ስለ ብዙ ምህረትህ .....
ለቁጥር በሚታክት የምህረት ብዛት እያኖርከኝ እንደሆነ ሳስብ እገረማለሁ። መቆሜን ሳስብ ዛሬ ላይ መድረሴን ሳሰላስል ትዝታዬ ከእኔ የሆነ በጎ ነገር ሳይሆን የምህረትህ ጉልበት ነው። ሁል ጊዜ መኖሬ ሁል ጊዜ በማማርህ ውስጥ የተሰወረ ነው። ለአፍታ ምህረትህን ብታቁርጥ ለነፍሴ ህልውና ገደብ ትሆናለህ። በማይሰለች የምህረት ብዛት ነፍሴን እያረሰረስካት ድርቀቷን አስቀርተሃል።
የበደሌን ክምር ጠራርጎ የወሰደው የምህረትህ ጎርፍ ነው። ርቆ ያለውን ማንነቴን የምህረትህ ፉጨት ድምጽ ነው ጠርቶ ያቀረበኝ። የኃጢአቴን ትውስታ ከውስጤ ያስወጣው የምህረትህ አቅም ነው። ቆምኩ ስል ትውስታኔ ምህረትህ ነው፣ ኖርኩኝ ስል ሀሳቤ እና ማሰላሰሌ ምህረትህ ነውና ክብርህን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። ስለ ብዙ ምህረትህ አመሰግንሃለሁ። አሜን
✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ጥር 18 2017 ዓ.ም ተጻፈ
@orthodox_new_mezmur@orthodox_new_mezmur