Nolawi ኖላዊ ኄር ዘ-ኦርቶዶክስ
ጌታዬ ሆይ !
ልዕልናን በክብርህ ፣ አምላክነትን በገዢነት ፣ አባትነትን በፍቅር የያዝህ ፤ ለኔም ክብሬና ጌታዬ ፣ አባቴና እረኛዬ የሆንከኝ እግዚአብሔር ወልድ ሆይ ተመስገን ። ዛሬን እኖር ዘንድ የአሁን አቅም ፣ አሁንን እቀበል ዘንድ የመኖር ጥበብ ስለሆንክልኝ ክበር ። ከልዕልቶች ሳይሆን የነፍስ ጌጥ ካላት ከድንግል የተወለድህ በመወለድህ ጽድቅና ሰላም የተስማሙልህ አንተ ነህ ። እባክህ ከራሴ አድነኝና ከቃልህ ጋር ልስማማ ። በመወልድህ ዓለሙ ብርሃን ተሟልቷልና እባክህ...