♡ ዝናውን ሰምቼ ♡
ዝናውን ሰምቼ ፈለኩት
ከሾላ ላይ ሆኜ አየሁት
ከአንተ ጋር ነኝ አለኝ መድኀኒቴ
ዛሬስ መዳን ሆነልኝ ለቤቴ
የረከሰው ቤቴን ጌታዬ ሳይንቀው
ጨለማውን ገፍ ብርሃን አደረገው
ለገናና ክብሩ ለእርሱ ተንበርክኬ
ዛሬ ተለወጠ ጎስቋላ ህይወቴ
እንደምን ወደደኝ ምን አግኝቶ ከኔ
ህይወቴ ያደፈ ነው የገባው ኩነኔ
አርሱ ግን ጎበኘኝ በማዳን አዋጁ
ስሙን አተመብኝ አደረገኝ ልጁ
ካለኝ እኩሌታ ለደኃ ሰጣለሁ
የበደልኩትን ሰው በእጥፍ እክሳለሁ
ያንተ ካደረከኝ የአንተ ነኝ ብያለው
ንገስብኝ አምላክ እገዛልሀለው
የአብርሃም አሞላክ የእስራኤል መና
የጠፋውን ሊፈልግ ሊያድን መጥቷልና
እኔንም ጎበኘኝ በማዳኑ ጥሪ
ወሮታውን ክፈይ ነፍሴ ሆይ ዘምሪ
ዝናውን ሰምቼ ፈለኩት
ከሾላ ላይ ሆኜ አየሁት
ከአንተ ጋር ነኝ አለኝ መድኀኒቴ
ዛሬስ መዳን ሆነልኝ ለቤቴ
የረከሰው ቤቴን ጌታዬ ሳይንቀው
ጨለማውን ገፍ ብርሃን አደረገው
ለገናና ክብሩ ለእርሱ ተንበርክኬ
ዛሬ ተለወጠ ጎስቋላ ህይወቴ
እንደምን ወደደኝ ምን አግኝቶ ከኔ
ህይወቴ ያደፈ ነው የገባው ኩነኔ
አርሱ ግን ጎበኘኝ በማዳን አዋጁ
ስሙን አተመብኝ አደረገኝ ልጁ
ካለኝ እኩሌታ ለደኃ ሰጣለሁ
የበደልኩትን ሰው በእጥፍ እክሳለሁ
ያንተ ካደረከኝ የአንተ ነኝ ብያለው
ንገስብኝ አምላክ እገዛልሀለው
የአብርሃም አሞላክ የእስራኤል መና
የጠፋውን ሊፈልግ ሊያድን መጥቷልና
እኔንም ጎበኘኝ በማዳኑ ጥሪ
ወሮታውን ክፈይ ነፍሴ ሆይ ዘምሪ