል ያስረዳል/መክ፭:፫/። እንደዚሁም ሁሉ ከምኞት ብዛትም ሕልም ሊከሰት ይችላል፡፡ ክፉ ምኞት በሕልምም ቢሆን ማርከሱ አይቀርም፡፡ ሐዋርያው ይሁዳ "እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ" በማለት የጻፈው መልእክት እዚህ ቦታ ላይ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ /ይሁ.፩:፰/ እንደሚታወቀው ነፍስ እንደ ሥጋ አትተኛም እንቅልፍም በእርሷ ዘንድ የለም፡፡ ስለዚህ ነፍስ በእንቅልፍ ልቤ ነው በማለት ማመካኘት አትችልም፡፡ ነፍሳችን በረከሰ ሕልም ምክንያት ከተጠያቂነት ነፃ መሆን የምትችለው ከእንቅልፍ ባልወሰደን ባልተኛንበት ጊዜ ተግባረ ዝሙትን በመቃወምና በመጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መሆኗን ስታስመሰክር ብቻ ነው፡፡ ይህም በሀዘንንና በፀፀት ከንስሀ አባት ዘንድ በመቅረብና በመናዘዝ ይገለጣል፡፡
★ሌላው ሕልመ ሌሊትን እንደ ኃጢአት የሚያስቆጥረው ሁኔታ አብዝቶ መመገብ ነው፡፡ ጾም ለጽድቅ ሥራ ሁሉ መሠረት እንደሆነ እንደዚሁ አብዝቶ መመገብም የኃጢአት ሁሉ መሠረት ነው፡፡ "እህልም ጉልበትን ያጠነክራል" ተብሏልና፡፡ ሰው ሁሉ ለቁመተ ሥጋ ያህል መመገብ ያሻዋል፡፡ መዝ.፻፫:፲፭ ሆኖም ለልዩ ልዩ የምግብ ዓይነቶች መጎምጀትና ከዚያም አልፎ አብዝቶ መመገብ ነፍስን ለስጋ ማስገዛት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ገዢዋን ተገዥ ማድረግ በመሆኑ ግፍ ነው፡፡ ንጉስ ለወታደር እንደመገዛት ነውና፡፡
ለሥጋ/ለሰውነት/ መገዛት የሚያሻውን ሁሉ ጥሮ ግሮ ማቅረብ የገዛ ሰውነትን ማምለክ ነው፡፡ ሐዋርያው "ሆዳቸው አምላካቸው ነው፡፡" በማለት የተናገረው "እንብላ እንጠጣ ነገ እንሞታለን" በማለት ከሞት በኋላ ተከትሎ የሚመጣባቸውን ወቀሳና ፍርድ ችላ ላሉ ሰዎች ነው፡፡ በአዳምና በሔዋን ሊነገር የማይችል ውርደትና ጉስቁልና ያመጣባቸው ለሆዳቸው መገዛታቸው ወይም ለመብል መሳሳታቸው መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ፊልጵ.፫:፲፱፡ ፩ቆሮ፲፭፥፴፪ ዘፍ.፫፥፩-፳፬
ወጣቶች ይልቁንም በዝሙት ሥራና ሐሳብ በእጅጉ የሚፈተኑ ሰዎች በሚገባ መጾም አለባቸው፡፡ በሰውነት ላይ የዝሙት ፆር ጸንቶ ሳለ አብዝቶ መመገብ የሚቃጠል እንጨት ላይ ጋዝ እንደማርከፍከፍ ነው፡፡ ጋዙ እንጨቱን የበለጠ እንደሚያቀጣጥለው አብዝቶ መመገብም የዝሙት ፍላጎትን የበለጠ እንዲበረታ
ያደርገዋል፡፡ አንድ ሰው በንቁ ልቡና ሳለ (ባልተኛበት ሰዓት) ወደ ኃጢአት የሚመሩትን ነገሮች ተግቶ እየተቃወመ ነገር ግን በተኛና ባንቀላፋ ጊዜ ዝንየት(ህልመ ሌሊት) ቢያገኘው በተራክቦ ዘር በማፍሰስ ያያት ሕልሙ ዕዳ ሆና አትቆጠርበትም፡፡ መሐሪ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውየው ተቃወማት እንጂ ወዶ ወደ እሷ እንዳልተሳበ ያውቃልና፡፡ አንቀላፍቶ ሳለ ዘሩ ቢወርድ ፈልጎ አላመጣውምና ዕዳ አይሆንበትም፡፡ ነገር ግን ተቃውሞ ማራቅ አልተቻለውም፡፡
★ "ዝንየትና" መንፈሳዊ ሥርየቱ
በየትኛውም ሁኔታ ዝንየት ያገኘው ሰው በዚያው እለት ሥጋ ወደሙ በቀበል (መቁረብ) አይችልም፡፡ አንድ ሰው ለሌሎች ለቁርባን የሚደረጉ ዝግጅቶችን ያሟላ ቢሆንም ሕልመ ሌሊትን በማየቱ ብቻ ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል ብቁ አይሆንም፡፡
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ የሚከለከለው ከቅዱስ ቁርባን ብቻ አይደለም፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመግባትም ይከለከላል፡፡ ለመግባትም የሚፈቀድለት ልብሱን ካጠበ ወይም ከቀየረና ገላውን ከታጠበ በኃላ በማግስቱ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ገጽ ፳፬) ወደ ቤተ መቅደስ መግባት አይቻልም ማለት ስለ ወር አበባ በሚያትተው አንቀጽ እንደተገለጸው ወደ ቤተ መቅደስ አይግባ እንጂ የመጀመሪያውን ቅጽረ ቤተክርስቲያን ዘልቆ በመግባት ጸሎት፣ ትምህርትና የመሳሰሉትን መንፈሳዊ ተግባራት በዕለቱም ቢሆን ማከናወን ይችላል።