#ከዜናዎቻችን| የቢሾፍቱ ከተማ ለዱባይ ባለሀብቶች በሊዝ ሊሰጥ መሆኑን መረጃ ማቅረባችንን ተከትሎ ነዋሪዎች አዲስ መረጃ ከመንግስት ተነገረን አሉ
(መሠረት ሚድያ)- መሠረት ሚድያ ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃው ቢሾፍቱ ከተማ ለዱባይ ባለሀብቶች በሊዝ እንደተሸጠ ለነዋሪዎች እንደተነገራቸው ጠቁሞ ነበር።
በዚህም ምክንያት ነዋሪዎች በአንድ ሳምንት ከመኖርያ እና የስራ ቦታቸው እንዲነሱ መታዘዛቸው መታወቁን ዘግበን ነበር።
ይህን ተከትሎ በደረሰን መረጃ መሰረት ደግሞ የቢሾፍቱ ከተማ አመራሮች ባሳለፍነው ሳምንት መባቻ ነዋሪዎችን ሰብስበው የአየር ካርታ ላላቸው ነዋሪዎች በምትኩ 105 ካሬ ቦታ እንሰጣለን ማለታቸው ታውቋል።
"በተመሳሳይ ለገበሬዎች 105 ካሬ እና የሊዝ ዋጋ ካሳ እንከፍላለን ብለውን ሄደዋል" በማለት ተናግረዋል።
ቢሾፍቱን 'በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል' ለማድረግ እየተሰራ ካለው ስራ ጋር በተያያዘ በርካታ የከተማው ቦታ ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሊሰጥ እንደሆነ በመጀመርያ የተሰማው የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ነበር።
(#ከዜናዎቻችን በሳምንቱ በቪድዮ ዩትዩብ ላይ ያቀረብናቸውን የተመረጡ መረጃዎች ቆየት ብለን በድጋሜ በፅሁፍ የምናቀርብበት አምድ ነው)
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia