ቁርአን የልብ መድኃኒት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦ 📖
《 ቁርአንን አሳምሮ የሚቀራ እሱ ከነዛ ታላላቅ መላኢካዎች ይመደባል》
━══ ❁❁❁ ═══
አብደሏህ ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ብለዋሉ፦

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


የ ረመዳን የየቀኑ ክስተቶች  #Ramadhan 11

1 -  በ 9 ኛዉ አመተ ሂጅራ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)  ከ ተቡክ ዘመቻ ከተመለሱ ብኋላ ፣ የ ሰቂፍ ወፍድ/ጀመዓ መዲና መጥተዉ  እስልምናን የተቀበሉበት ቀን ።

2 -  በ ደዉላ ዑመዊያ ዘመን  በ 94 አመተ ሂጅራ ታላቁ ታቢዕይ ( ሰዒድ ኢብን ጁበይር ) በ ሀጃጅ ቢን ዩሱፍ የ ተገደሉበት ቀን ።

3 - በ 986 አመተ ሂጅራ የ ዑስማኒያ ደዉላ ከ ደዉለቱል  ( ሰፈዋንያ) ጋር ባደሩጉት ትልቅ ዉጊያ በመጨረሻ ዑስማንዮች አሸነፉ።

በዚህ ጦርነት ከ  ሰፍዋንዮች ወደ 15 ሺ የሚጠጋ የ ጦር ሰራዊት አልቀዋል።

( ደዉላ ሰፈዋንያ)  ማለት  በ ኢራን ሀገር የ ሺዓን መዝሀብ አስተምህሮት ለማስፋፋት የተመሰረተ ነበረ።

       🔗SHARE 🔗SHARE 

    ☪ https://t.me/onlyquran11
    ☪ https://t.me/onlyquran11


ረመዿን 11፦ ጁዝእ፡ 11
ቃሪእ፡ አሕመድ አል-ዐጀሚ




“አንዳችሁ አላመነም ‘እምነቱ ሙሉ አይሆንም’ እኔ እሱ ዘንድ ከልጆቹ ከወላጆቹ ከሰዎች በጠቅላላ ይበልጥ ተወዳጅ እስክሆን ድረስ።”

ረሱል (ﷺ)


የረመዳን የየቀኑ ክስተቶች #Ramadhan10

1- የ ሙዕሚኖች እናት  ኸዲጃ  3 አመት ከ ሂጅራ በፊት ወደ አኼራ የሄዱበት ቀን ።

2 - በ 648 አመተ ሂጅራ ( መንሱራ ) ተብሎ በሚታወቀዉ ጦርነት ሙስሊሞች  የ መስቀል ጦረኞችን  አሸንፈዉ ድል የተቀናጁበት ።

3 - በ 485 አመተ ሂጅራ ታዋቂዉ የ እስላም ሚኒስቴር  በ (ኒዛሚያ ) መድረሳ ዉስጥ ትልቅ አስተወፆ ሲያደርጉ የነበሩት ( አቡልሀሰን አልይ ኢብን ኢስሃቅ / ንዛም አልመሊክ ) ተብለዉ የሚታወቁ ወደ አኬራ የሄዱበት።

4 - የ ግብፅ ሙስሊሞች ለ ረጅም አመታት ከ አይሁዳዊያን ጋር ባደረጉት ፊልሚያ በ 1393 አመተ ሂጅራ በ መጨረሻዉ አሸንፈዉ የበላይ የሆኑበት።

    🔗SHARE 🔗SHARE 

    ☪ https://t.me/onlyquran11
    ☪ https://t.me/onlyquran11




ረመዿን አስር፦ ጁዝእ፡ 10
ቃሪእ፡ ዐዲል ረያን




ያኢላሂ:'! ዒባዳቸው ቅቡልነት ከሚያገኙ ባርያዎችህ አርገን!


"የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም!"
~
በነብያችን ﷺ ላይ የሚሳለቅ ራሱን እንጂ እሳቸውን ምንም ሊያደርጋቸው አይችልም። የላካቸው አምላክ "መወሳትህን/ዝናህን ከፍ አደረግንልህ" ብሏቸዋል። ይሄው የዝናቸው ከፍ ማለትም ነው ዛሬ በርካታ ውሾችን እያስጮኻቸው ያለው። ትላንትም የዛሬዎቹ ውሾች አያቶች የመልእክተኛውን ክብር ሊያንቋሽሹ ሞክረው ነበር። አላህ ግን ራሱ ለመልእክተኛው ﷺ ተከላካይ ጠበቃ ይሆንና መልእክተኛው ግን ነገሩን ንቀው እንዲተውት እንዲህ ይጠቁማቸዋል፡-

(فَٱصۡدَعۡ بِمَا تُؤۡمَرُ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِینَ ۝  إِنَّا كَفَیۡنَـٰكَ ٱلۡمُسۡتَهۡزِءِینَ ۝  ٱلَّذِینَ یَجۡعَلُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَـٰهًا ءَاخَرَۚ فَسَوۡفَ یَعۡلَمُونَ ۝  وَلَقَدۡ نَعۡلَمُ أَنَّكَ یَضِیقُ صَدۡرُكَ بِمَا یَقُولُونَ ۝  فَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ ٱلسَّـٰجِدِینَ ۝  وَٱعۡبُدۡ رَبَّكَ حَتَّىٰ یَأۡتِیَكَ ٱلۡیَقِینُ)

"የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለፅ፤ አጋሪዎችንም ተዋቸው። እኛ ተሳላቂዎችን ሁሉ በቅተነሃል። (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፤ በርግጥም (የስራቸውን ዋጋ) ወደፊት ያውቃሉ። አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን በርግጥም እናውቃለን። ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው፤ ከሰጋጆቹም ሁን። እውነቱም (ሞት) እስከሚመጣህ ድረስ ጌታህን አምልክ።" [አልሒጅር፡ 94-99]

ስለዚህ ተሳላቂዎቹ ውሾች ቢሳለቁም የነብያችን ﷺ ዝና የበለጠ ይገናል። የውሾቹ ስም ይከስማል። ውሻ ደግሞ ምን ታሪክ አለውና?! እስኪ የነብያችንና የትላንት ጠላቶቻቸውን ዝና አወዳድሩ። ሲጀመር መወዳደር ይችላሉ? በጭራሽ! “የሰማይና የመሬት ያክል ነው” ብንል እንኳ በትክክል አይገልፀውም።

ግን የነብያችንን ﷺ ክብር ለማጉደፍ ተፍ ተፍ የሚሉ ሰዎች አላማቸው ምን ይሆን? መልሱ ግልፅ ነው።
1.  አንዳንዶቹ በነብዩ ﷺ እውቅና ሂሳብ እውቅና መሸመት የሚፈልጉ ናቸው። “አንዳንዶች ታዋቂዎችን በመተቸት ታዋቂ መሆን ይፈልጋሉ” ሲባል አልሰማችሁም?
2.  ሌሎቹ ደግሞ የኢስላም ውበቱና ሁለንተናዊነቱ የሚያስቀናቸው፤ ከፍተኛ ግስጋሴው የሚያስበረግጋቸው ናቸው። ስለሆነም ሙሐመድን ﷺ ሲያንቋሽሹ የኢስላም ውበቱ የሚደበዝዝ፣ ግስጋሴው የሚገታ ይመስላቸዋል። እውነታው ግን ተቃራኒው ነው። ኢስላም ዛሬ ጠላቶቹን እንቅልፍ በሚነሳ መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ ነው። ስለዚህ ውሾቹ አመል ሆኖባቸው ይጮሃሉ እንጂ የኢስላምን ግስጋሴ ሊገቱት አይችሉም! ውሾቹ ይጮሃሉ፣ ዋው! ዋው! እያሉ። ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል። ውሻ ግመልን ማስቆም ከቻለች ትሞክር።

