የግል ኩባንያዎች ነዳጅ እንዲያስመጡ ተፈቀደ ።
የግሉ ዘርፍ ከሽያጭ በተጨማሪ ነዳጅ ማስመጣት እንዲችል የሚፈቅደው አዋጅ ስራ ላይ ዋለ፡፡
የነዳጅ ግብይት አዋጅ ቁጥር 1363/2017 ላለፈው 11 አመት በስራ ላይ የነበረውን አዋጅ የቀየረ ሆኖ ባለፈው ጥር ነበር በፓርላማ የፀደቀው፡፡ ይህ አዋጅ በሳለፍነው ሳምንት በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ስራ መግባቱ ነው የታወቀው፡፡
በዚህም እስካሁን በመንግስታዊው የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ብቻ ተይዞ የነበረውን የነዳጅ ከውጭ ገዝቶ የማስገባት ስራ ሌሎች ኩባንዎችም ማከናወን እንዲችሉ በር የሚከፍት ነው፡፡
የነዳጅ ንግድ የመንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ አካል ሆኖ እየተሰራበት የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡
Via @mussesolomon