አልዋሽም ነበረ ቃል አባይ አረገኝ ዳግም ተመልሶ ፍቅር አገረሸብኝ ክልክሉልኝ ፍቅርን ገባ ወጣ ይላል እኔእንደው ትቻለው ምን ፍጠር ይለኛል ታምሜለታለው በእሱ የተነሳ ምዬ ትቼው ነበር ስሙን ላላነሳ አውጄ በይፋ ተናግሬው ለሰው እንዴት የተውኩትን መውደድ ልመልሰው አገርሽቶብኛል መውደድ እንደ አመሉ ስምል ያዳመጡ እንግዲህ ምን ይሉ ፍጹም የተውኩትን ልቤን ስሽረው ደግሞ አገረሸብኝ ዳግመኛ ሳየው ይታዘበኝ ወዳጅ ሀገር ጉድ ይበለኝ ላይዘልቅ አግደርድሮ ፍቅር ድል ሲያረገኝ መውደድ መውደድ ያለ የበፊቱንማ በአንዱ ላይ ያይላል አንዱ ሳይሰማ ወራትና አመታት ቀናት የማይሽሩት መውደድ ለካ ሃያል ነው የማይታገሉት
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