• ታኅሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ገነተ-ማርያም ቀበሌ አርክን በተባለ ልዩ ጎጥ ሲያመርቱ የዋሉትን የጤፍ ምርት ለመጠበቅ አውድማ ተኝተው የነበሩ 5 የአንድ ቤተዘመድ አባላት የሆኑ አርሶ አደሮች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንደተገደሉ የተጎጂዎች ቤተሰቦች ለኢሰመኮ አስረድተዋል። በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ታጣቂዎች (በተለምዶ “ፋኖ”) ቀደም ብለው ከአካባቢው በመሸሻቸው የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ሲገቡ አውድማው ላይ ተኝተው ያገኟቸውን በግጭት ውስጥ ምንም ተሳትፎ የሌላቸውን አርሶ አደሮች እንደገደሏቸው ጨምረው ገልጸዋል።
• ታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ከደብረ ማርቆስ ከተማ ወደ ደብረ ኤልያስ ወረዳ በጭነት መኪና ተሳፍረው በመጓዝ ላይ የነበሩ የደብረ ኤልያስ ወረዳ የመንገድ ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት 2 ሴት ሠራተኞች ጎዛመን ወረዳ ውግር ቀበሌ ሲደርሱ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጠቂ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ከመኪና አስወርደው ከወሰዷቸው በኋላ በማግሥቱ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ተገድለው እንደተገኙ የሟች ቤተሰቦች አስረድተዋል።
• በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ብሔረሰብ ዞን እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሸካ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች መካከል አልፎ አልፎ በወሰን አለመግባባት ምክንያት ግጭቶች የሚከሰቱ ሲሆን፣ ኅዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ በዘለቀ ግጭት በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ብሔረሰብ ዞን፣ መንገሺ ወረዳ፣ የሪ ቀበሌ ጂፎር ንኡስ ቀበሌ ውስጥ 5 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል። እንዲሁም የተወሰኑ ነዋሪዎች የቤት ውስጥ ዕቃዎችን እና የእርሻ ሥራ መሣሪያዎችን ጨምሮ ንብረት ተዘርፏል።
• በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን፣ ሳጃ ወለል ወረዳ፣ የላሎ ገለታ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት አቶ ዳግም ኢገዙ እና አቶ ጸጋ ተክሌ የተባሉ 2 ሰዎች ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) ጋር “ግንኙነት አላችሁ፤ ስንቅ እና መረጃ ታቀብላላችሁ” በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከተያዙ በኋላ በዚያው ዕለት ማለትም መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በጥይት ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተጥሎ ተገኝቷል።
• መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ወረዳ ኢተያ ገምባ ጀቴ፣ ኢላላ እና ጢሮ ኢላላ ቀበሌዎች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) ታጣቂዎች “በአካባቢው ላለው የመንግሥት ጸጥታ ኃይል ድጋፍ ታደርጋላችሁ” በሚል አቶ አለኸኝ አባተ፣ አቶ ተመቸው አርቄ፣ አቶ በለጠ ከበደ፣ አቶ ተመስጌን ተፈራ እና አቶ አስፋ ርቀው የተባሉ 5 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል፡፡
• መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ኢተያ ገምባ ጀቴ ቀበሌ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አቶ ሙሳ ኑሩ፣ አቶ ኢብራሒም መሐመድ፣ አቶ ኢብራሒም ኡመር እና አቶ ጉልማ (ከ5 ቤተሰቦቹ ጋር) በአጠቃላይ 9 ሰዎችን ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) “ድጋፍ ታደርጋላችሁ” በሚል ገድለዋል።
• ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቤጊ ወረዳ፣ የኮበሬ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አቶ መሐመድ ሀጂ ጀማል የተባሉ ሰው ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) “ድጋፍ አድርገሃል” በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከተያዙ በኋላ በዕለቱ በጥይት ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተጥሎ ተገኝቷል።
• ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቆንዳላ ወረዳ፣ የወንዲ ዶች ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት አቶ ምናለ ቃስም የተባሉ ሰው “ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) ድጋፍ ታደርጋላችሁ” በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከተያዙ በኋላ በጥይት ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተጥሎ ተገኝቷል።
• ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ንጋት ላይ በምሥራቅ ሸዋ ዞን፣ ዱግዳ ወረዳ፣ ብርቢሣ እና ጋሌ በተባሉ ቀበሌዎች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) አባላት “የመንግሥት አካላትን ተባብራችኋል” በሚል በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ባደረሱት ጥቃት ሕፃናትን፣ ሴቶችን እና አረጋዊያንን ጨምሮ 17 ወንዶች እና 21 ሴቶች በአጠቃላይ 38 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል፤ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪል ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል። 78 መኖሪያ ቤቶችንም አቃጥለዋል።
• ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት በምሥራቅ ሸዋ ዞን፣ ዱግዳ ወረዳ፣ መጃ ላሉ ቀበሌ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) አባላት በቀበሌው በሚኖሩ የጉራጌ ብሔር ተወላጆች ላይ በምሽት ቤታቸውን በላያቸው ላይ በማቃጠል እና ጥይት በመተኮስ በአጠቃላይ 12 ሰዎችን ገድለዋል።
• ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት 2፡00 ሰዓት አካባቢ በምሥራቅ ሸዋ ዞን፣ በመቂ ከተማ 02 ቀበሌ ማንነታቸው በውል ባልታወቀ ነገር ግን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) አባላት መሆናቸው በተጎጂዎችና በተጎጂ ቤተሰቦች የተጠረጠሩ የታጠቁ አካላት በፈጸሙት ጥቃት 3 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን አንድ የ12 ዓመት ሕፃንን ጨምሮ 4 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል።
• ኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ሌሊት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) ታጣቂዎች በአርሲ ዞን፣ ሽርካ ወረዳ፣ ሶሌሳ ረከታ እና መከና ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ የክርስትና እምነት ተከታዮችን ከሌሎች ነዋሪዎች ለይተው በፈጸሙት ጥቃት 13 ሰዎችን ከመኖሪያ ቤቶቻቸው በማስወጣት በጥይት ገድለዋል።
ምንጭ ኢሰመኮ
መረጃን ከመሠረት!