🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
📣ለሴቶች

ነገ ጠዋት 3:30 በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ

ልዩ ሙሃደራ

⭐️የጀነት ቁልፍ⭐️

⚠️መልእክቱን ሼር በማድረግ የምንዳ ተካፋይ እንሁን!
https://t.me/darulhadis18


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
 📣የማይቀርበት ልዩ ፕሮግራም ለሴቶች

"فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ .. " محمد ١٥

" እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን…" ሙሀመድ 15

❓ከሞት በኋላ ህይዎት እንዳለ የሚያምን ሰው ሁሉ ምኞት ጀነት መግባት ነው አይደል?

🔑ወደዚህ ውድ ወደሆነው  ዘላለማዊ ሀገር ለመግባት ቁልፉን ማግኘት ግድ በመሆኑ
የዚህ እሁድ ዉሎ በአላህ ፈቃድ ስለቁልፉ መማማር ይሆናል።

▫️በተጨማሪም በእለቱ ሌሎች አስተማሪ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።


➤እሁድ ታህሳስ 27፣2017

➤ከጠዋቱ 3:30-:6:00

➤18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

⚠️የፕሮግራሙ ታዳሚ በመሆን፣ እህቶችንም በመጋበዝ የእውቀትና የምንዳ ተካፋይ ይሁኑ!

https://t.me/darulhadis18


Forward from: ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር – አዲስ አበባ ibnu Mas'oud islamic center
በ2017(1446/47)ቁርአን እና የዲን ትምህርት ፈላጊዎች ልዩ እድል

    በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ስር የሚገኘው ዳሩል ሐዲሥ ኢንስቲትዩት ለአዋቂ ወንዶች የተመላላሽ የቁርኣን ሒፍዝ ፕሮግራም እና ኪታብ ትምህርት ፕሮግራም በማዘጋጀት ምዝገባ ጀምሯል። ከታች የተቀመጡትን መስፈርት የምታሟሉ  ተማሪዎች ከመስከረም  3 -መስከረም 9 ድረስ በኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር ዋና መርከዝ 18 አደባባይ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ያስታውቃል።

 1. ለቁርአን ሒፍዝ ፕሮግራም
ቁርአን ነዘር በተጅዊድ የጨረሰ እና ቢያንስ 3ጁዝ የሀፈዘ የዲን ትምህርት እየተማረ የሚገኝ(መሰረታዊ የዲን ኪታቦችን የጨረሰ)
እድሜው ከ18 እስከ 25 የሆነ
     
2. በጀማሪ ጧሊበል ኢልም ደረጃ 
ቁረኣንና መሰረታዊ የአቂዳና ፊቅህ ኪታቦችን የቀራ

3. በመካከለኛ ጧሊበል ኢልም ደረጃ
በፊቅህ ፣ በአቂዳ፣ በነህው በሶርፍ መሰረታዊ መትኖችን የቀራ እና ዐረብኛ ማንበብ የሚችል
 ለሁሉም እርከኖች የጋራ መስፈርቶች
በጥሩ ስነ-ምግባር የታነጸ ለዚህም መረጃ ማቅረብ የሚችል።

የመርከዙን ደንቦች አክብሮ ለመማር ዝግጁ የሆነ።

ከተማረ በኋላ ዑማውን ለማገልገል ዝግጁ የሆነ።

መግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል።

ተያዥ ማቅረብ የሚችል።

👉 ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ፡‐ 18 አደባባይ አካባቢ የሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር 

👉 ትምህርቱ የሚሰጥባቸው ቀናት
👉 ለቁርአን በሳምንት 6 ቀናት፤ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
👉 ለኪታብ በሳምንት 4 ቀናት ከሰኞ እስከ ሐሙስ
👉 ትምህርቱ የሚሰጥበት ሰዓት፡‐ ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:00 
👉 ለምዝገባና ለበለጠ መረጃ:- ስልክ 0912617007
                      
 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

____
Ibnu Mas'oud islamic center
https://t.me/merkezuna


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
📣የመዝጊያ ፕሮግራም

በኢብን መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር የዳሩል ሐዲስ የሸሪዓና የቋንቋ ኢንስቲትዩት ባለፈው አንድ ዓመትና በዚህ ክረምት ወራት ለወንድ ታዳጊዎችና ወጣቶች ሲሰጥ የቆየውን ትምህርት መጠናቀቅ ምክኒያት በማድረግ የተዘጋጀ ፕሮግራም

በዕለቱም

⚡️በተለያዩ ዳዒዎች የሙሀደራ ፕሮግራም

⚡️በተማሪዎች የሚቀርቡ  ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይኖራሉ

🗓 አሁድ ጷጉሜ  03/2016

⏰ ከጠዋቱ 3:00-6:30 ጀምሮ

🕌 18 በሚገኘው ኢብን መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ነሲሃ መስጅድ

https://t.me/darulhadis18


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
📣የክረምት ትምህርት መዝጊያ ፕሮግራም ለሴቶች

ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር በክረምቱ በዋናው መርከዙና በቅርንጫፎቹ ለታዳጊና ወጣት ሴቶች ሲሰጥ የቆየውን ትምህርት መጠናቀቁን ምክኒያት በማድረግ የተዘ ጋጀ ልዩ መድረክ።

🗞በዕለቱ የሚኖሩን ፕሮግራሞች

▫️ምክር ለተማሪዎች:የተማሩትን መተግበር

▫️ምክር ለወላጆች: ልጆች ከአላህ የተሰጡን አደራዎች

▫️በተማሪዎች የሚቀርቡ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች

🗓የፊታችን ቅዳሜ ጷግሜ 2፣2016

🕡 ከ3:00-6:30

📎መልእክቱን በማሰራጨት በኸይር ስራ ተሳታፊ እንሁን!

🕌18 አካባቢ በሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መሰኡድ ኢስላሚክ ሴንተር

https://t.me/darulhadis18


Forward from: ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር – አዲስ አበባ ibnu Mas'oud islamic center
🎓 በዓይነቱ ልዩ የኮርስ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም በኢማም አህመድ መስጂድ ተጋብዘዋል። በዕለቱም፤

⭐️ ከተለያዩ ሀገራት በመጡ ታላላቅ ኡለማዎች ምክር ይሰጣል

⭐️ ብልጫ ላሳዩ ተማሪዎች የሽልማት ስነስርዓት

⭐️ በኮርሱ ተሳታፊዎች የሚቀርቡ እና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይኖራሉ

🗓 እሁድ ነሀሴ 19/2016

⏰ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ

🕌  ፕሮግራሙ የሚካሄደው አለም ባንክ በሚገኘው ኢማሙ አህመድ መስጆድ ነው


_
ibnu Mas'oud islamic Center
@merkezuna


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
📣ለ2017 ምዝገባ  ጀምረናል (ለሴቶች)

"አላህ መልካም ለሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል”

ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር አዲስ አበባ 18 በሚገኘው መርከዝና  በቤተል ቅርንጫፍ ለ2016 የትምህርት ዘመን የዲን ትምህርቶችን ለመስጠት ምዝገባ ጀምሯል።

የሚሰጡ ትምህርቶች

1⃣ 📖 ቁርአን ለወጣቶች እና ለእናቶች

🔅 በነዘር (ለጀማሪዎች)
🔅 በነዘር (በተጅዊድ )

ከመሰረታዊ የዲን ትምህርት ጋር

🕥የሰአት አማራጭ

▪️ጠዋት ከ1:00-2:30 ጠዋት ከ3:00-6:30፣ከሰአት 8:00-9:30 ፣ከአስር በኋላ10:30-12:00

🔅 ቁርኣን ሂፍዝ (ከ2:30-10:00)

2⃣ ከ 15 -18 አመት ላሉ ታዳጊዎች የቀን ሙሉ የቁርኣንና የተርቢያ ትምህርት

3⃣ የ2 አመት የሰርተፊኬት ፕሮግራም(ከ3:00-6:30)

4⃣ለተማሪና ለሰራተኛ በሳምንት 1 ቀን ቅዳሜ ጠዋት (3:00-6:30) የኪታብ ቂርአት

5⃣ የ2 አመት የዲፕሎም ፕሮግራም

🗓የመመዝገቢያ ቀናት ከነሐሴ 1-20፣፡2016

ከሰኞ እስከ ጁሙዓ  ከጠዋቱ  3:00-9:30

ለበለጠ መረጃ፦
ለ18 ☎️ 0904 36 66 66

ለቤተል ☎️0911062499/
0913840323  ይደውሉ።

⚠️መልእክቱን ሼር በማድረግ  የበኩላችንን አስተዋጽዖ እናድርግ።

https://t.me/darulhadis18


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
⚘️ዲን እየተማሩ ነውን?

🪴ኢስላም ከማንኛውም ነገር በፊት ዕውቀትን በመገብየት ላይ አደራ ይላል፡፡ ምክንቱም የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዕውቀትን መሰረት ያላደረጉ ከሆነ አላዋቂ ሳሚ ... እንደሚባለው ብሂል ከልማቱ የምንዘፈቅበት አዘቅቱ ያመዝናል፡፡  አንዳንዴም በኛ ሳይገደብ የኛው የጥፋት ረመጥ ይቀጥልና ሌሎችን እኛ የሰመጥንበት አዘቅጥ ውስጥ እንዲዋኙ የጥፋት ጀልባ እና መቅዘፊያ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ 
       
🪴ቁርአን ስለ እውቀት ፋይዳዎችና ስለ አዋቂዎች ደረጃ ብዙ ይላል። ዓዋቂው አምላካችን ስለ እውቀት ባለቤቶች ከፍ ያለ ደረጃ ዓዋቂዎች በሚገነዘቡት መልኩ እንዲህ ይላል፡-

"يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ" [٥٨:١١]
«አላህ ከናንተ እነዚያ ያመኑትንና እነዚያ ዕውቀት የተሰጡትን በደረጃ ከፍ ያደርጋል» ሙጃደላህ፡11
                           
🪴ታላቁ ሶሃብይና የቁርአን ተፍሲር ዓዋቂ ዓብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንዲህ ሲል የአንቀፁን መልዕክት የሚያጠናክር ንግግር አላቸው «የተማሩ ሰዎች ደረጃ ከተራው ሙዕሚን ሰባት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡ ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ ያለው ርቀት የአምስት መቶ ዓመት ርቀት ይሆናል»

በሌላ የቁርአን አንቀፅ አላህ እንዲህ ይላል፡-

"إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ"  [٣٥:٢٨]
«አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው»  ፋጢር፡28

🪴መልዕክተኛው (ﷺ)  እንዲህ አሉ፤ «ዕውቀትን ቅሰሙ አላህን የምትፈሩት ባወቃችሁት ልክ ነውና»

አዎን! የማያውቁትን አካል እንዴት ተገቢውን ፍራቻ ይፈሩታል?!

🪴አላህ መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲጨምርላቸው እንዲጠይቁት ያዘዘው ብቸኛ ነገር ዕውቀት ነው! ከየት አመጣኸው ትይኝ ይሆናልና ማስረጃውን :-

"وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا "
«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ በል» 20፡114

🪴የትኛውም የዕውቀት ደረጃ ላይ ብንገኝ በአላህ ከታገዝንና ጥረት ካደረግን ብዙ መሻሻል ይቻላልና አሁኑኑ ጥረት ማድረጉን እንጀምር።

🤲አላህ  በኢስላማዊ ዕውቀት ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንል አንድ ያግዘን፤ እውቀትን ያግራልን። ልባችንን በቁርአን ያብራልን።

አሚን !
_
@abujunaidposts


Forward from: ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር – አዲስ አበባ ibnu Mas'oud islamic center
  📣 بشرى سارة لطلبة العلم

✍ التعليق على رسالة الشيخ محمد ابن عبد الوهاب إلى أهل القصيم
   
لقاء علمي مع الشيخ الدكتور خالد بن عبد اللطيف محمد نور حفظه الله

✍ السبت والأحد ٢١-٢٢ محرم ١٤٤٥ هے بدأ من الساعة التاسعة والنصف صباحا

المكان؛ مسجد النصيحة بمركز ابن مسعود الإسلامي في حي ١٨، أديس أببا

/////___////

🌟 ልዩ የዒልም መድረክ በነሲሓ መስጂድ
ከዶ/ር ሸይኽ ኻሊድ ዓብዱለጢፍ ሀፊዘሁላህ

👌ቅዳሜና እሁድ ሐምሌ 20‐21/2016 ቅዳሜና አሁድ ከ 3፡30 ጀምሮ 18 ማዞሪያ በሚገኘው ነሲሓ መስጂድ

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

____
🕌 ibnu Masoud islamic Center
t.me/merkezuna




Forward from: NESIHA TV ነሲሓ ቲቪ
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ብስራት ለወላጅና ለልጆች
እንኳን ደስ አላችሁ!!!


ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ከነሲሃ ቲቪ ጋር በመሆን ልዩ የክረምት ኮርስ በተመላላሽ እና በርቀት ለሁሉም ፆታ በተመቻቸ መልኩ ያዘጋጀን መሆናችንን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው።

🖍ዕድሜያቸው ከ10 - 12 ለሆኑ ልጆች፣
ከ13- 14 ለሞላቸው ታዳጊዎች፣ እንዲሁም 15 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ወጣቶች፣

✔️እምነታቸውን ከምንጩ የሚያውቁበት !
✔️የኢባዳን አፈፃፀም የሚማሩበት!
✔️ኢስላማዊ ተርቢያ የሚቀስሙበት!
✔️መልካም አርአያዎቻቸውን የሚተዋወቁበት ታላቅ መድረክ

በተጨማሪም ከሸሪዓዊ እውቀት ባሻገር ለወጣቶች የWeb Development ኮርስ በማዘጋጀት የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን ከፍ የሚያደርጉበት እድል አመቻችቷል።

ምዝገባውንም በአካል መጥተው አሊያም በኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ።
ለወንዶች ከሰኔ 17- 28 ባሉት ቀናት 18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዋና ቢሮ በስራ ሰዓት በአካል በመምጣት መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን፤
ለሴቶች ደግሞ ከሰኔ 17- 23 18 ባለው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ,በቤቴልና በፉሪ ቅርጫፎች መመዝገብ ይችላሉ።

በተጨማሪም የትም ሳይሄዱ www.course.nesiha.tv ላይ በመግባት መመዝገብ ይችላሉ

📌ለበለጠ መረጃ
 ለወንዶች በስልክ ቁጥር 0912617007/0912023190/0912617005
 ለሴቶች ለ18 ኢብኑመስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር 0904366666
ለቤቴል ቅርጫፍ 0911105653/0911375952/
ለፉሪ ቅርጫፍ 0911479151/0912058590 ይደውሉ፤ ይመዝገቡ፤ በእውቀት ብርሀን ከፍ ይበሉ።

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
@nesihatv


✨የሴቶች አረፋ እና ተያያዥ ነጥቦች

🎙በሸይኽ ኢልያስ አህመድ (ሐፊዘሁላህ)

@ustazilyas


Forward from: Taha Ahmed
በዓረፋ ቀን ልንተገብራቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት የትኞቹ ናቸው?

ኢብኑ ረጀብ ለጣኢፉ አል-መዓሪፍ በተባለው ኪታባቸው ላይ የጠቀሱትን እና ሌሎችም ዑለማዎች ከጠቆሟቸው ነጥቦች ከዋና ዋናዎቹ የተወሰኑትን በአጭሩ እንመልከት:‐
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ:- “በዓረፋ እለት ከእሳት ነፃ መውጣቱን እና ለወንጀሎቹ ምህረትን የሚፈልግ ሰው ለዚያ ሰበብ የሚሆኑ ነገሮችን መፈፀም ይኖርበታል:: ከነዚያ ሰበቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:-
1️⃣ የዓረፋን ቀን መፆም:-
አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)

2️⃣ መላ አካላትን አላህ ከከለከላቸው ነገሮች ማራቅ በተለይ ፈፅሞ አላህ ምህረት ከማያድርግለት ወንጀል በእሱ ላይ ማጋራት (ሺርክ) እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል::

3️⃣ የተውሂድ መገለጫ የሆነውን እና የአላህን አጋር የሌለው ብቸኛ አምላክነት እንዲሁም በሁሉ ነገር ላይ ቻይነት የሚያረጋግጠውን “ላ ኢላሃ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢ ቀዲር ” የሚለውን ዚክር ማብዛት:: ይህ ዚክር በእለቱ አላህን ከምናወድስባቸው ቃላት የተሻለውና ምርጡ እንደሆነ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ በተናገሩበት ወቅት እንዲህ ሲሉ አሳውቀዋል:– "እኔና ከኔ በፊት የመጡት ነብያት ከተናገርነው ንግግር ሁሉ በላጩ ይህ ነው።"

4️⃣ አላህን ምህረት እንዲያደርግለት እና ከእሳት ነፃ ከሚወጡት ባሮቹ እንዲያደርገው አብዝቶ መለመን:: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- “ከዓረፋ ቀን የበለጠ አላህ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም::” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በተጨማሪም ዱዓእ ተቀባይነት ሊያገኝበት ከሚችልባቸው ቀናት መካከል አንዱ እና ልዩ ቀን ነው:: መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት የዓረፋ ቀን ዱዓእ ገልፀዋል:- “ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓእ ነው::” ስለሆነም በዚህ ቀን ለራሳችን፣ ለወላጆቻችን፣ ለልጆቻችን፣ ለባለቤቶቻችን፣ ለቅርብ ዘመዶቻችን፣ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ በርትተን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።

5⃣ በአጠቃላይ በተሰማራንበት ቦታ ሁሉ በቻልነው አቅም መልካም ነገሮችን ከማድረግ እንዲሁም አላህን ከማውሳት ልንሳነፍ አይገባም:: በተለይ ከሰላት በኋላ ተክቢራ ማድረግ ከዛሬው እለት ፈጅር ሰላት የሚጀምር መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም:: ይህም ማለት ተክቢራ ማድረጉ ዛሬ የተጀመረው ከአምስቱ ግዴታ ሰላቶች በኋላ የተገደበ (ሙቀየድ) በመባል የሚታወቀው ነው እንጂ ከዚያ ውጪ ያልተገደበ (ሙጥለቅ) በመባል የሚታወቀው የተክቢራ አይነት እስከ አያመ-አተሽሪቅ ማብቂያ ማለትም የአስራ ሶስተኛው ቀን ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ይቀጥላል::

አላህ በመልካም ስራ ላይ ያበረታን እንዲሁም ይቀበለን!

✍️ ጣሀ አህመድ

🌐
htt rel='nofollow'>ps://t.me/tahaahmed9


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
📣 አስደሳች ዜና ለወላጆች

ክረምት እየደረሰ ነው ……

አያምልጦት እድሉን ይጠቀሙ !


ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳረል ሀዲስ ከ 10 አመት በላይ ላሉ ለሴት ታዳጊዎችና ወጣቶች ልዩ የ 2 ወር የዲን ኮርስ በ4 ደረጃዎች አዘጋጅቶ መምጣታችሁን እየጠበቀ ነው።

ይህ ኮርስ በአላህ ፈቃድ

✔️እምነታችውን ከምንጩ የሚያውቁበት !

✔️ተቀባይነት ያለው ሶላት እንዲሰግዱ የሚያግዛቸውን ት/ት የሚያገኙበት!


✔️ኢስላማዊ ስነ ምግባርና አደቦችን የሚቀስሙበት!

✔️አርአያዎቻቸውን የሚተዋወቁበት!

✔️ለሴት ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ክህሎት የሚማሩበት!

🔸በየደረጃው የሚሰጡ ኮርሶች ፦
☑️ቃኢዳ
☑️ቁርአን
☑️ዐቂዳ 
☑️ ፊቅህ
☑️ ተርቢያ 
☑️ ሲራ
☑️ ተጅዊድ…

ትምህርቱ የሚሰጠው
📆ከሐምሌ 1-ነሐሴ 30
🕘ጠዋት ከ2:30-6:30

የምዝገባ ቀን፦ ከሰኔ 3-23(የኢድ ቀናቶች ዝግ ነው)
ሰአት :-ከጠዋት 3:00-9:00

▫️ለበለጠ መረጃ:-

1.ለ18 ማዞሪያ (መርከዝ ዋና ቢሮ)
0904366666

2.ለቤተል ቅርንጫፍ
0911105653/0911375952

3 ለፉሪ ቅርንጫፍ
0911479151/
0912058590
⚠️ወላጆች ልጆቻችሁን በማስመዝገብ ለልጆቻችሁ መስተካከል ሰበብ በማድረስ ኀላፊነታችሁን ተወጡ!

👆መልዕክቱን ሼር እናድርገው።

@darulhadis18


Forward from: 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
💎ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀናት💎

➢ ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሐጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያለቸው እነኝህ ቀናት ናቸው።

➢ ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል ፦

«ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው »

(ሰሂሁል ጃሚዕ 1133)

📌 በነዚህ ቀናቶች በአላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑና ወደሱ የሚያቃርቡንን መልካም ስራዎች በመተግበር ላይ ልንበረታና ቤተሰቦቻችንንም የዚህ ኸይር ተቋዳሽ እንዲሆኑ በማድረግ ልናሳልፈው ይገባል።

📩 http://t.me/nesiha_ouserya




Forward from: 🗞 የ አቡጁነይድ መልዕክቶች Abujunaid posts
10ቱ የዙልሒጃ ቀናት.pdf
333.4Kb
🗞 ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት

✍ ዝግጅት፦ አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ ህዳር 2004

🔗 የፅሁፉ ሊንክ
https://d1.islamhouse.com/data/am/ih_articles/single/am_Virtues_of_the_Ten_Days_of_Dhul_Hijjah.pdf

🔗 telegram Share Link
https://t.me/abujunaidposts/374


----------------
📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
ፕሮግራሙ ሴቶችንም ያካትታል


Forward from: ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር – አዲስ አበባ ibnu Mas'oud islamic center
🌟 ልዩ የዳዕዋ ዝግጅት በነሲሓ መስጂድ

👌እሁድ ዙልቂዕዳ 26/1445 ዓ.
ግንቦት 25/2026 ከ 3፡30 ጀምሮ 18 ማዞሪያ በሚገኘው ነሲሓ መስጂድ


ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

__
🕌 ibnu Masoud islamic Center
t.me/merkezuna



20 last posts shown.