መሠረት ሚድያ ቃሊቲ አካባቢ ስለሚገኝ የወጣቶች ማጎርያ ካምፕ በቅርቡ ያወጣውን ዜና የሚያረጋግጥ መግለጫ ኢሰመኮ ሰጠ
(መሠረት ሚድያ)- መንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መሠረት ሚድያ ታህሳስ 19/2017 ዓ/ም ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ ስለሚገኝ የወጣቶች ማጎርያ ካምፕ ያወጣውን ዜና የሚያረጋግጥ መግለጫ ማምሻውን አውጥቷል።
ሚድያችን በዚህ ዘገባው በአዲስ አበባ ከቃሊቲ ማሰልጠኛ ውሀ ልማት ጀርባ በሚገኘው እና ምስሉ ላይ በሚታየው ማጎርያ ካምፕ ውስጥ እድሜያቸው ከ15 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ጭምር በየግዜው እየገቡበት እንደሆነ ጠቁሞ ነበር።
ለውዝ አዟሪ፣ ሊስትሮ፣ የሀይላንድ እቃ ሰብሳቢ፣ መንገድ ላይ የሚለምኑ፣ የቀን ሰራተኞች ወዘተ መንገድ ላይ እየተያዙ ያለምንም ጥያቄ ተጭነው እየተወሰዱ እንደሚገኙም መረጃ አጋርተን ነበር።
ኢሰመኮ ዛሬ ባወጣው መግለጫው በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. ባደረግኳቸው ክትትሎች በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ 'ቃሊቲ አካባቢ' ተብሎ በሚጠራው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ሰፈር ባለ ሰፊ መጋዝን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ማእከል/ቦታ የማስገባት ድርጊት አሁንም መቀጠሉን ተገንዝቤያለሁ ብሎ የመረጃውን እውነትነት አረጋግጧል፡፡
"ወደ ማቆያው ከገቡት ሰዎች መካከል በማእከሉ ከመቆየት እና የእርሻ ሥራ ከመሥራት እንዲመርጡ በማድረግ፤ የእርሻ ሥራ ለመሥራት የመረጡ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ እርሻ ጣቢያዎች ተወስደው እንዲሠሩ እንደሚደረግ ለመገንዘብ ተችሏል። ይህም የነጻነት መብታቸውን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶቻቸውን የሚጥስ ነው" በማለት ኢሰመኮ አስታውቋል።
አክሎም "በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት፣ የሚደረጉ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ጉባኤዎች እንዲሁም ከሌሎች ተመሳሳይ ኹነቶች ጋር በተያያዘ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎችን በኃይል በማንሳት በአንድ ስፍራ እንዲቆዩ የማድረግ አሠራር እንዲቆም፤ ወደመጡባቸው አካባቢዎች የመመለስ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ሰብአዊ መብቶቻቸውን ባከበረ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ እና ችግሩ ሁሉ አቀፍ የፖሊሲ ምላሽ የሚያስፈልገው መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ የኢሰመኮ ክትትሎች ተጠቁሟል" ብሏል።
በዚህ ስፍራ ታስረው የተለቀቁ ዜጎች "መኝታ እና ምግብ ብሎ ነገር የለም፣ ጤነኛ ሆኖ የገባው ህይወቱ አልፎ ሲወጣ አይተናል" በማለት ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia