አልፈልግም ስትለኝ እምባዬ እንዳይመጣ ታግዬ ፈገግ አልኩኝ ። ለእምባዬ ፊት መስጠት አልፈለኩም ። የሄደን ሰው እምባ አይመልሰውም ብዬ ነው መሰለኝ !
ግን ከፋኝ ፦
ተደግፌባት ነበር ። አደጋገፌ በጥርጣሬ አልነበረም ። ከኔ እሷን አምናት ነበር ፣ እንዳልጎዳት ስጣጣር ነበር ። እንዳላሳዝናት ሁኔታዬን ሁሌ አየው ነበር !
አልፈልግህም ስትለኝ ....
ጭር አለብኝ በግርግር ውስጥ ጭርታ ስሜት እንዴት ይወለዳል ? ጭርታው አስፈራኝ ጭርታው ድብርት ወለደ ። ስታብራራ መልስ መስጠት አልፈለኩም ። እንዲ ስለው እንዲ ይላል ብላ ምላሽ ተሸክማ እንደመጣች ገብቶኛል ።
ምላሽ ካጠና ሰው ጋር ውይይት ትርፍ የለውም ። ማን ለማን ብሎ ከማን ጋ ይሆናል ? ይሄ መስቀል ሳላጉረመርም የምሸከመው ነው !!
ግን ይሄን ሁሉ ሲሰማኝ ፈገግ ብዬ ነበር ።
እሷም አልፈልግህም ስለው ፈገግ ብሎ ነበር ትል ይሆናል ።
©Adhanom Mitiku
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery