ዛሬ ምሽት ከደብረ ሲና 52 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
- በቅርብ ቀናት ከተከሰቱት ርዕደ መሬቶች በመጠኑ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል
(መሠረት ሚድያ)- ዛሬ ለሊት 7:20 ላይ የተከሰተው ይህ ርዕደ መሬት 5.1 ሆኖ በሬክተር ስኬል እንደተመዘገበ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል፣ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ንዝረቱ እንደተሰማቸው እየጠቆሙ ይገኛሉ።
ይህ በቅርብ ቀናት ውስጥ በአብዛኛው አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ከተከሰቱት ርዕደ መሬቶች በመጠኑ ከፍተኛው እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ የተጠጋ ሆኖ ተመዝግቧል።
የሰሞኑን ተደጋጋሚ ክስተት ተከትሎ በርካታ የጥንቃቄ መልእክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia