አዲስ የተሾመዉ የትግራይ አስተዳድር
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዐቢይ አቶ ጌታቸው ረዳን ከስልጣን አውርደው ታደሰ ወረደን መሾማቸውን ለእነ ደብረጽዮን አሳወቁ። የህወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልና የስራ አስፈጻሚ አባሉ አቶ ፍስሃ ጽዮን ትናንት ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው ነበር፡፡
በዚህ ጉዟቸውም ዐቢይ አህመድንና ሌሎች የብልጽግና ከፍተኛ ባለስልጣናትን በአራት ኪሎ አግኝተው ተነጋግረዋል ተብሏል፡፡
በዚህም ወቅት ሬድዋን ሁሴን ፣ ጌዲዮን ጢሞቲዎስና ሌሎች ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን ፣ መቀሌን ለቀው ወደ አዲስ አበባ የሸሹት አቶ ጌታቸው ረዳ ግን አልተገኙም ተብሏል፡፡
ዐቢይ እነ ደብረጽዮንን “እናንተ ከኤርትራ ጋር ሆናችሁ እኔን ለማጥፋት ለምን መስራት ጀመራችሁ” ሲሉ መጠየቃቸውም ተሰምቷል፡፡
ሆኖም እነ ደብረጽዮን ግን “እኛ ከኤርትራ ጋር በዚህ መንገድ ለመስራት አልተስማማንም ፣ እንዲያ አይነት ስምምነት ብንፈጽም ኖሮ እዚህ ምን እናደርጋለን” ማለታቸውም ታውቋል፡፡
የውስጥ አዋቂ ምንጮች እንዳሉትም እነ ደብረጽዮን ዐቢይን “ትግራይ ላይ ለምን እንደዚህ እንደከፋህና እንደጨከንክ አልገባንም” ብለውታል ተብሏል፡፡
በዚህም ወቅት ዐቢይ ፈገግ ብለው “ ጌታቸውን አንሳልን አላችሁኝ አነሳሁላችሁ ፣ ታደሰ ወረደን ሹምልን አላችሁ ሾምንላችሁ ፣ ታዲያ ሌላ ምን ትፈልጋላችሁ” ማለታቸው ታውቋል፡፡ ከታደሰ ጋር ተስማሙና ሰላም አምጡ ማለታቸውም ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም ዐቢይ አህመድ በይፋ በቀጣይ ሰኞ እና ማክሰኞ ለታደሰ ወረደ ይፋዊ የሹመት ደብዳቤ እንደሚሰጡ ተነግሯል፡፡
ታደሰ ወረደ ከዐቢይ አህመድ ፣ ከብርሃኑ ጁላና ከሬድዋን ሁሴን ጋር ባደረጉት ውይይት የክልሉ መሪ እንዲሆኑ መወሰኑ ታውቋል፡፡
ጀነራል ታደሰ ወረደ በትግራይ ጦርነት አይነሳም ፣ ነገሮች ከቁጥጥራችን ውጭ አይደሉም ፣ ዐቢይም ጦር እንደማያዘምት ነግሮኛል ማለታቸው ታውቋል፡፡
እኒህ ሰው የቲዲኤፍ አዛዥ ሲሆኑ በቀጣይ ከእነ ደብረጽዮን ጋር አብረው እንደሚሰሩም ይጠበቃል፡፡ ዐቢይ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዘዳንት አድርገው እንደሾሙም እየተነገረ ነው፡፡
የጌታቸው ረዳ እጣ ፈንታ በይፋ ባይታወቅም ፣ ዐቢይ ግን በሁለት ዓመቱ ጦርነት ያወረዱባቸውን የስድብ ናዳ አሁን ከህወሃት ሰዎች በይፋ ከለይዋቸው በኋላ ሊያወራርዱባቸው ይችላሉ የሚል ግምት አለ፡፡
እንዲሁም ነባር ፖለቲከኞቹ የህወሃት ሰዎችና የጦር ጀነራሎች ዐቢይን አምነው እስከመጨረሻው ለመገዛት ተስማምተው ይቀጥላሉ ወይ የሚለው ተጠባቂ ሆኗል፡፡
ምናልባትም ዐቢይ ከኤርትራ ጋር እጀምረዋለሁ ላሉት ጦርነት ጠላትና ሃይል ቅነሳ ለማድረግ በሚል ህወሃቶችን ያሻቸውን እንዲያደርጉ እንደተዋቸው እየተነገረ ነው፡፡