ከ 119 ዓመት በፊት ልዑል ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል አርፈው ቀብራቸው ሐረር በቅ/ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተከናወነበት ዕለት
ከ 119 ዓመት በፊት ልዑል ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል አርፈው ቀብራቸው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተከናወነበት ዕለት ነበር።
በ 1894 ዓ.ም በመጀመሪያ ላይ በብርቱ ስለታመሙ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ጥር 4 ቀን ከከተማቸው ከሐረር ተነሱ። ጥር 9 ቀን ቡርቃ ወንዝ አድረው የጥምቀትን በዓል አክብረው ከዋሉ በኃላ ህመሙ ስለፀናባቸው ወደኀላ ተመልሰው ቁልቢ ገብተው በሐኪም ይታከሙ ጀመር።
እዚሁ ሲታከሙ ከቆዩ በኃላ መጋቢት 13 ቀን 1898 ዓ.ም ቁልቢ ላይ አርፈው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
አፄ ምኒልክ የአርባቸው ለቅሶ የሚለቀሰው አዲስ አበባ እንዲሆን ባዘዙት መሠረት ሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን በአዲስ አበባ በዙሪያዋ ያሉት የየገዳማቱና የየአድባራቱ ካህናት የክርስቲያን የፍታት ጸሎት ተደርጎ በማግስቱም ማክሰኞ የጊዮርጊስ ዕለት ሚያዝያ 23 ቀን 1898 ዓ.ም በሰኢ ሜዳ ላይ ድንኳን ተተክሎ መኳንንቱና ሠራዊት ተሠብስቦ የራስ መኮንን የማዕረግ ልብሳቸውንና የራስ ወርቃቸውን ኒሻኖቻቸውና የጦር መሳሪያቸውን ተይዞ በፈረሰና በቅሏቸው በወርቅ እቃ ተጭነው በሠራዊት መካከል እየተመላለሱ ተላቅ ለቅሶ ተለቀሰላቸው:: ከአልቃሾቹም አንዱ ደግነታቸውን ለማስታወስ እንዲህ ብሎ አሟሸ
(ግንቦት 1 ቀን 1844 -- መጋቢት 13 ቀን 1898)

ስልከኛው ሲያረዳ ነገር ተሳሳተው
መኮንን አይደለም ድኃ ነው የሞተው
(ግንቦት 1 ቀን 1844 -- መጋቢት 13 ቀን 1898)