ባይሆን ከእኛ አንድ ነገር ይጠበቃል። ከሃዲዎችን የነብያችንን ﷺ ስም ለመዘለፍ ያበቃቸው ለነብዩ አስተምሮ ያላቸው ጥላቻ መሆኑ ይታወቃል። አዎ የነቢዩ ﷺ ሱና እጅጉን ያስቆጫቸዋል! እውነቱ ይህ ከሆነ ከሃዲዎችን የበለጠ ለማስቆጨት የሚጓጓ፤ ለሙሐመድ ﷺ እውነተኛ ወዳጅነቱን ማንፀባረቅ የሚፈልግ፣ ብሎም የአላህን ውዴታ ማትረፍ የሚሻ የበለጠ ወደ መልእክተኛው ሱና ይቅረብ። ትእዛዛቸውንም ይፈፅም። ከከለከሉትም ይራቅ። ይህን የሚያደርግ ጠላቱን የበለጠ ያስቆጫል። የአላህንና የመልክተኛውንም ﷺ ውዴታ ያፍሳል። ያ ሱብሓላህ! የአላህና የመልክተኛውን ውዴታ ያገኘ ምን የቀረበት ነገር አለ?! ያ ወሃ፞ቡ አንተ ወፍቀን! ኣሚን

(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 08/2005)
=
✅የቴሌግራም ቻናል✅

🔗SHARE 🔗SHARE 

    ☪ https://t.me/onlyquran11
    ☪ https://t.me/onlyquran11


የረመዳን የየቀኑ ክስተቶች ። #Ramadhan 9

1 / ሙስሊሞቹ በሰቅሊያ ደሴት ዳርቻ በ 212 ሂጅሪያ ሰፈሩ ፣ ( አሰድ ቢኑ ፉራት ) የሚባለው የጦር አዛዥ የ ሰቅሊያን ደሴት በመሃከለኛው ነጭ ባህር ድል በማድረግ ከፈተ ፣ ቦታውም በጣም አመቺ  ነበር ፣ በደቡብ አፍሪካና በጣልያን መሃል አዋሳኝ ቦታ ነው።

2/ በ 270 አመተ ሂጅራ ታላቁ የ ዛሂሪያ መዝሀብ ፈቂህ ና ኢማም ( ሙሀመድ ኢብን ዳዉድ ኢብን አልይ)  ወደ አኬራ ሄዱ ።

ለመጀመሪያ ጊዜ የ ዛሂሪያን መዝሀብ የመሰረቱ ናቸዉ ከዛ ኢማም ( ኢብን ሀዝም ) እርሳቸዉን ተከትሎ ይሄን መዝሀብ አስፋፉት።

3 / በ 1326 ( ቡልጋርያ ) ሀገር ከ ደዉለቱል ኡስማንያ የተነጠለችበት ና ራሷን ችላ የተቋቋመችበት ቀን ።

4 / 1350 ሂጅሪያ በረመዳን 9 አሽ - ሸይክ ( ዩሱፍ ቢን  ኢስማኤል ቢን ዩሱፍ አን ነብሀኒይ ) ወደ አኼራ የሄዱበት ቀን።


ረመዿን አስር፦ ጁዝእ፡ 9
ቃሪእ፡ አቡበከር ሻጥሪ




የ ረመዳን የየቀኑ ክስተቶች ። #Ramadhan 8

1 - በ 665 አመተ ሂጅራ  ( ሱልጣን ዟሂር ባይበርስ ) የ ዓካ / عكا ከተማን ሙሉ በ ሙሉ በ ሙስሊሞች ግዛት ስር ያስገቡበት  ቀን።

2 - ታላቁ የ እስላም ሊቅ እዉቀታቸዉ እንደ ባህር የሆኑት ኢማም ( ጀዓፈር አሷዲቅ ) በ 83 አመተ ሂጅራ የተወለዱበት ቀን።

3 -  ታላቁ ሙሀዲስ  ኢማም ( ኢብን ማጃህ ) በ 273 አመተ ሂጅራ ወደ አኬራ የሄዱበት ቀን።

#Taatewwan baati ramadaana keessa argaman.

( Ramadana 8 ffaa...))

1 - Bara hijra 665 Guyyaa ( Sulxaan Zaahir baybaras)  Magaalaa ( Akkaa عكا ) jeamtu kan harka faranjoota turte Guutuu guuttutti Harka islaamatti galche

2 - Guyya Aalimni Ilmiin isaa akka baharaa tahe imaam ( Ja3afar Assadiq ) itti dhalate bara hijra 83 .

3 - Guyyaa Muhaddisni Hadiisa Sunanaa imaam ( Ibnu maajaah )  bara hijra 273 itti aakirame.

© Muaz shamsu.


ረመዿን 8፦ ጁዝእ፡ 8
ቃሪእ፡ ዐብዱ-ር'ረሕማን አል-ዑሲ




መልዕክቱን ለሌሎችም ያጋሩ 👉

🔈 -{ قال ﷺ }بلغوا عني ولو آية

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብሏል 
ከእኔ አንዲትንም አንቀፅ ቢሆን አድርሱ

ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/onlyquran11
https://t.me/onlyquran11


የናፈቀነው ረመዳን ከመጣ 7 ቀን ተቆጥሯል እኛስ የናፈቅነውን ወር በምን ሁኔታ እያሳለፍን ነው 😢❓


የ ረመዳን የየቀኑ ክስተቶች ። #Ramadhan 7

1 - በ 361 አመተ ሂጅራ እስላማዊ ጃሚዓ / ዩኒቨርሲቲ ( አል_አዝሀር ) ለመጀመሪያ ጊዜ በ ፋጢሚዮች ደዉላ የ ሺዓን አስተምህሮት ለማስፋፋት ታቅዶ የተመሰረተ ።

ግን ከተወሰኑ ዘመናት ቦሃላ በ( ሳላሃዲን አል አዩብ ) ኺላፋ ዘመን ዩኒቨርሲቲዉ ወደ ሱኒ መዝሀብ ተመለሰ ፣ ከዛ ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ታላላቅ የ እስላም ልቃዉንቶችን እያፈራ ይገኛል።

( ልብ በሉ አል፣አዝሀር ዩኒቨርሲቲ  አብዛኛዉ ቀዲም የ ሀገራችን ኡለማዉች የዝህ ምሩቅ ነበሩ። 

ለምሳሌ
የ ታላቁ  ቁርዓን ሙፈሲሮቻችን
1 በ አማርኛ ሼይክ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ ፣
2  ኦሮምኛ ሼይክ መሀመድ ረሻድ አብዱሌ ። رحمهما الله جميعا

2 - በ 251 አመተ ሂጀራ  ታዋቂ የ አህሉሱና ወልጀማዓ ና በ ሱሉክ / ተሰዉፍ ሱኒይ ፈርጥ የ ሆኑ ኢማም السري السقطي ( ሲርይ አስቅጢ ) ወደ አኬራ የሄዱበት ቀን ።

3 - በ 599 ታላቅ ና አንደበተ ርቱህ የ ሆኑ  የ እስላም ፣ዓሊም ( ዘይኑዲን አልይ እብን እብራሂም እብን ነጃ) ወደ አኬራ የሄዱበት ቀን።

🔗SHARE 🔗SHARE 

    ☪ https://t.me/onlyquran11
    ☪ https://t.me/onlyquran11


ረመዿን 7፦ ጁዝእ፡ 7
ቃሪእ፡ ዐብደ-ል'ሏህ በስፈር

20 last posts shown.